13/03/2026
ይህ እንባ የወገን ያለ የህዝብ ያለ የሚል ድምጽ ምልክት ነው
**
ይህኝ የጋሞ እናቶች ናቸው። ሁሉን አሜን ብለው የሚኖሩ ለአሜን የተፈጠሩ ምስኪን ነፍስ ያላቸው ውድ የሆኑ እናቶች ።
ዛሬ ግን ልጆቻቸውን ቀብረው ፣የቤታቸውን ምሶሶ የሆነውን አባወራ ሞት ቀምቷቸው ማንባት ውሎ አዳራቸው ከሆነ እነሆ 3 ቀናትን ተቆጠሩ።
በእነኝህ እናቶች መንደር ክቡር የሆነው የሰው ልጅ እንደ ተራ ነገር በየደቂቃው ከአፈር ክምር ውስጥ በድን ሥጋው እየተለቀመ ይወጣል።
ከአከባቢው የሚመጡ ምስሎችን የሚያመላክቱት አስክሬኖች እንኳን በክብር ጋቢ ለብሰው በሳጥን ተሸፍነው እተቀበሩ አይደለም።
ከሞቱት ውጪ የተፈናቀሉ በሺ የሚቆጠሩ አባወራዎች መሄጃ ጠፍቷቸው በየጥጋ ጥጉ ሀገሬው ጋ ተጠግተው ተቸግረዋል።
ይህ ህዝብ ክፉ ዘመን ተደቅኖበት ፈተነው እንጅ ለእራሱ የማያንስ የሰው እጅን መመልከት እንደ ቅጣት የሚቆጥር ክቡር ህዝብ ነበር።
ዛሬ ግን ድጋፋችሁን ይሻል። የክልል መንግስታት፣የፌዴራል ሴክተር መስርያ ቤቶች፣የሃይማኖት ተቋማት፣ረጅ ድርጅቶች ፣የፋይናንስ ድርጅቶች ከሐዘን መግለጫ ከፍ ያለ የዕለት ደራጅ ምግብ፣መጠለያ እና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ትለግሱ ዘንድ ተጠይቃችዋል።
ያው የእናንተው ወገን አይደለምን ? በክፉ ዘመን አብሮነታችን ካልታዬ ወደማን ሄደን እንሸሸጋለን
እባካችሁን 🙏?Kune Demelash kassaye -Arba Minchchnch