09/09/2026
ይነበብ ,ይነበብ
(ምንጭ ከ ስለ እናት ገፅ ላይ የተወሰደ) «በጣም አሳዛኝ ታሪክ ስለሆነ ልብ ብለው ያንብቡት»
ታሪኩ እውነተኛ ይሁን እንጂ የፊልም ባለሞያዎች ወደ ፊልም ቀይረው
እንባ በሚያራጭ መልኩ ሰርተውታል።
እኔም የታሪኩ ጭብጥ ስለ መሰጠኝና እናንተም እንደምትወዱት
ስላመንኩ ታሪኩን አጠር አጠር አርጌ አንዳንድ የራሴንም ሀሳብ
አክዬበት ላካፍላችሁ ወደድኩ።
ነገሩ እንዲህ ነው፦በሊባኖስ ሀገር ከሚገኘው በአንድ ትምህርት ቤት
ውስጥ መምህሯ ክፍል/ክላስ/ ገብታ ስታስተምር ከተማሪዎቹ አንዱ
ይነሳና "መምህር እቃ ተሰርቂያለሁ" ይላል።
መምህሯም በስርቆቱ እጅግ ተበሳጭታ የተሰረቀው እቃ ምን እንደሆነ
ካጣራች ቡኀላ ተማሪዎች ለፍተሻ እንዲዘጋጁ አደረገችና ፍተሻዋን
ቀጠለች።
፡
በፍተሻው ሰዓት ታዲያ አንዲት እድሜዋ 10 ኣመት እማይሞላ ተማሪ
ተራዋ ደርሶ ቦርሳዋን እንድትከፍት ስትጠየቅ አሻፈረኝ ትላለች።
፡
መምህሯም በንዴት ጡፋ ምራቋን ፊቷ ላይ ተፍታባት አንቺ ሌባ ኣንቺ ነሽ
የሰረቅሽው ፓሊስ ነው ምጠራልሽ እያለች ስትጮህ በአጋጣሚ በክፍሉ
በር ሲያልፋ የሰሙት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር(ዳይሬክተር) ከተፍ
ይላሉ።
:
ይህን ጊዜ ልጅቷ የባሰ ድንጋጤና ፍርሃት እያንቀጠቀጣት እባክሽ ይቅር
በይኝ እኔ ሌባ አደለሁም ከፈለግሽ እንኪ ፈትሽኝ ግን እዚህ ተማሪዎች
ፊት አደለም እያለች መምህሯ እግር ስር ወድቃ ልመናዋን ቀጠለች።
:
መምህሯ ግን የተማሪዋን ስሜት ለአፍታ ቆም ብላ ለመረዳት ከመሞከር
የከፋ ስሜት ውስጥ ሆና እየደነፋች ነው።
፡
በዚህ ጊዜ በእድሜ ጠና ያሉት ሴት ዳይሬክተር ቆይስቲ መምህር ምን
እንደተፈጠረ ንገሪኝ ብለው ዳይሬክተሯ መምህሯንና ተማሪዋን ወደ ቢሮ
ወሰዷቸው።
፡
ከዛም ልጅቷን በተረጋጋ ሁኔታ እንድትቀመጥ ቢያደርጉም መምህሯ ግን
እስካሁን መረጋጋት አልቻለችም።
፡
ይሄኔ በመምህሯ ድርጊት ጥቂት ብስጭት ያላቸው ዳይሬክተሯ
መምህሯን ገላመጠው ዝም እንድትል ካደረጉ ቡኃላ ልጅቷን እረጋ
ብለው "ቦርሳው ውጥ ምንድነው ያለው" ብለው ጠየቋት።
፡
ልጅቷም "ቦርሳው ውስጥ ያለው ተማሪዎች በልተው የጣሉት ትርፍራፊ
ነው ያለው" አለች በህፍረት እየተሸማቀቀች።
፡
ዳይሬክተሯም በመገርምና ባለማመን ስሜት
"እንዴት እንዲህ ይሆናል" ሲሉ ጠየቋት።
፡
እሷም "ለወንድሞቼ ልወስድላቸው ብየ ነው" አለች አንገቷን ደፍታ
በሚያሳዝን ሁኔታ ቅስሟ ተሰብሮ።
፡
ይህን ጊዜ ዳይሬክተሯ ከመቀመጫቸው ተነስተው ተጠጓትና ፀጉሯን
እየደባበሱ "ኣይዞሽ የኔ ልጅ ተረጋግተሽ ስለ አባትሽና ስለ እናትሽ ንገሪኝ
አሏት።
፡
ይህች ኣንዲት ፍሬ ልጅ እንባዋ እየወረደ እንዲህ ኣለች " ኣባቴ
በሽፍርና ነበር እሚያስተዳድረን ቡኃላ ግን በሃሽሽ ተጠርጥሮ ወህኒ ቤት
ገባ። እናቴም ብትሆን ምንም ገቢ ያልነበራት ስትሆን ያባቴን መታሰር
ስትሰማ እራሷን ስታ ሆስፒታል ግባች።በዛው የተነሳ ሽባ ሁና
ቀረች።ታዲያ ሁለት ጨቅላ ወንድሞች ኣሉኝ ቤት ነው ጥያቸው
የመጣሁት ዘመድ ስለሌለን ዘወር ብሎ እሚያየን የለም።እሚላስ
እሚቀመስ የለንም።ታዲያ ይችን ፍርፋሪ ወስጄ ሂይወታቸውን ብታደጋት
ብዬ አሰብኩና ተማሪዎች አስተርፈው የጣሉትን ሳያዩኝ ለቃቅሜ ቦርሳየ
ውስጥ ኣስገባሁ።ይሄን ነው ያደረኩት።እናም እባካችሁ ለተማሪዎች
እንዳትነግሩብኝ።ትምህርቴንም ቢሆን አቋርጣለሁ።ብቻ አትናገሩብኝ
እያለች አንጀት በሚያላውስ ሁኔታ እንባዋን በአራት መንታ
እያዘነበች ችግሯን ምንም ሳትደብቅ በልጅ አንደበቷ እተኮላተፈች
ለማስረዳት ሞከረች!