24/02/2026
ወዳጆቼ! ይህ ፎቶ ትናንት ጀምሮ ማህበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቆታል፤ አይታችሁታል ብዬ አስባለሁ። 🤗
ታሪኩ እንዲህ ነው፦
ወንድማችን መኖሪያውን ደቡብ አፍሪካ አድርጎ ለብዙ ዓመታት ኖሯል። 'ሰው ብቻውን መሆን የለበትም' ብሎ ትዳር ሊመሰረት ሲያስብ አንዲት ልጅ ተዋወቀ። በፍቅር ተስማሙ።
የወደፊት የልጆቹን እናት ለማምጣትም 1.2 ሚሊዮን ብር ከፍሎ ደቡብ አፍሪካ አስገባት። ኤርፖርት ድረስ አበባ ይዞ በጉጉት ጠበቃት። እሷም በሰላም ደረሰች፤ ወንድማችንም የናፈቃት የትዳር አጋሩን በማግኘቱ እጅግ ደስ አለው።
ግን... ነገሩ መልኩን ቀየረ! 🙄
ወዳጃችን ሰላም ሊላትና አበባ ሊሰጣት ሲቀርብ፤ እሷ ግን ግራ ገባት። 'እርስዎ ማን ነዎት?' ብላ ጠየቀችው። 'የኔ ውድ እኔ እኮ ባልሽ ነኝ!' ቢላት፤ 'እናቴ ድረሽልኝ!' ብላ መጮህና መሸሽ ጀመረች። 😳
ወዳጆቼ እንቀጥል ወይስ ይበቃል? . . ."
part2 በቅርብ ቀን