Mykey's Journey

Mykey's Journey Photographer & Storyteller 🇪🇹
• Passionate about people and meaningful Stories • • Passionate about people and all things story•

እህህ ብለን የምንቆጭባቸውን ነገሮች መቋጨት የምንችለው፣ ገና ባልተበረዘው ንጹሕ የሕፃናት አእምሮ ላይ መልካም ዘር መዝራት ስንችል ብቻ ነው። ልጆች የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ፣ የአባቶችን ጽና...
04/09/2026

እህህ ብለን የምንቆጭባቸውን ነገሮች መቋጨት የምንችለው፣ ገና ባልተበረዘው ንጹሕ የሕፃናት አእምሮ ላይ መልካም ዘር መዝራት ስንችል ብቻ ነው። ልጆች የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ፣ የአባቶችን ጽናትና የሰማዕታትን ገድል በውል ተረድተው ሲያድጉ፣ ከራሳቸው ሕይወት መቃናት አልፈው የሚገጥማቸውን ዓለም ዋጅተው ቤተክርስቲያንንም ይጠቅማሉ።

ሐመረ ብርሃን የብራና ሥራ ድርጅት እየሠራችሁት ያለው ሥራ ሁሌም የሚያስገርመኝ እና እግዚአብሔርን የማመሰግንበት ነው፤ በተለይም ደግሞ ላለፉት ክረምቶች ከሠራችኋቸው ሥራዎች አንስቶ አሁን እስከ ተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ ድረስ በሕፃናት ላይ የምትሠሩት ሥራ ለቤተ ክርስቲያን እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ አብዝቼ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። በጣም ነው የኮራሁባችሁ!

The exhibition will be held at Holland Park from Nehase 28 to Meskerem 3.

Hamere Berhan | ሐመረ ብርሃን

These photos and promotional content were created by Mykeys Journey as a small contribution to support Hamere Birhan’s work.

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ነሐሴ ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

Hamere Noah Kidist Kidanemihret Monasteryሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyewነሐሴ ፲ - ፳፻፲፰ ዓ.ም ምሽት 3:43አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ
18/08/2026

Hamere Noah Kidist Kidanemihret Monastery

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ነሐሴ ፲ - ፳፻፲፰ ዓ.ም ምሽት 3:43
አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

11/08/2026

አንድ ጊዜ ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ሲያስተምሩ፣ "መርሳት እግዚአብሔር የሰጠን ጸጋ ነው" ማለታቸውን አስታውሳለሁ። በወቅቱ ንግግራቸው እንግዳ ሆኖብኝ ፤"እንዴት! መርሳትም ጸጋ ሊሆን ይችላል?" በማለት እጅግ ተደንቄ ነበር። ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ግን፣ እውነትም መርሳት ትልቅ ጸጋ ነው።

ከወዳጆቼ ጋር ተሰብስበን ስንጫወት፣ መሃል ላይ ድንገት ሐሳብ ጠልፎኝ ጭልጥ እላለሁ። "ያለብኝን ሁሉ አስቸጋሪ ነገር ረስቼ ነው እንዴ አሁን ከልቤ የምስቀው?" ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ። አንዳንዴ የረሳሁትና አልተፈታም ብዬ የማሰብውንም የትላንትንም ሸክም መልሼ ላስበው ስሞክር፣ አእምሮዬን ይከብደውና "የራሱ ጉዳይ" ብዬ እተወዋለሁ። ነገር ግን፣ ፈጽሞ የማይፈታ የሚመስል፣ መቆሚያ መቀመጫ የሚያሳጣ ጭንቀት ሲበረታብኝ፣ መሸሸጊያዬን አውቀዋለሁ፤ በቀጥታ ወደ ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ።

በአንድ ወቅት የኢንስታግራም ገጼ 'Highlight' ላይ "Emergency" የሚል ማህደር ከፍቼ አንዲት አጭር ቪዲዮ አስቀምጬ ነበር። ነፍሳችን ስትዝል፣ እግዚአብሔር "ብርታት" በተባለ አምቡላንስ ጠልፎ ወደ ቤተክርስቲያን ያመጣንና (First Aid) ይሰጠናል። ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሆስፒታል አይደለችም እንዴ? እጅግ የሚገርመው ደግሞ፣ እዚያ ስንደርስ "መርሳት" የሚባል ማስታገሻ ይሰጠናል፤ ያንን መድኃኒት ከዋጥን በኋላ፣ የተቀረው ውጣ ውረድ ሁሉ በእግዚአብሔር ጊዜና ጥበብ ቀስ በቀስ ሲስተካከል ሰላም ሆነን እንመለከታለን።

ከእነዚህ የነፍስ ድንገተኛ ሆስፒታሎች መካከል፣ ሐመረ ኖኅ እንጦጦ ኪዳነምህረት ገዳም አንዷ ናት። በዚያች ስፍራ ያለችው ሐኪም ደግሞ እጅግ ልዩ ናት፤ ስሟ ራሱ ፈውስ የሆነ፣ ምሕረትን የምታድል "ኪዳነ ምሕረት"!

ወደ ሆስፒታል ሄዳችሁ፣ የምታክማችሁ ሐኪም የገዛ እናታችሁ ብትሆን ምን ዓይነት መረጋጋት እንደሚሰማችሁ አስቡት!

መልካም ጾመ ፍልሰታ

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ነሐሴ ፬ - ፳፻፲፰ ዓ.ም ምሽት 7:54
አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

Sound Source :- TikTok page of Dessie Medhanealem School.

iphone17promax

📍ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ሐምሌ ፳፯ - ፳፻፲፰ ዓ.ም ምሽት 2:37 ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyewሐምሌ ፳፻፲፰ ዓ.ም – August 2026Addis Ababa, Ethi...
03/08/2026

📍ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል

ሐምሌ ፳፯ - ፳፻፲፰ ዓ.ም
ምሽት 2:37

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ሐምሌ ፳፻፲፰ ዓ.ም – August 2026
Addis Ababa, Ethiopia

A Few Frames from Lalibela Jun 07, 2025 ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyewሐምሌ ፳፻፲፰ ዓ.ም – August 2026Addis Ababa, Ethiopia
01/08/2026

A Few Frames from Lalibela
Jun 07, 2025

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ሐምሌ ፳፻፲፰ ዓ.ም – August 2026
Addis Ababa, Ethiopia

በአንድ ወቅት ላሊበላ ሄጄ ያነሳሁትን አንድ ፎቶግራፍ ስመለከትየ«ጤዛ» ትውስታዬ ድንገት ብልጭ አለብኝ። በፎቶው ላይ የሰፈሩት ሰዎች፣ ልክ ከፊልሙ ውስጥ ወጥተው ከሌንስ ፊት የቆሙ ያህል ነበ...
22/07/2026

በአንድ ወቅት ላሊበላ ሄጄ ያነሳሁትን አንድ ፎቶግራፍ ስመለከት
የ«ጤዛ» ትውስታዬ ድንገት ብልጭ አለብኝ። በፎቶው ላይ የሰፈሩት ሰዎች፣ ልክ ከፊልሙ ውስጥ ወጥተው ከሌንስ ፊት የቆሙ ያህል ነበር የተሰማኝ። ያነሳሁትን ምስል ከ«ጤዛ» የትኛው ፍሬም ጋር ይገናኝ ይሆን እያልን ስናመሳስል እና ስንገረም ነበር። ይህች ቅጽበት፣ አንድ የጥበብ ስራ Inspired ያደረገኝ ይህ ነው ብለን ከማሰባችን ውጪ እንዴት ከዕለታዊ ህይወታችን ጋር እንደሚዋሃድ እና ለስራዎቻችን ትልቅ Inspiration እንደሚሆን በተለይም አተያያችን ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ያረጋገጥኩበት አጋጣሚ ነበረች።

📍ላልይበላ , ኢትዮጵያ

ጤዛ» ፊልምን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁበትን ትክክለኛ ቅጽበት አሁን ላይ ሆኜ ባላስታውሰውም፤ በውስጤ ያሳረፈው የተለየ ስሜት ግን ዛሬም ድረስ ትዝ ይለኛል። ከአንድ ወዳጄ ጋር ሆነን (Frame by frame) እያቆምን፣ የምስል ቅንብሩን እና የካሜራ እንቅስቃሴውን ስንተነትን ያሳለፍነው ጊዜ አይረሳኝም። ለእኔ «ጤዛ» (Storytelling) ምን መምሰል እንዳለበት ያሳየኝ ትልቅ የጥበብ ማሳያ ነው።



እውነት ነው፤ የፊልሙ ዋነኛ ጭብጥ የዘመኑን ፖለቲካዊ ምስቅልቅል፣ ስደትን፣ የማንነት ቀውስንና የምሁራንን ፈተና በጥልቀት ማሳየት ነው። እኔ ግን ከዚህ ሁሉ ባሻገር ፊልሙን የምወደው እና ደጋግሜ የማነሳው ለተነገረበት መንገድ፣ በእያንዳንዱ ፍሬም ውስጥ ላለው ስነ-ውበት እና የተፈጥሮ ገጽታ ትክክለኛውን ነገር ተጠቅመው መመልከቴ ነው።

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
አዲስ አበባ,ኢትዮጵያ | Addisababa,Ethiopia
ሐምሌ ፳፻፲፰ ዓ.ም | July 2026

16/07/2026

I recently went back to Piassa for work after a long time.

It felt like I was walking through a different city. The transformation is beautiful, but at the same time, it felt like meeting someone I once knew who had completely changed.

የሆኑ ሰው ሰላም ብዬ የማልፍባቸው መንገዶች ነበሩ 😊

Piassa is where my journey into street photography began. That’s why I remember its old streets and atmosphere so vividly. Seeing how much it has changed brings back a lot of memories.

I like the new look of Piassa, but I’ll always miss and love the old Piassa. It will always have a special place in my heart.

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ሐምሌ ፳፻፲፰ ዓ.ም - July 2026
Addis Ababa, Ethiopia

St. Michael Church, CMC Limited Edition Prints Available - 60x40 © Mikiyas Liyew Shot on iphone 17 pro max -    BTS Vide...
01/06/2026

St. Michael Church, CMC
Limited Edition Prints Available - 60x40
© Mikiyas Liyew

Shot on iphone 17 pro max -


BTS Videographer-

K + H 🤍
28/05/2026

K + H 🤍



‘’ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ : ዲያብሎስን አሰረው : አዳምን ነጻ አወጣው : ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ’’📍 በቦሌ ደብረሳሌም መድኃኔዓለም፤ መጥምቁ ...
12/04/2026

‘’ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ : ዲያብሎስን አሰረው : አዳምን ነጻ አወጣው : ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ’’

📍 በቦሌ ደብረሳሌም መድኃኔዓለም፤ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ ካቴድራል

ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew
ሚያዚያ ፳፻፲፰ ዓ.ም - April 2026
Addis Ababa, Ethiopia

Address

Addis Ababa

Telephone

+251916565758

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mykey's Journey posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mykey's Journey:

Shortcuts

Share

Category