Sisay Terefe

Sisay Terefe " ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።"
(የዮሐንስ ወንጌል 14:6)

28/05/2025

ኢ አቢኑ አቴቲ 🙏

ሰባኪው አዲስ ተጋቢ ሙሽሮችን ወደመድረክ ጠርቶ የጋብቻ ስስነርዓታቸውን እያስፈፀመ እያለ "ይህንን ጋብቻ የሚቃወም ካለ ወደ መድረክ ይምጣ አለ!"በዚህ ጊዜ አንድ የ3 ዓመት ህፃን ልጅ ያቀፈች...
02/07/2024

ሰባኪው አዲስ ተጋቢ ሙሽሮችን ወደመድረክ ጠርቶ የጋብቻ ስስነርዓታቸውን እያስፈፀመ እያለ "ይህንን ጋብቻ የሚቃወም ካለ ወደ መድረክ ይምጣ አለ!"

በዚህ ጊዜ አንድ የ3 ዓመት ህፃን ልጅ ያቀፈች እርጉዝ ሴት ከአዳራሹ መጨረሻ ወንበር ተነስታ ወደፊት ማዝገም ጀመረች።

ሙሽሪትም ያች ህፃን የያዘች እርጉዝ ሴት ወደፊት ስትመጣ ስታይ ሙሽራውን ወራዳ ልክስክስ በሚስትህ ላይ ነው ልታገባኝ የነበረው አለችና በጥፊ ሙታው በጎን ባለው በር ወጥታ ሮጠች።
ታዳሚውም አብዛኛው እያጉረመረመ በሚቀርበው በር እየወጣ ሄደ።

ያች ህፃን የያዘች ሴት ፊት ወንበር ላይ ስትደርስ ከአንዱ ወንበር ላይ ቁጭ አለች። ሰባኪውም ግራ ተጋብቶ "ምነው ችግር አለ እህቴ?" አላት።

ያች ሴትዮም "ምንም ችግር የለም ጌታዬ! ጆሮዬ የመስማት ችግር ስላለበት በደንብ እንዲሰማኝ ከፊት ልቀመጥ ብዬ ነው!" አለችው።

የመልዕክቱ አንኳር ጭብጥ፡-
የነገሮችን ፍፃሜ ሳናይ (ሳንሰማ) ቸኩለን በግምት አንደምድም (አንወስን) የሚል ነው!

 በእንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጎድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ በራሷ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች በጣምም መጮህ ጀመረች ባለቤቱም አህያዋን ለማውጣት ብር...
23/06/2024


በእንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጎድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ በራሷ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች በጣምም መጮህ ጀመረች ባለቤቱም አህያዋን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለተ አልቻለም፡፡

አህያዋም ብዙ ያገለገለችና ያረጀች ስለሆነች እንዲሁም ሌሎች እንስሳትም ወደ ጉድጓዱ እንዳይገብበት በማሰብ ጉድጓዱ ውስጥ ሊቀብራት ወሰነ፡፡

ጎረቤቶቹንም አስተባብሮ ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ አህያዋ ይህን ስትመለከት እየቀበራት መሆኑነ ተረዳችና በሰቀቀን አለቀሰች፡፡ይሁን እንጂ አህያዋ አፈር ሲደፋባት አንድ ነገር ታደርግ ጀመር፡፡ አፈሩ በተደፋባት ቁጥር አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ጀመር፡፡በተደጋጋሚ ከሚደፋባት አፈር ላይ መቆምም ትጀምራለች፡፡

በሂደት ውስጥ በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች ከፍ እያለች በመጨረሻም ጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መውጣት ቻለች፡፡

በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ሰዎች በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡
ሰው ያስባል እግዚአብሔር ይፈፅማል!!!!!!!

ከእግዚአብሔር አይምጣ እንጂ ከሰው የመጣ እሱ ይመልሰዋል !!!!!!
#ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ

 ህፃን አሜንን እስከ ወዲያኛው አጥተናታል  😭😭😭እንድትድንልን ሁላችንም ጉጉትና ናፍቆት አድሮብን ነበር። የመዳኗን ዜና ለመስማት ጆሮአችን ጓጉቶም ነበር 😭ቢሆንም እኛ እንዳሰብነው ሊሆን አል...
17/06/2024


ህፃን አሜንን እስከ ወዲያኛው አጥተናታል 😭😭😭

እንድትድንልን ሁላችንም ጉጉትና ናፍቆት አድሮብን ነበር።
የመዳኗን ዜና ለመስማት ጆሮአችን ጓጉቶም ነበር 😭

ቢሆንም እኛ እንዳሰብነው ሊሆን አልቻለም።

አሜን ድጋሚ ወደ ማትመለስበት ሄዳለች አምልጣናለች።

ህፃን አሜን ባለፈው ሀሙስ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ሕንድ ሀገር ደርሳ በዕለተ አርብ ነበር ሕክምና ማድረግ የጀመረችው።

በወቅቱ በነበረባት አጣዳፊ የልብ ችግር ምክንያት #የፅኑ ህሙማን ክፍል በመግባት ሕክምናው ተጀምሮላት ነበር።

ለኦፕሬሽን ቅድመ ዝግጅት
የልቧ ህክምና ብሎም በተያያዥነት በሳንባ ላይ የነበረ ችግር እና በእጅና በእግር ላይ የነበረ እብጠት ለማስተካከል ከፍተኛ ርብርብ ቢደረግም በሕንድ ሃገር ባለው ሕክምና ከሶስት ቀናት በላይ በህይወት መቆየት አልቻለችም።

ስስታችን አሜን በቃኝ ብላ እጅ ሰጥታለች። 😭😭

ብዙ ልፋት አድካሚ ውጣ ውረዶች ከሰው ሊደረግ የሚገባ ሁሉ ተደርጎ ሊሳካ አልቻለም።

እንግዲህ እግዚአብሔር ያለው ሆኗል ። አሜንም ለዘላለም አሸልባለች ።

አንዳች የሚሰዋ ነገር ቢኖር ሰውተንም እንድትድንልን ምኞታችን ነበር 😭😭

ወላጅ አባት እና እናት
ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ሁላችሁ የአሜንን መዳን የናፈቃችሁ ሁሉ በፀሎት በዱኣ ስትተጉ የነበራችሁ ኢትዮጵያዊን በአጠቃላይ መፅናናት ይሁንልን 😭😭

 አይጧ የግድግዳውን ቀዳዳ በመጠቀም የቤቱባለቤት በታሸገ ካርቶን እቃ ይዞ ሲገባ ትመለከታለች፡፡አይጧ “ዛሬ ደግሞ ምን አይነት ምግብ ይዞ መጣ!?” ብላተደስታለች፤ ነገር ግን ሰውዬው ለባለቤቱ...
08/06/2024


አይጧ የግድግዳውን ቀዳዳ በመጠቀም የቤቱ
ባለቤት በታሸገ ካርቶን እቃ ይዞ ሲገባ ትመለከታለች፡፡
አይጧ “ዛሬ ደግሞ ምን አይነት ምግብ ይዞ መጣ!?” ብላ
ተደስታለች፤ ነገር ግን ሰውዬው ለባለቤቱ ሊያሳያት
የታሸገውን ካርቶን ሲከፍተው ወጥመድ ነው፡፡ አይጧ
ደነገጠች፤ ወዲያውኑ ወደ እርሻው ተመለሰችና ጮክ ብላ
“በዚህ እርሻ ውስጥ የምትገኙ እንስሳቶች ሆይ! የአይጥ
ወጥመድ እየተጠመደላችሁ ነው፤ ወጥመድ! መጥመድ!!”
በማለት ትናዘዛለች፡፡
ይህን ድምፅ በንቃት የሰማችው ዶሮ ካጎነበሰችበት ቀና
በማለት “አይጦ ላንቺ ምን ያህል እንደሚያስጨንቅሽ
ይገባኛል፤ ነገር ግን እኔን አይመለከትም እዛው ጣጣሽን
ቻይ” ትላታለች፡፡ መከራ የበዛበት አይጥ የቤቱ በግ
ወደሚገኝበት ቦታ ትሄድና የቤቱ ባለቤት የአይጥ ወጥመድ
ገዝቶ እንደመጣ ትነግረዋለች፡፡
በጉ በንቀት አይን እየተመለከታት “ይቅርታ አድርጊልኝ
አይጦ ምንም ልረዳሽ አልችልም” ይላታል፡፡ እቤት ውስጥ
ከሚኖሩት እንስሳቶች የቀረው አንድ በሬ ነበር፤ አይጦ
እርሱንም እርዳታ ለመጠየቅ ወዳለበት ትሄዳለች፡፡
“ወጥመድ ወጥመድ የአይጥ ወጥመድ ይዘው መጡ”
ትለዋለች፤ በሬው ምንም ሳይመስለው እየሳቀ “አይጦ
ምን ነክቶሽ ነው! እኔ እንደሆን ቆዳዬን እንኳ አይጎዳውም፤
ጣጣሽን ቻይ” በማለት ያባርራታል፡፡
አይጧ በጣም ተበሳጭታ አንገቷን አቀርቅራ የገበሬውን
ወጥመድ ብቻዋን ልትጋፈጥ ወደ ቤቷ ትመለሳለች፡፡
በዛው ቀን ምሽት ሰው ሁሉ በተኛበት ወጥመዱ ከፍተኛ
ድምፅ አሰማ፡፡
የገበሬው ሚስት አስቸጋሪዋ አይጥ ተያዘችልኝ በሚል
ሀሳብ ወጥመዱ ወዳለበት ስፍራ ታቀናለች፡፡ ጨለማ
ነበርና ምን እንደተያዘም ሳታውቅ የአይጧ ጭራ መስሏት
በወጥመዱ የተያዘውን አደገኛ እባብ አፉን ነበር
የያዘችው፡፡ እባቡ ነከሳት ነደፋትም፡፡ ገበሬው በፍጥነት
ወደ ሆስፒታል ይወስዳታል፤ ከታከመች በሗላ ወደ ቤት
ይመልሳታል ነገር ግን አደገኛ ራስ ምታቱ አለቀቃትም፡፡
ዶሮ ደግሞ ለእንደዚህ አይነት ራስ ምታት ፍቱን መድሃኒት
መሆኑ የምናውቀው ጉዳይ ነውና ገበሬው ቤት ውስጥ
የምትገኘውን ዶሮ “ለመድሀኒትነት” አረዳት፡፡ ነገር ግን
የገበሬው ሚስት ከህመሟ ልታገግም አልቻለችም፤
ህመሟ እየበረታ ሄደ፡፡ የአካባቢው ሰው ሊጠይቃት ይጎርፍ
ጀመር፤ ገበሬው እነዚህን እንግዳ ያስተናግድበት ዘንድ
በጉን አረደው፡፡ የገበሬው ሚስት ህመሟ በርትቶ ሆስፒታል
ስትታከም ከቆየች በሗላ ትሞታለች፡፡ ታዲያ ህዝብ ሁሉ
ሊያስቀብራት መጣ፤ አስቀበራትም፡፡ ከቀብር ሲመለሱ
ገበሬው ለቀባሪዎች በሬውን አረደው፡፡
አይጧ ይህንን ድርጊት በሙሉ በዛቺ ግድግዳ ቀዳዳ እንደ
ፊልም ትመለከት ነበር፡፡ በድርጊቱ በጣም አዘነች፡፡
ይህ አጭር ታሪክ ትልቅ ትምህር አለው፡፡ ለሌላ ጊዜ አንድ
ሰው ችግር ላይ ነው ሲባል ሰምተን የኔ ችግር አይደለም
በምንልበት ጊዜ አስታውሱ አንዱ ተጨቆነ ማለት
ሁላችንም መጨቆናችን አይቀርም፡፡
ሁላችንም ህይወት በምትባል ጉዞ ላይ ተሳታፊዎች ነን፡፡
ታዲያ መንገዱ ላይ ዞር ዞር ብሎ በመቃኘት እርስ በርስ
ልንረዳዳ ይገባል፤ አይመለከተንም ብለን ብናስብ እርዳታ
ከመስጠት ወደ ሗላ ማለት የለብንም፡፡
ከሁሉም በላይ አዛኙን ፈጣሪም እናስብ ለሰው ልጅ
ስታዝን ያዝንልሀል ስትረዳ ይረዳሀል ፈጣሪ በእዝነቱ
ይመልከተን
ለነዚህ ሰዎች ይህን መልዕክት እናስተላልፍ;
በህይወታችን ለረዱን በሙሉ
እርዳታቸው እንደጠቀመን ይወቁልን
እዚህ አለም ላይ አጥብቀህ ልትይዘው የሚገባ ምርጥ
ባህሪ-“ቅን አስተሳሰብ” ነውና፡፡
ይህ ጠቃሚ መልዕክት እርሶ ዘንድ እንዲቀር አይፍቀዱ!!!
#ሼር በማድረግ ሌሎችም እንዲማሩበት ያድርጉ

 ??ራስህን "ነቢይ ነኝ" ብለህ ከመሾምህ በፊት ነቢዮ ኢሳይያስ እኛ አሁን እየታነጽንበት ላለው ወንጌል በመጋዝ ሁለት ቦታ ተሰንጥቆ መሞቱን ታውቃለህ!?ራስህን "ነቢይ ነኝ" ብለህ ከመሾምህ ...
07/06/2024

??

ራስህን "ነቢይ ነኝ" ብለህ ከመሾምህ በፊት ነቢዮ ኢሳይያስ እኛ አሁን እየታነጽንበት ላለው ወንጌል በመጋዝ ሁለት ቦታ ተሰንጥቆ መሞቱን ታውቃለህ!?

ራስህን "ነቢይ ነኝ" ብለህ ከመሾምህ በፊት ለዚህ የወንጌል እውነት ሐዋሪያው ዮሐንስ በሚፈላ ዘይት በርሜል ውስጥ ተዘፍዝፎ መሞቱን: እንዲሁም ሐዋሪያው ጴጥሮስ "እንደ ጌታዬ በቁሜ አልሰቀልም" ብሎ ወደታች ተዘቅዝቆ በመሰቀል መሞቱን ታውቃለህ!?

የጥንቱ ሐዋሪያት ዘመናዊ ውድ መኪና የመንዳት: ዘመናዊ ቪላ የመስራት: የቱርክ ሱፍና የፈረንሳይ ሽቶ የመቀባት አባዜና ጥማት አልነበረባቸውም::

የጥንቱ ሐዋሪያት በጥቁር ገበያ በተጭበረበረ ዶላር: ዮሮና ፓውንድ: ከድሆች መቀነት በተዘረፈ ብር ቢሊየነር የመሆን ሕልም አልነበራቸውም::

የጥንቱ ሐዋሪያት ዘይት: ውኃና ጨርቃ ጨርቅ ሽጠው ባለጠጋ የመሆን ሕልም አልነበራቸውም:: ትልልቅ አዳራሾች አልገነቡም:: የተሸቃቀጠ ወንጌል ሰብከው ዝና አላካበቱም:: ሐሰትን ከእውነት ቀላቅለው እንደ ሸቀጥ ለገበያ አላቀረቡም!!

ዛሬ ዛሬ ነቢይ: ሐዋሪያ: ቢሾፕ እያሉ የተለያዩ ስሞችን ለራሳቸው የሚሰጡ ሰዎች የስሙን ዋጋና ክብር አላወቁም:: ስሙን የያዙ የጥንቱ እውነተኛ አገልጋዮች ስሙ የሚጠይቀውን እውነተኛ የሕይወት መስዋዕትነት እንደከፈሉ እነዚህ መክፈል አይፈልጉም!!

ዛሬ ማንም ስሙን የያዘው ሰው ስሙ ለሚጠይቀው እውነት ኑሮና ሕይወት መከራ መቀበል ዋጋ መክፈል አይፈልግም::
የገዛ ምኞታቸው አገልጋይ እንደመሆናቸው መጠን እግዚአብሔርን ማገልገል ለሚያመጣው መስዋዕትነት ዝግጁ አይደሉም:: ፈቃደኛም አይሆኑም!!

የጥንቱ ነቢያትና ሐዋርያት ዓለማና ግብ ለወንጌሉ እውነት መጋደልና ነፍሳቸውን መስጠት ነው:: የዘወትር ትጋታቸው ነፍሳትን ለጌታ መማረክ፣ የክርስቶስ ክብር፣ ደቀ መዝሙራዊ ሕይወትና ተግባራዊ ክርስትና ነው!!

አንድ አይነ ስውር ህጻን ልጅ "አይነ ስውር ነኝ እባካችሁን እርዱኝ" የሚል ጽሁፍ ይዞ መንገደኛውን ይማፀናልከፊት ለፊቱ ባስቀመጠው የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘንቢል ውስጥ ትንሽ ሳንቲሞች ተቀምጠዋ...
07/06/2024

አንድ አይነ ስውር ህጻን ልጅ "አይነ ስውር ነኝ እባካችሁን እርዱኝ" የሚል ጽሁፍ ይዞ መንገደኛውን ይማፀናል

ከፊት ለፊቱ ባስቀመጠው የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘንቢል ውስጥ ትንሽ ሳንቲሞች ተቀምጠዋል

በዚያ መንገድ ሲያልፍ የነበረ አንድ ሰው ሳንቲም ከመፀወተው በኃላ እይነ ስውሩን አስፈቅዶት ጽሁፉ የተጻፈበትን ወረቀት ገልብጦት ከጀርባው ሌላ ጽሁፍ ጻፈበት

ወዲያውኑ እግረኛው ሁሉ ዘንቢሉ ውስጥ ሳንቲም እየወረወረ ሞላው

የዚያኑ ቀን ረፋድ ላይ ሰውዬው ወደ አይነስውሩ ልጅ ባቀናበት ወቅት "ምን ብለህ ነው የጻፍከው? ከዚያን ሰአት ጀምሮ እኮ ዘንቢሌ በሳንትም ተሞላ" ሲል ይጠይቀዋል

"ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው: እኔ ግን ላየው አልችልም" የሚል ነው የጻፍኩልህ ብሎ መለሰለት

👇🏾

ሁለቱም ጽሁፎች የልጁን አይነስውርነት ይገልጻሉ ነገር ግን ሰዎች ሲያነቡት የኮረኮራቸው የዛሬን ቀን ውብነት ለማየት መታደላቸው ሲረዱ ነው

ዛሬን ማየትህ እድለኛ ነህ !!❤️🙌🏼

07/06/2024

እኔ ክርስቲያንን ከእግዚአብሔር በላይ መውደድ አልችልሞ 😥 እርሱ የወደደውን አደረገ 😥😥

😭ብዙ ኢትዮጵያውያን በእርዳታ የተባበሩት ና ብዙ ሚሊዮን ብር ለህክምና የተዋጣላችው እንዲሁም ህክምናቸውን እያደረጉ የነበሩት እኚህ እናታ ሁላችንም ወደ ማንቀርበት ዓለም ሄደዋል::እማማ 😭 ነ...
07/06/2024

😭

ብዙ ኢትዮጵያውያን በእርዳታ የተባበሩት ና ብዙ ሚሊዮን ብር ለህክምና የተዋጣላችው

እንዲሁም ህክምናቸውን እያደረጉ የነበሩት

እኚህ እናታ ሁላችንም ወደ ማንቀርበት ዓለም ሄደዋል::

እማማ 😭

ነብስ ይማር

የዘማሪት ዘሪቱ ከበደ የመጀመሪያ ልጅ ህይወት አለፈ😥የዘሪቱ ከበደ የመጀመሪያ ልጅ ክርስቲያን ላቃቸው ለህክምና ወደ ሆስፒታል ገብቶ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ከሰአት አመሻሽ ላይ ህይወቱ ማለፉ ተሰ...
05/06/2024

የዘማሪት ዘሪቱ ከበደ የመጀመሪያ ልጅ ህይወት አለፈ😥

የዘሪቱ ከበደ የመጀመሪያ ልጅ ክርስቲያን ላቃቸው ለህክምና ወደ ሆስፒታል ገብቶ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ከሰአት አመሻሽ ላይ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

ለዘማሪት ዘሪቱ ከበደ እና ለመላው ቤተሰቦቿ መፅናናትን እንመኛልን ::
ቅዱሳን በዚህ ከባድ ጊዜ እሷን እና ቤተሰቧን በፀሎታችን እንድናስብ እና አብረናቸው እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን 😭❤️🙏

Address

Halaba
Alaba K'ulito

Telephone

+251909971439

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sisay Terefe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category