13/07/2026
💔 "አግኝቶ ማጣት ከባድ ነው!" — በአንድ ጀምበር ህይወታቸው የተቀየረው የዳንኤል እና የእህቱ ትዕግስት ልብ የሚነካ ታሪክ 😢
የኢቢኤስ ቲቪ (EBS TV) "ከውበት በላይ" ፕሮግራም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖች ሙሉ ቀን ወጪያቸውን በመሸፈን፣ ልብስ በመግዛት፣ ምሳና እራት በመጋበዝ እንዲሁም መቆሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የሚያደርገው በጎነት በእጅጉ የሚያስመሰግን ነው። 👏
በቅርቡ በፕሮግራሙ ላይ የቀረበው የዳንኤል ፀጋዬ ታሪክ የብዙዎችን ልብ ነክቷል። ዳንኤል ቀደም ሲል የሚያከራያቸው 6 ሞተሮች የነበሩት ቢሆንም፣ በደረሰበት አደጋ ምክንያት ንብረቱን በሙሉ ሸጦ ዛሬ ላይ ሳንቡሳ በመሸጥ ልጆቹን ለማስተዳደር እየታገለ ይገኛል።
ነገር ግን ከዳንኤል ታሪክ በላይ ይበልጥ ልብን የሚሰብረው የእህቱ የትዕግስት ታሪክ ነው! 😭
ትዕግስት ከፕሮግራሙ አቅራቢ ሮቤል ጋር በነበራት ቆይታ በእንባ እየታጠበች የቤተሰቧን መከራ እንዲህ ስትል አካፍላለች፦
"ባለቤቴ ስትሮክ ታሞ ቤት ከተኛ ስድስት ዓመቱ ነው። ድሮ ተሳቢ መኪና፣ ሚኒባስ እና በርካታ ንብረት ነበረን። ነገር ግን ሁሉንም ንብረታችንን ለባለቤቴ ህክምና ሸጠን ጨረስነው። ዛሬ ላይ እኔ ሻይ ሸጬ ለሶስት ልጆቼ እንጀራ ይዤ መግባት ከብዶኛል።
ልጆቼ ድሮ ብዙ ነገር ለምደው ነበር። አንደኛዋ ልጄ የአባቷን ህመም መቋቋም አቅቷት ትምህርቷን አቋረጠች፤ አባቷ አቅብጦ (አሞላቆ) ስላሳደጋት አሁን ያለው ህይወት በእጅጉ ከበዳት። ሁሉም ነገር በአንድ ጊዜ ጎደለባት።
አንዳንድ ጊዜ መኪና ስር ግቢ ግቢ ይለኛል። ድሮ በሀብት ሰዓት ሲያልፉ ሲያገድሙ የእኛ ቤት ቤታቸው የነበሩ ዘመዶቼም ሆኑ ጓደኞቼ፣ አሁን ያለሁበትን ምስኪን ቤት ማንም አያውቀውም..."
ባለቤቷ ግን በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ሆኖ "አይዞሽ ሁሉም ነገር ያልፋል" እያለ ያበረታታታል።
🙌 መልእክት ለኢቢኤስ ቲቪ (EBS TV)፦
ለወንድማችን ለዳንኤል ያደረጋችሁት ድጋፍ በእጅጉ ያኮራል። ነገር ግን የዳንኤል እህት የትዕግስት ታሪክና አሁን ያለችበት መከራ እጅግ በጣም ያሳዝናል። እባካችሁ ትዕግስትን ድጋሚ ጋብዛችሁ ፕሮግራም ስሩላት፤ ደጋግ ሰዎች እንዲያግዟት መንገድ ክፈቱላት።
የእህታችንን ችግርና መከራ ሌሎች ደጋግና ርኅሩኃን ሰዎች እንዲመለከቱትና የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉላት መረጃውን #ሼር (Share) በማድረግ ለሁሉም እናድርሰው!
"ቸርነት ለራስ ነው!" 🙏
#ከውበትበላይ #ትብብር #በጎነት #የኢትዮጵያዊነት
Via፦ ዘሪሁን ተዝናኑ (ከ EBS TV የተወሰደ)