Eqbel pics

Eqbel pics እኔ ፎቶ ማንሳት በጣም እወዳለሁ በቃ��እውነት!!!

በነገራችን ላይ የዛሬው  #ንጋታችን እና  #ምሽታችን ይኽን ይመስል ነበር😍
21/10/2022

በነገራችን ላይ የዛሬው #ንጋታችን እና #ምሽታችን
ይኽን ይመስል ነበር😍

የማለዳ ውበት❤ፀሀይ፦ አሁን መምጫዬ ደርሷል ልቀቂ ቦታጨረቃ፦ቆይ ትንሽ ትንሽ...(በዚች ሚጢጢ አቅሟ☺)
21/10/2022

የማለዳ ውበት❤
ፀሀይ፦ አሁን መምጫዬ ደርሷል ልቀቂ ቦታ
ጨረቃ፦ቆይ ትንሽ ትንሽ...
(በዚች ሚጢጢ አቅሟ☺)

❤
09/10/2022

12/09/2022

+ አንገት ተቆርሶ የተከበረ ልደት +

በመጽሐፍ ቅዱስ ልደት ያከበሩት የግብፁ ንጉሥ ፈርዖንና የይሁዳው ገዢ ሄሮድስ ናቸው:: እርግጥ ነው ልደትን ማክበር በአሕዛብ ነገሥታት ቢዘወተርም የሚነቀፍ ነገር አይደለም:: ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስም የሚጀምረው የሰማይና የምድርን ልደት በሚተርከው "ኦሪት ዘልደት" ነው::
"እግዚአብሔር አምላክ፥ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ፥ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው" (ዘፍ. 2:4)

ትልቅዋ አፈር መሬት በሰባት ዓመት ማረፍዋን አይተን እኛም በሰባት ቀን እንደምናርፍ የምድርን ልደት መተረክ አይተን ልደታችንን ብናከብር ክፋት የለውም:: (Microcosm /ንዑስ ዓለም/ እንዲል ቴዎሎጂ) የመድኃኔዓለምን ልደት ከፍ አድርገን የብዙ ቅዱሳንን ልደት ደግሞ እንዲሁ በቤተ ክርስቲያን ማክበራችን ልደት አንዱ እግዚአብሔርን ማመስገኛ ቀን ስለሆነ ነው:: ከኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት አንዳንዶቹ ደግሞ የልደቴ ቀን ብለው የሚያከብሩት ለዳግም ልደት ክርስትና የተነሡበትን ቀን ነው::

በዛሬው ዕለት ሔሮድስ ያከበረው ልደት ግን እጅግ የተረገመው ልደት ነበር:: ተጋባዦቹ የንጹሕን ሰው ደም የጠጡበት ልደት ሔሮድያዳ እንደ ታላቂቱ ባቢሎን "በሰማዕቱ ደም ሰክራ" የዋለችበት የልደት ግብዣ ቀን ነበር::

በዚህ ልደት የተቆረሰው ኬክ አይደለም:: በዚህ ልደት እፍ ተብሎ የጠፋው ሻማ አይደለም:: በሰይፍ ተቆርሶ በሰሃን የቀረበው ከሴት ከተወለዱት ሁሉ የሚመስለው የሌለ ቅዱስ ሰው አንገት ነበር:: በሻማ ፈንታ የጠፋው ክርስቶስ "እርሱ የሚያበራ መብራት ነበር እናንተም ጥቂት ዘመን በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ" ብሎ የተናገረለት መብራት ቅዱስ ዮሐንስ ነበር:: እርግጥ ነው በልደት ሰበብ ብዙ ኃጢአት ይሠራል:: በሔሮድስ ልደት ግን የተሠራው ግፍ ዓለምን የሚያንቀጠቅጥ ግፍ ነው::

ሔሮድስ የገደለው ማንን ነው? ነቢይን ነውን? እውነት እላችኁዋለሁ ከነቢይ የሚበልጠውን ነው:: ከሴት ከተወለዱት ሁሉ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያለ አልተነሣም:: አንድን ሰው ብቻ የገደለ መስሎታል::
እርሱ የገደለው ዓሥር ሰው ነው:: ከነቢያት የመጨረሻውን ነቢይ ከሐዋርያት የመጀመሪያውን ሐዋርያ ገደለ:: ለብዙዎች የንስሓ ሰባኪያቸውን ለብዙዎች አጥማቂያቸውን ገደለ:: መለኮትን ያጠመቀውን ወደር ያልተገኘለትን አጥማቂ ገደለ::

አንገቱ ተቀልቶ ለሚያይ ወንጀለኛ ይመስለዋል እርሱ ግን ብቻውን በበረሓ የኖረ ባሕታዊ ነበረ:: ጮማ ያቆረጠ ጠጅ ባፉ ያልዞረ በልብስ ያላጌጠ ሰውነቱን በኃጢአት ያላሳደፈው መናኝ በዚያች በተረገመች የልደት ቀን አንገቱ በሰሐን ቀረበ::

የሐዲስ ኪዳኑ ናቡቴ ሕገ እግዚአብሔርን ርስት አድርጎ በኤልዛቤዋ ሔሮድያዳ ምክር በሔሮድስ ትእዛዝ ተገደለ:: የሐዲስ ኪዳኑ ኦርዮ የሔሮድስን አመንዝራነት ለመደበቅ በግፍ ተገደለ:: ዳዊት ኦርዮን ባስገደለ ጊዜ በእጅ አዙር አደረገው እንጂ በፊት ለፊት አላደረገውም:: በኁዋላም ዕድሜውን ሙሉ አልቅሶአል:: ሔሮድስ ግን ኀዘኑ የለበጣ ነበረ::

ቅዱስ ያሬድ “ቢበላው ይሻላል” ባለለት መሐላው አሳብቦ ታላቁን ነቢይ አንገቱን ቀላው:: ቅዱስ ኤፍሬም "አዳምን በጎኑ አጥንት በሔዋን ድል የነሣው ሰይጣን ሔሮድስን በጎኑ አጥንት በሔሮድያዳ ድል አደረገውና ቅዱሱን ዮሐንስ ገደለው" ይላል::

በቤተ መንግሥቱ መካከል የዮሐንስ አንገት እንደ ምግብ በሳሕን ይዘሽ ለእናትሽ ያቀበልሽ አንቺ ሴት ምንኛ ብትረገሚ ይሆን:: በምድረ በዳ የጮኸ አፉን ክፉ ያላዩ ዓይኖቹን ምላጭ ያልነካው ጠጉሩን በሳሕን ላይ ይዘሽ ስትሔጂ ምን ተሰምቶሽ ይሆን?

መጥምቁን በመግደል ኃጢአትን መሸፈን አይቻልም:: ቅዱስ ኤፍሬም "የዮሐንስ ራስ የገዳዮቹን ኃጢአት አጉልቶ የሚያጋልጥ መብራት ነበረ:: ዮሐንስ በቃሉ ከተናገረው በላይ በሞቱ ኃጢአታቸውን ከፍ አድርጎ አሳየ" ይላል::

ክፋታቸውን ለመደበቅ እንደ ሔሮድስ ንጹሐንን የሚያስሩ : የልባቸውን ሠርተው በሞተ ጊዜ የውሸት የኀዘን መግለጫ የሚሠጡ ሁሉ መጨረሻቸው ዕብደት ነው:: ከማንም በላይ የሟች ደም የሚጮኸው በገዳይ ሕሊና ውስጥ ነው::
ሔሮድስ ዮሐንስ ገድሎ ተረበሸ:: አይሁድ ጌታ ለመነሣቱ ብዙ ምስክር ቀርቦላቸው ያላመኑትን እርሱ ግን ያለ ማስረጃ "መጥምቁ ዮሐንስ ተነሥቶአል" ብሎ መዘላበድ ጀመረ::

ዮሐንስን በሰይፍ መቅላትና ስብከቱን ዝም ማስባል የሚቻል መስሎት ነበር:: ዮሐንስ ግን ሰማዕት ሲሆን በገዳዩ ሔሮድስ ልብ ውስጥ ስብከት ጀመረ:: እኛ ቆመን ስንለፈልፍ አንሰማም ዮሐንስ ግን ሞቶ ገዳዩን አስጨነቀ:: ነቢዩ ኤርምያስን ጉድጉዋድ የጣለው ንጉሥ ጳስኮርን :- ከእንግዲህ ስምህ ማጎርሚሳቢብ ነው ለራስህና ለወዳጆችህ ፍርሃት አደርግሃለሁ እንዳለው የመጥምቁ ገዳዮች ገድለን አረፍን ሲሉ ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ፍርሃት ሆኑ:: ንጹሐንን መግደልና በሞታቸው መሳቅ ይቻላል:: የደማቸውን ድምፅ ግን ከራስ ከሕሊና ማጥፋት አይቻልም:: አሁንም እንላለን ከሟች በላይ ገዳይ ያሳዝናል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 2 2013 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ] ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

2015🌻🌻🌻
11/09/2022

2015
🌻🌻🌻

የ2014 የመጨረሻዋ📷
10/09/2022

የ2014 የመጨረሻዋ📷

 #ጷጉሜ 3ቅዱስ_ሩፋኤል❤የአመት ሰው ይበለን🙏
08/09/2022

#ጷጉሜ 3
ቅዱስ_ሩፋኤል❤
የአመት ሰው ይበለን🙏

05/09/2022

  ከሁሉም በላይ ነህና...😢🙏
28/08/2022

ከሁሉም በላይ ነህና...😢🙏

Address

Bahir Dar

Telephone

+251910298790

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eqbel pics posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Eqbel pics:

Share