15/09/2023
ሰርክ አዲስ ---አዲስ አበባ!
አዲስ አበባ ሁሌም አዲስ ናት! ዘወትር አዳዲስ ነገሮች መስራትና መዋብን ያወቀችበት የሁላችን መዲና!
አዲስ አበባ አጠናቀን በሸኘነው 2015 ዓ.ም የበርካቶችን እምባ አብሳለች! ገጽታዋን የቀየሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ገንብታ በርግጥም ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን የማረጋገጥ ጉዞዋ ሰምሮላታል፡፡ አዱ ገነት አዲስ ነገር መፍጠር አዲስ ልማዷ ነውና ሸማችን ከአምራች ያገናኙ በአምስቱ የከተማዋ መውጭያና መግቢያ በሮች ግንባታ ጀምራ የሁለቱን ጥንቅቅ አድርጋ በማጠናቀቅ ለህዝቡ እነሆ ብላ ሰጥታለች!
መጀመር ብቻ አይደለም አጠናቅቆ ስራ መጨረስ የሚታውቅባት አዲስ አበባ የገበያ ማዕከላቱ ተጠናቅቀው በተመረቁ አፍታ ሳይቆዩ ስራቸውን ጀምረዋል! በአምራችና በሸማች መካከል የተሰገሰገውን ደላላ ማራገፍ ጀምረዋል፡፡ እነኚህ ገበያ ማዕከላት ጅምላም ችርቻሮም የሚያገበያዩ ናቸው፤ ዘመናዊ የማቀዝቀዣና ማሞቂያ መሳሪያ የተገጠመላቸው ማከማቻ ናቸውና ምርት ሳይበላሽ ማቆየት የሚያስችል አቅም አላቸው!
የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ፣ የህጻናት መጫወቻና መቦረቂያ ገንብታ እነሆ ያለችውም በ2015 ተሰርቶ የአዲስ አመት አዲስ ስጦታ ብላ ብቅ ያለችበት አመት ነው !
የአረጋውያን መጦሪያና እንክብካቤ ማዕከል ተመርቄ ለአባቶች ማረፍያነት ጀምሯል! እየተለወጠች ያለችው አዲስ አበባ ይህ ነው አዲሱ መልኳ፡፡
ለከተማዋ መለወጥና መትጋት መነሻ የሆኑት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሁሌም ከአንደበታቸው የማይጠፋው አባባል መሬት መያዝ የመጀመሩ ማሳያ ነው፤ "አዲስ አበባን እንደ ሰሟ አበባ እናደርጋታለን" ይላሉ። ይሄው እየሆነ ነው።
ሌላው ‹‹አዲስ አበባ የሁላችን ቤት ናት ››ይላሉ። እውነት ነው! አዲስ አበባ ለሁሉ እንድትመች መኖሪያም መስሪያም ለማድረግ በትጋት ሰርተው ለውጥ አሳይተዋል፡፡ የለውጡን ፍሬ ሁሉም የሚቋደሰው ለማድረግ በትጋት ሰርተዋል፡፡
ራዕያቸውን የተጋሩ ልበ-ቀና ባለሀብቶች ከጎናቸው ተሰልፈዋል ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ተወተዋል፡፡ በመንግስት በጀት ከሚሰሩ በርካታ የልማት ስራዎች በተጨማሪ ለሰው ልጅ ሕይወት መቀየር የላቀ ፋይዳ ያላቸውን በሰው ተኮር ስራዎች ማኅበረሰቡን በማነቃነቅ የሕዝቡን የመረዳዳትና የመደጋጋፍ ዕሴት ያጎለበቱ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
በጎ ፈቃደኝነት ባህል ማድረግ ያስቻለ ስራ ተስረቷል፤ አዲስ አበባ ከተማ ማዕድ በማጋራት ውስጥ ፍቅርም የምትሰጥ ከተማ ናት! አዲስ አበባ ከተማ በክረምት ወራት ብቻ ከ16 ሺህ በላይ የአቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን ቤት አፍርሳ አሳምራ በመገንባት ለነዋሪዎቿ ምቾት ለመስጠት ሳትታክት የምትሰራ ከተማ መሆንዋን አሳይታለች!
አዲስ አበባ ባለፈው የሰራቻቸውን ስንቅ እያደረገች ለተጫማሪ ድል በትጋት የምተሰራ ከተማ ያደረጓት ከንቲባ አዳነች ናቸውና ስለሰሩት መልካም ስራ እናመሰግናለን!🙏 አዲሱ ዓመት ለርሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው የሰላም የጤናና የፍቅር እንዲሁም የብዙ መልካም ስራ መስርያ አመት አንዲሆንላቸው እንመኛለን!🙏