Amard Ethiopia

Amard Ethiopia ለህዝብ የመረጃ ቋት ሆኖ የሚያገለግል

 በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ የፈጀው ዘመናዊው እና ውብ ተደርጎ የተገነባው ግዙፉ የአስተዳደር ህንፃ በደመቀ መልኩ  ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ዝግጁ ሆኗል...
06/09/2026



በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ የፈጀው ዘመናዊው እና ውብ ተደርጎ የተገነባው ግዙፉ የአስተዳደር ህንፃ በደመቀ መልኩ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ዝግጁ ሆኗል።

ህንፃው ዘመናዊ የደህንነት ካሜራዎች የተሟሉለትና ዘመናዊ የህንፃ ጥበብ አሟልቶ የተገነባ ባለ 9 ወለል ህንፃ ነው።

የዚህ ህንፃ ግንባታ የጉራጌ ህዝብ የአንድነት፣ የጥንካሬና የልማት አዲስ ምዕራፍ ጅማሮ ማሳያ ነው

ይህ አዲስና ዘመናዊ የአስተዳደር ህንፃ ግንባታ የድንጋይና የኮንክሪት ክምችት ብቻ አይደለም፤ የጉራጌ ህዝብ የማንነት፣ የውበት፣ የትጋትና የታላቅነት መገለጫ አዲስ አሻራ ነው!

የህዝባችን የልማት ተምሳሌትነት፡ የጉራጌ ህዝብ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር በራሱ ጥረትና ላብ ተዓምር መስራት የሚችል፣ "በራሴ እጅ" ባይ ኩሩ ህዝብ ነው። ይህ ህንፃ የዚሁ የማይበገር የስራ ወዳድነት መንፈስ ህያው ምስክር ይሆናል።

ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ ቅርስ፤ ዛሬ የምናስቀምጠው እያንዳንዱ ሳንቲምና የምናፈሰው ጠብታ ላብ ነገ ልጆቻችን በኩራት ቀና ብለው የሚሄዱበትን ታሪክ ይሰራል።

የህንፃው መጠናቀቅ ለዞኑ ማህበረሰብ የሚሰጠውን የመንግስት አገልግሎት በማዘመን የህዝባችንን እንግልት ይቀንሳል፤ ልማትንም ያፋጥናል።

አንድነት ኃይል ነው ከተማው ከገጠሩ፣ በሀገር ውስጥ ያለው በስደት ከሚኖረው ወገኑ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ካልተረባረበ ይህ ህልም እውን አይሆንም።

ሀገር እና ስራ ወዳዱ የጉራጌ ማህበረሰብ ጀምሮ የመጨረስ ምሳሌም መሆኑን ይህ ግዙፍ ህንፃ ምስክር ነው።

በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ  የእምርታ ቀን በማስመልከት   ጨምሮ ሌሎችም በተገኙበት የHLS አበባ እርሻ ልማት ጎብኝተዋል።ስፖርተኞቹም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሀልአምባ ከ...
06/09/2026

በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የእምርታ ቀን በማስመልከት ጨምሮ ሌሎችም በተገኙበት የHLS አበባ እርሻ ልማት ጎብኝተዋል።

ስፖርተኞቹም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሀልአምባ ከተማ ሲደርሱም በህዝቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በሙአይ ታይ ስፖርት ውድድር አሸናፊ የሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒና ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሀመድ መኪ ጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሀል አምባ ከተማ ሲደርሱ በወረዳው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ስፖርተኞች፣ አድናቂዎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ደማቅ አቀባበል እያደረጉላቸው ነው።

ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒ በETFC ሀገሩን ወክሎ በታሪካዊው አድዋ ሙዚየም በተካሄደው የሙይታይ ፍልሚያ የደቡብ ሱዳን ተጋጣሚውን ስካይን በማሸነፍ አስደናቂ ብቃቱን ማሳየቱ ይታወሳል።

በመርካቶ ዱባይ ተራ ከባድ የእሳት አደጋ ተከሰተ፤ የነጋዴዎች ዕድሜ ልክ የለፉበት ንብረት በሰዓታት ውስጥ ወደመ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም - በአዲስ አበባ ከተማ ትልቁ ክፍት የገበያ ማዕ...
06/09/2026

በመርካቶ ዱባይ ተራ ከባድ የእሳት አደጋ ተከሰተ፤ የነጋዴዎች ዕድሜ ልክ የለፉበት ንብረት በሰዓታት ውስጥ ወደመ

ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም - በአዲስ አበባ ከተማ ትልቁ ክፍት የገበያ ማዕከል በሆነው መርካቶ "ዱባይ ተራ" (ሸማ ተራ) በመርካቶ ዱባይ ተራ እሳት አደጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ በድንገት በተቀሰቀሰ ከፍተኛ የእሳት አደጋ በቢሊዮን የሚቆጠር የነጋዴዎች ንብረትና ዕድሜ ልክ የተለፋበት ጥሪት በጥቂት ሰዓታት ውስጥ መውደሙ ታወቀ።

#መርካቶ

ለመስቀል በዓል ተጓዦች መልካም ዜና  | የመስቀል ተጓዦች ከአላስፈላጊ የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪና ብዝበዛ ነፃ በሆነ መልኩ በተተመነላቸው ህጋዊ ታሪፍ ብቻ እንዲስተናገዱ ይደረጋል ተብሏል።የመ...
04/09/2026

ለመስቀል በዓል ተጓዦች መልካም ዜና

| የመስቀል ተጓዦች ከአላስፈላጊ የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪና ብዝበዛ ነፃ በሆነ መልኩ በተተመነላቸው ህጋዊ ታሪፍ ብቻ እንዲስተናገዱ ይደረጋል ተብሏል።

የመስቀል በዓል ተጓዦች ያለምንም እንግልት፣ የትራንስፖርት እጥረትና የመንገድ መጨናነቅ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በድምቀት ማክበር እንዲችሉ የጉራጌ ዞን እና በኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በቅንጅት መስራት መጀመራቸውን አስታወቁ።

በበዓሉ ወቅት የሚኖረውን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ታሳቢ በማድረግ አደጋዎችን ለመከላከል የሁለቱ ዞኖች የቀቤና የወሊሶ እና የሸገር ከተማ የትራፊክ ፖሊሶችና የፀጥታ አካላት በጥምረት ይሰራሉ።

ለልማትም ሆነ ለሌላ ጉዳይ በሚል ሰበብ ከተጓዦች ላይ የሚሰበሰብ ምንም አይነት መዋጮ ወይም ህገወጥ ክፍያ አይኖርም ሲሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።

ተጓዦች በሰላም ገብተው እንዲመለሱ የፀጥታው ዘርፍ ሌት ተቀን ይሰራል ብለዋል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

6ኛው የኬር ኦድ የ15 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መስከረም 10 ቀን 2018 በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ይካሄዳል ።ነሀሴ 26/2018 በዞኑ የስፖርት መነቃቃት ለመፍጠርና ተተኪ አትሌቶች ለማ...
01/09/2026

6ኛው የኬር ኦድ የ15 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መስከረም 10 ቀን 2018 በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ይካሄዳል ።

ነሀሴ 26/2018 በዞኑ የስፖርት መነቃቃት ለመፍጠርና ተተኪ አትሌቶች ለማፍራት እንደሚያግዝ ተገልጿል።

በውድድሩ ዙርያ በአዲስአበባ ከተማ መግለጫ ተሰጥቷል ።

የኬርኦድ ስፖርት ልማት ዋና ስራ አስኪያጅ አትሌት ተሰማ አብሽሮ እንደገለፁት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ለ6ኛ ዙር የሚካሄደው የ15 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መስከረም 10 ቀን 2018 ይካሄዳል ።

ዞኑ ሀገሪቱን የሚያስጠሩ ታላላቅ አትሌቶች የሚፈልቁበት መሆኑን ጠቁመው የኬርኦድ ሩጫ በዞኑ የስፖርት መነቃቃት ለመፍጠርና ተተኪ አትሌቶች ለማፍራት እንደሚያግዝ ገልፀዋል ።

በቅርቡ በሲድኒ ውድድር አሸናፊ የሆኑት ሁለቱ አትሌቶች በኬርኦድ ሩጫ ተሳታፊ እንደነበሩ ተናግረዋል ።

የዊልቸር ውድድርን ጨምሮ ከ20ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍል እንደሚሳተፍ የገለፁት አትሌት ተሰማ ህብረተሰቡ ያለው የስፖርት መነቃቃት እንደሚያድግና እየተዝናና ጤናውን እንደሚጠብቅ አስረድተዋል ።

25 የአትሌቲክስ ክለቦችን የሚወክሉ ሁለት ሺህ አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን ለአሸናፊዎችና ለአሰልጣኞች ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት መዘጋጀቱን ገልፀዋል ።

ኮማንደር አትሌት ሰለሞን ባረጋ በበኩሉ ዞኑ ለአትሌቲክስ ስፖርት ምቹ በመሆኑ በርካታ አትሌቶች መውጣት እንደሚችሉ ገልፆ ታዳጊዎች በውድድሩ ተሳትፎአቸው እያደገ መሆኑን ተናግሯል።

የኬር ኦድ የ15 ኪሎሜትር የጎዳና ሩጫ በሀገሪቱ የውድድር እድልን የሚያሰፋ መሆኑን የገለፀው አትሌት ሰለሞን ሀገሪቱን በታላላቅ የአለም መድረኮች የሚወክሉ አትሌቶች ለማግኘት ያስችላል ብሏል።

የጌታ ወረዳ አስተዳደር ከጔታ ክፍለ ህዝብ በጋራ በመሆን የፍታውራሪ ሳፎደጀን የባህል አዳራሽ የገቢ አሰባሰብና በወረዳው የልማት ስራዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ...
30/08/2026

የጌታ ወረዳ አስተዳደር ከጔታ ክፍለ ህዝብ በጋራ በመሆን የፍታውራሪ ሳፎደጀን የባህል አዳራሽ የገቢ አሰባሰብና በወረዳው የልማት ስራዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የጉንችሬ ጤና ጣቢያ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉየጤና ጣቢያው መገንባት የእናቶችንና ህጻናት ሞት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑም...
29/08/2026

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የጉንችሬ ጤና ጣቢያ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ

የጤና ጣቢያው መገንባት የእናቶችንና ህጻናት ሞት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑም ተመላክቷል።

ጤና ጣቢያው ከ28ሺ በላይ ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን የሆስፒታሎችን ጫና እንደሚቀንስም ተመላክቷል።

የጉራጌ የቅቤ ዕቁብ — ውጆውጆ በጉራጌ ማኅበረሰብ በተለይም በሴቶች መካከል የተለመደ የወተትና የቅቤ ዕቁብ፣ የመረዳጃና የትብብር ባህላዊ ሥርዓት ነው። በአካባቢው እንደሚለያይ ተሳታፊዎቹ በቡ...
23/08/2026

የጉራጌ የቅቤ ዕቁብ — ውጆ

ውጆ በጉራጌ ማኅበረሰብ በተለይም በሴቶች መካከል የተለመደ የወተትና የቅቤ ዕቁብ፣ የመረዳጃና የትብብር ባህላዊ ሥርዓት ነው።

በአካባቢው እንደሚለያይ ተሳታፊዎቹ በቡድን ተደራጅተው በየተራ የወተት ወይም የቅቤ ድርሻ ይሰጣሉ።

ይህም አንዲት እናት በብቻዋ ከምታገኘው የተለየ ሁኔታ፣ የብዙ ተሳታፊዎች ወተት ተሰብስቦ በአንድ ጊዜ በቂ የሆነ ቅቤ፣ ወተት ወይም አይብ እንዲደርሳት የሚያደርግ የጋራ የመረዳጃ ዘዴ ነው።

በዚህ ሥርዓት የተሳታፊዎች ድርሻ በተለመዱ የመስፈሪያ ዘዴዎች ይለያያል።

ውጆ የጉራጌ ሴቶች በጋራ መረዳዳትን፣ ቁጠባን፣ ተሳትፎንና ማኅበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር ባህላዊ እሴት ነው። በተለይ ከመስቀል በዓል ዝግጅት ጋርም ተያይዞ የቅቤ ውጆን መሰብሰብ እንደ እናቶች የዝግጅት ድርሻ ይጠቀሳል።

በአጭሩ፦ ውጆ ቅቤን ብቻ ለመሰብሰብ የተዘጋጀ ዘዴ ሳይሆን፣ “ዛሬ ለአንቺ፣ ነገ ለእኔ” በሚል መንፈስ የሚገለጽ የጉራጌ ሴቶች የጋራ መረዳጃና የቁጠባ ባህል ነው።

22/08/2026

ናቲ ይችላል

እጅግ ያሳዝናል ባለሙያዋ ደርባባዋ እናታችን አርፈዋል ነፍሳቸውን ይማርልንየሀዘን መግለጫ፡ የታዋቂዋ ቲክቶከር የሀና እናት ወ/ሮ ደምበጭ ሰርቆባ በቤታቸው ህይወታቸው አልፎ ተገኘ።በዋሺንግተን ...
22/08/2026

እጅግ ያሳዝናል ባለሙያዋ ደርባባዋ እናታችን አርፈዋል ነፍሳቸውን ይማርልን

የሀዘን መግለጫ፡ የታዋቂዋ ቲክቶከር የሀና እናት ወ/ሮ ደምበጭ ሰርቆባ በቤታቸው ህይወታቸው አልፎ ተገኘ።

በዋሺንግተን ዲሲና ሜሪላንድ አካባቢ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ትልቅ ሀዘንና ድንጋጤ የፈጠረ አሰቃቂ ዜና ተሰምቷል።

ታዋቂዋ የቲክቶክ ባለሙያ የሀና እናት ወ/ሮ ደምበጭ ሰርቆባ ልብ በሚሰብር ሁኔታ በቤታቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ተገኘ።

እንደ ቤተሰብ መረጃ፣ ወ/ሮ ደምበጭ ህይወታቸው ከማለፉ በፊት የነበረውን ምሽት ለሚመጣው ታላቁ የመስቀል በዓል ቤተሰቦቻቸውን ለማስደሰት ቅቤ ሲያነጥሩና የቤታቸውን ድባብ በበዓል ጠረን ሲያውዱ አድረው ነበር።

ነገር ግን በነጋታው ጠዋት በእሳቸው ዘንድ ህጻናት ልጆቻቸውን የሚያስጠኑ ወላጆች ስልክ ሲደውሉ ምላሽ ባለማግኘታቸው ተጨንቀው ለልጃቸው ለሀና ይደውሉላታል።

ሀና በተጨነቀ መንፈስ ወደ እናቷ ቤት ስታመራ፣ እናቷ በቤቱ መግቢያ በር አቅራቢያ መሬት ላይ ወድቀው ነፍሳቸው ከስጋቸው ተለይታ አግኝታቸዋለች።

በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ፖሊስ የሞታቸውን መንስኤ ለማጣራት ከፍተኛ ምርመራ ጀምሯል። ከፕሮፔን ጋዝ ሌክ (Propane Gas) እስከ ሌሎች አደጋዎች ድረስ የሞታቸው ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ሁሉ እየተመረመሩ ይገኛሉ።

የሀዘን ድንኳን ወዳጅ ዘመድ ሀዘኑን እንዲካፈል አርብ እስከ እሁድ ኦገስት 23 በዋሺንግተን ዲሲ የሀዘን ድንኳን ተክሎ ይቆያል።

ማክሰኞ ኦገስት 25 በዲሲ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የጸሎት፣ የፍትሃትና የሽኝት ስነ-ስርዓታቸው ይፈጸማል።

ለቲክቶክሯ ሀናና ለቤተሰቦቿ በሙሉ ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥ እያሰበን፣ ለወ/ሮ ደምበጭ ሰርቆባ ነፍስ በሰላም እንድታርፍ እንመኛለን።

Address

Addis Ababa
1212

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amard Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category