Ethio Culture

Ethio Culture entertainment

01/02/2026

86ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ውሎ በፎቶ ሲገለጽ ይሄን ይመስላል።

ባህል ደስታ - ባህል ፍካት - ባህል ውበት

ድንቅ ምድር!

27/01/2026
የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ የደስታ ማብሰሪያ ስነ-ስርዓት ክብርት ሸዊት ሻንካ ያስተላለፉት መልዕክት፦ጥር 19፣ 2018ዓ.ም ...
27/01/2026

የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ የደስታ ማብሰሪያ ስነ-ስርዓት ክብርት ሸዊት ሻንካ ያስተላለፉት መልዕክት፦

ጥር 19፣ 2018ዓ.ም ወላይታ ሶዶ

ኢትዮጵያ ሀገራችን የበርካታ ብሔሮችና ብሔረሰቦች መገኛ፤ የውብ ባህሎች፣ ታሪኮችና ዕሴቶች ባለቤት ነች፡፡
ብዝኃነት በተግባር የሚገለጥበት፤ የህዝብ ትስስርና አብሮነት ጎልቶ የሚታይበት፤ ፍቅርና ሰላም የሚጸናበት፤ መከባበርና መተሳሰብ የሚተገበርበት፤ ድንቅ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ሀይማኖታዊ ክብረ በዓላትም መገለጫዎቿ ናቸው፡፡

ባህላዊ፣ ታሪካዊና ሀይማኖታዊ ክብረ በዓላትና ዕሴቶች እንዲለሙና እንዲጠበቁ ይዘታቸውንና ስርዓታቸውን ሳይለቁ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሻገሩ በህግ ስልጣን የተሰጠው የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መሆኑን አስታውሰዋል።

በመላው ሀገራችን የሚገኙ ባህላዊ ዕሴቶችና ትውፊቶች ጎልተው እንዲታዩና እንዲተዋወቁ፣ እንዲለሙ የማድረግ ሥራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በተለይ የሀገራችን ቱባ ባህላዊ ዕሴቶች ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ ከፍ ለማድረግ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማካተት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የወላይታ ህዝብ ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" ሀገራችን ኢትዮጵያ ካሏት ቱባ ባህላዊ ክብረ በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡ ጊፋታ የሰላምና የህብረት ተምሳሌት፤ የአንድነታችንና የጥንካሬያችን መሠረት፤ የአብሮነታችንና የኩራታችን ምንጭ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የበርካታ እሴቶች ባለቤት የሆነው የወላይታ ህዝብ ጊፋታ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች መዝገብ ውስጥ በይፋ መስፈሩ፤ ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ ብቻ ሳትሆን የጥንታዊ ባህል፤ፈ፣ ጥበብና ስልጣኔም መነሻ መሆኗን የሚያሳያል ብለዋል፡፡

ይህ ዕውቅና የኢትዮጵያዊያን ብዛሃ ባህል፣ ዕሴትንና ውበትን ለዓለም ከማስተዋወቁም በላይ፣ ባህሉን ጠብቆ ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ ያለንን ኃላፊነት በእጅጉ የሚጨምር፤ የበለጠ እንዲስፋፋ የሚያደርግ፤ ትውፊቶቹ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የሚሰጡ ጥቅሞች እንዲጎለብቱ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።

ጥር 20 ጀምሮ በእንጅባራ
23/01/2026

ጥር 20 ጀምሮ በእንጅባራ

ቱባ ባህሉ ከቱባ እናቶች🙏✅
23/01/2026

ቱባ ባህሉ ከቱባ እናቶች🙏✅

23/01/2026

The Battle of Adwa on March 1, 1896, saw Emperor Menelik II lead a unified Ethiopian force of around 100,000 troops—armed with modern rifles from France and Russia—against an invading Italian army of about 17,000 under General Oreste Baratieri. Despite being outnumbered, the Italians launched a poorly coordinated attack near the town of Adwa, resulting in a crushing defeat: over 6,000 Italians killed or wounded, thousands captured, and their colonial ambitions shattered.
The victory forced Italy to sign the Treaty of Addis Ababa later that year, recognizing Ethiopia's full sovereignty and marking the only decisive African triumph over a European power during the Scramble for Africa. This preserved Ethiopia's independence until 1936 and became a powerful symbol of resistance, fueling pan-African pride, inspiring anti-colonial leaders like Marcus Garvey, and proving that colonial domination was not inevitable. Adwa remains a cornerstone of Ethiopian national identity and global Black liberation history. 🇪🇹

ዝነኛው አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ከዚህ አለም ተለየ። ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን!😭😭😭
16/01/2026

ዝነኛው አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ከዚህ አለም ተለየ። ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን!😭😭😭

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Culture posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share