22/08/2026
በዓለ ንግስ
👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በእናታችን ስም በክብር ለምናመሰግንበት ትንሣኤና ዕርገት መታሰቢያ አመታዊ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን
👉 እድሜዋ 64 ሲሆን በእናት አባቷ ቤት 3 ዓመት በቤተመቅደስ 12 ዓመት ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9 ወር ከ 5 ቀን ከልጇ ከወዳጇ ጋር 33 ዓመት ከ 3 ወር ከቆየች በኋላ ዓለምን ለማዳን በእለት አርብ ጌታችን በመስቀል በተሰቀለም ጊዜ የሚወዳት እናቱን ለሚወደው ደቀ መዝሙር ለዮሐንስ እነኋት እናትህ በማለት የአደራ ልጆቿ እንድንሆን ያደራ እናታችን እንድትሆን በቀራንዮ በእግረ መስቀል ስር ለኛ ለሁላችን ሰጥቶናል
👉ነሐሴ 16 ቀን አስደናቂውን የእመቤታችንን #የዕርገቷን በዓል ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች የእመቤታችን ማርያምን ሱባኤ በፍፁም በረከት እንድንፈጽም ያደረገን ምስጋና ይግባው ጣዕመ ፍቅሯን ያላረቀችብን እመቤታችንን ምስጋና ይግባት የአባቶቻችን #ሐዋርያት በረከትና ረድኤት ለሁላችንም ይድረሰን
👉የእመቤታችን የእረፍቷ ጊዜ ሲደርስ ጥቂት ታመመች እመቤታችን የአምላክ እናት እንደመሆኗ መጠን ሕመም ባይገባትም የሰው ልጅ እንደመሆኗ መጠን ነው የታመመችው አገልጋይዋ ቅዱስ ዮሐንስ በኤፌሶን ወንጌልን እያስተማረ ሳለ ትዕዛዝ በደመና ተጭኖ ወደ እመቤታችን መጣ ሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት በፀጋ አውቀው በደመና ተጭነው መጡ ሁሉን የምታፅናና እመቤት ሐዋርያትም ሲያፅናኗት ደስ ይበልሽ አሏት
👉እመቤታችንም በአልጋዋ ጠርዝ ተቀምጣ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ወደ ዘላለማዊው ዓለም እንደምሄድ በምን አወቃችሁ አለቻቸው ሐዋርያትም ‹ በደመና ጭኖ እንደ ዓይን ጥቅሻ ያመጣን አንቺ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ልትሄጂ ስለሆነ ነው አሏት
👉እመቤታችንም ድምጿን ከፍ አድርጋ ጌታዬ ፈጣሪዬ መድኃኒቴ ሆይ ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈፅሜ አመሠግናለሁ የእኔን አገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ አድርገህልኛልና ከእንግዲህ ያመሠግኑኛል አለች
👉 ከእነሱ መለየቷን ሲያውቁ ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ጠየቁ ወላዲተ አምላክም እጇንም በላያቸው ላይ ዘርግታ ባረከቻቸው በዚያን ጊዜ የክብር ባለቤት ልጇ እልፍ አእላፍ መላእክት አጅበውት እያመሰገኑት መጥቶ አረጋጋት በሰማይ ያዘጋጀላትን ተድላ ደስታ ነገራት
👉ጌታችንም ከገነት ያመጣውን አፒሊያኖስ የሚባል መዓዛው ለነፍስ የሚጣፍጥ የሚመስጥ አበባ በአፍንጫዋ እያሸተተች በጆሮዋ እየሰማች ያለ ጣር ያለ ጋር በተመስጦ በደስታ ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየ
👉ጌታችንም ንፅህት ነፍሷን የብርሃን መጎናፀፊያ አልብሶ በመላእክት ዝማሬ ጥር 21 ቀን ወደ ሰማይ አሳረጋት ነብዩ ዳዊት ‹"ነፍሴ ሆይ ወደ እረፍትሽ ግቢ እግዚአብሔር መልካም ነገርን አድርጎሻልና›" እንዳለ መዝ.114÷7 #እመቤታችንም በልጇ ደስታ ወደ ሰማይ እረፍቷ ገባች
👉በሌላ ታሪክ #እመቤታችን በእረፍቷ ጊዜ ጌታችን ሲመጣ "ልጄ ወዳጄ እኔ አንተን ወልጄ እንዴት እሞታለሁ በእውኑ ሞት ለእኔ ይገባኛልን ብላ ጠይቃው ነበር
👉እሱም በሲዖል የሚሰቃዩትን ነፍሳት አሳይቷት እናቴ እነዚህ በሲዖል የሚሰቃዩት ነፍሳት የሚያገኙት እረፍት ባንቺ ሞት ነው ሲላት የሞቷን መልካምነት በሲዖል ለሚሰቃዩት ነፍሳት ነፃ መውጣት መሆኑን የተረዳችው #እመቤታችን ልጄ ሆይ ለእነዚህስ አይደለም አንዴ ሰባቴ ልሙትላቸው ብላ በፍቃዷ እዳረፈች ሊቃውንት ይተርካሉ
👉ወዳጆቼ እመቤታችን ለእኛ ለልጆችዋ ሰባቴ ለመሞት በነፍሷ የተወራረደች እናት ሆና ሳለ በዚህም እመቤታችንን በነፍስ ፍቅር አለመውደድ ማለት ከጣዕመ ፍቅሯ መሰደድ በቁም ለሲዖል እሳት መማገድ ነው
👉 አለማመስገን ማለት በነፍስ በሥጋ ከፀጋ ፍቅሯ መራቆት ለሰይጣንና ለሠራዊቱ ተላልፎ መሰጠት ነው ከወለላይቱ ከአዛኝቱ ጣዕመ ፍቅር መለየት ማለት ከሞቱት በላይ ከሚኖሩት በታች ሆኖ በቁም መሞት ነው
👉ከዚህ በመቀጠል አብይ ነጥቡ የወላዲተ አምላክ #ማርያም ነዉ በእለተ እረፍቷ የተፈፀመዉን የመሠወር ሚስጢር ያየ ዮሐንስ ሲሆን የመጨረሻውን ትንሣኤና ዕረፍት ለማየት የታደለዉ #ቶማስ ብቻ ነዉ
👉በወቅቱና በቦታዉ ያልነበረው ቶማስ የትንሣኤዋንና የዕርገቷን ምስጢር ተገልፆለት ለሐዋርያት በነገራቸው ጊዜ መቃብሩን ከፍተዉ ቢያዩት ባዶዉን ስላገኙት ለማየት ሐዋርያቱ በአመቱ ነሐሴ አንድ ቀን እንደገና ሌላ ፆመ ይዘዋል
👉ሱባኤ በመግባትና ፈጣሪያቸዉን በመለመን በነሐሴ 16ኛዉ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን እመቤታችንን መንበር ቅዱስ ጴጥሮስን ረዳት ካህን ቅዱስ እስጢፋኖስን ቀዳሚ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁሩቧቸዋል ሐዋርያትም የዚህ ድንቅ ሚስጢር ተካፋይ ሆነዋል
👉አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት የእመቤታችንን ማርያምን ዕረፍቷን ትንሣኤዋን እርገቷን በፆምና በፀሎት አይተዉ የህሊና ዕረፍታቸውን የደመደሙት እመቤታችን ለትንሣኤዋ ተጨባጭ ምልክት በዕርገቷ ጊዜ የሰጠችዉን ሰበን ለበረከት ከተካፈሉ በኋላ ነዉ ለኛም የቃል ኪዳን ልጆቿ በረከት ረድኤቷ ከኛ ጋር ይሁን
👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ጥበቃ የቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ረድኤት በረከት ጥርጥር የሌለባት የመንግስተ ሰማያት መዉረሻ ንፅህት ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታቸው ከኛ ጋር ፀንታ ትኑር "አሜን" ✝️💒✝️
#ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ኦርቶዶክሳዊ
Fasika Get
👉ነሐሴ 16/2018 ዓ/ም
ከታች ያሉትን Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።👇👇👇
YOUTUBE 👇👇
https://youtu.be/3nWnUmnfzbc
Facebook 👇
Fasika Photography ንጻሬ ምስሎች
Tiktok👇👇
https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-995purKgJnR