Yeka Woreda 07 Communication

Yeka Woreda 07 Communication Yeka Sub City Wereda 07 Communication Is a 24 Hour Working Public Medical 🌍

የአዲስ አበባ ከተማን ከፍታና የነዋሪዎቿን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ከጫካ ፕሮጀክት እስከ መገናኛ ደረጃውን ጠብቆ የተሰራ የኮሪደር መንገድ!
17/04/2026

የአዲስ አበባ ከተማን ከፍታና የነዋሪዎቿን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ከጫካ ፕሮጀክት እስከ መገናኛ ደረጃውን ጠብቆ የተሰራ የኮሪደር መንገድ!

"ቀጣዩ የብርሃን ተስፋ!‎‎በንፋስ ኃይል አማካኝነት ጨለማን ለመግፈፍ፣ ዐቅምን በለየ የቅድመ ጥናት እና ልዩ እቅድ ወደ ተግባር ዛሬ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን እውን አድርጋለች። ይህ ፕ...
16/04/2026

"ቀጣዩ የብርሃን ተስፋ!
‎
‎በንፋስ ኃይል አማካኝነት ጨለማን ለመግፈፍ፣ ዐቅምን በለየ የቅድመ ጥናት እና ልዩ እቅድ ወደ ተግባር ዛሬ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን እውን አድርጋለች። ይህ ፕሮጀክት 100 ሜጋ ዋት ንጹህ የኃይል አቅርቦት በመጨመር ወደ ዘርፈ ብዙ እና ቀጣይነት ባለው የኃይል መጻዒ ዕጣ ፈንታ ለመገንባት የምናደርገውን ጉዞ ያጠናክረዋል። ይህም አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ አብነት ነው።
‎
‎ለዘመኑ የኃይል ዐቅም ተደማሪ የሆነውን ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ተገኝተን በኩራት እያስመረቅን፤ የተገኘው ውጤት መሰል ስራዎችን ለማበራከት የሚያተጋን ነው።
‎በሁሉም ዘርፎች የምናስመዘግበው የኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ ተጠናክሮ እየቀጠለ፣ ይበልጥም እየለማ ይሄዳል። ከምንጊዜውም በላይ ታላቅ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም!



ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በጥረት የደመቀች፣ ከአለም የቱሪዝም ቁንጮ ላይ የተገኘች መዲናችንከቃል በላይ የሆነ፣ እምቢ ብሎ ጠንክሮ መስራት ለምን ውጤት እንደማይደርስ ያያንበት፣ በጠላት ጩኸት መሃል በድምቀት የታየ ውበ...
14/04/2026

በጥረት የደመቀች፣ ከአለም የቱሪዝም ቁንጮ ላይ የተገኘች መዲናችን

ከቃል በላይ የሆነ፣ እምቢ ብሎ ጠንክሮ መስራት ለምን ውጤት እንደማይደርስ ያያንበት፣ በጠላት ጩኸት መሃል በድምቀት የታየ ውበትን የተላበሰች፣ ከአለም የቱሪዝም ከተሞች መሃል በቁንጮነተ መታየት የጀመረች፣ ከምንም ተነስታ ይህ የምታዩት ከቃል በላይ የሆነ ስፍራን የተላበሰች ከተማ ነች።

ይህ ሰፈር ምኑም የማይታወቅ ሰፈር ነበር። ዛሬ ግን ለአይን ማራኪ፣ ለመንፈስ አርኪ፣ ለከተማችን ጌጥ፣ ለቱሪዝም መዳረሻ፣ ለወጣቱ መዝናኛ፣ ለህፃናት መፈንጫ፣ ለአንጋፋዎች ማረፊያ፣ ለተማሪዎች ማንበቢያ፣ ለስፖርተኞች መንቀሳቀሻ፣ ለሙሽሮች መድመቂያ፣ ..... ለማንም ይሁን ትርጉም ያለው ቦታ ሆኗል። ይህን ያየነው በአጋጣሚ አይደለም፣ በጥረት ነው። እንሰራለን ብለው በቆራጥነት በቆሙ አመራሮች እና ለህዝብ በሚያልም መንግስት የተሰራ የታሪክ ስፍራ ነው::

ነገ ትልቅ እንድትሆን የምንመኝላት ኢትዮጰያ ዛሬ ወስደን በምንጠቀምበት የምርጫ ካርድ የሚወሰን ነዉ!! ዛሬ ወስደን የምንጠቀምበት የምርጫ ካርድ ነገ ለምንጠይቅበት መብት፣ ለምንሻው ተጠያቂነት...
13/04/2026

ነገ ትልቅ እንድትሆን የምንመኝላት ኢትዮጰያ ዛሬ ወስደን በምንጠቀምበት የምርጫ ካርድ የሚወሰን ነዉ!!

ዛሬ ወስደን የምንጠቀምበት የምርጫ ካርድ ነገ ለምንጠይቅበት መብት፣ ለምንሻው ተጠያቂነት እና ለምንመኘው ሉዓላዊነት ብቸኛው ሕጋዊ እና ሰላማዊ መሣሪያችን ከመሆኑ ባሻገር ነገ ትልቅ እንድትሆን ለምንመኝላት ኢትዮጰያ ወሳኙ ጉዳይ ነዉ፡፡

በመሆኑም የመራጮች ምዝገባ ዜጎች የሚገቡት "ማህበራዊ ውል" ሲሆን፣ የመራጭነት ካርድ በመያዝ በጠንካራ የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ተመልካች ከመሆን ወጥቶ ውሳኔ ሰጪ መሆን ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ዴሞክራሲ በሂደት እንጂ በምኞት የማይገነባ በመሆኑ፣ በተፈጠረዉ ምቹ የፖለቲካ አዉድ፣ ካርድ በማውጣት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ወሳኝ ተዋናይ የመሆን ፍላጎትን እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያለንን ዝግጁነት በፖለቲካ ተሳትፎ ጥራት እዉን ማድረግ ዜጎች የሚወጡት ሃገራዊ ኃላፊነት ነው፡፡

ስለዚህ በሕዝብ ፈቃድ ላይ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት በፅናት የሚቆመው "ሀገሬ በእኔ ድምፅ ትመራለች" የሚል ፅኑ እምነትን በተግባር ማሳየት ኢትዮጵያን የሚመጥን የስልጡን ዜጎች ማሳያ ነዉ እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘ...
13/04/2026

የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንደስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል።

የመጀመሪያውን ክፍል ማክሰኞ ሚያዚያ 6/ 2018 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ።

12/04/2026
በመላው ኢትዮጵያ በክርስትና ጥላ ውስጥ በሚገኙ  ቤተ-እምነቶች ያሉ ክርስቲያኖች የትንሳኤን በዓል በተስፋ፣ በመስዋዕትነት እና በአዲስ መነሳት መንፈስ በአንድነት ያከብራሉ። ከሳምንታት የፆም፣...
12/04/2026

በመላው ኢትዮጵያ በክርስትና ጥላ ውስጥ በሚገኙ ቤተ-እምነቶች ያሉ ክርስቲያኖች የትንሳኤን በዓል በተስፋ፣ በመስዋዕትነት እና በአዲስ መነሳት መንፈስ በአንድነት ያከብራሉ። ከሳምንታት የፆም፣ ጥሞና እና ራስን የመመልከት ጊዜ በኋላ ፋሲካ በእውነተኛ አምልኮ፣ መንፈስን አድሶ፣ ቤቶችንም በደስታ ይሞላል። በዘመድ አዝማድ መጠያየቅ እና ማዕድ መካፈልም ፍቅርን ያዳብራል።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዓመታዊውን የፋሲካ መዐድ ማጋራት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአንድነት ፓርክ በጋራ መታደማቸው ለእውነተኛው የአንድነት መንፈስ ጉልህ ማሳያ ነው።

‎በዓለ ትንሳኤው በመላው ኢትዮጵያ የእምነት፣ ቤተሰባዊነት እና የመታደስ መንፈስ የሚታይበት ጊዜ ነው። ሁላችንም በዚህ የትንሳኤ መንፈስ ዛሬም፣ ነገም፣ ሰርክ ቤታችንን፣ ልባችንንም ለተቸገሩ ወገኖች እንክፈት! መልካም በዓል።

በየካ ከተማ አስተዳደር በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ አንድ ኪሎ ስጋ በ650 ብር እየተሸጠ ይገኛል።አስተዳደሩ የኑሮ ውድነቱን እና ገበያውን ለማረጋ...
12/04/2026

በየካ ከተማ አስተዳደር በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ አንድ ኪሎ ስጋ በ650 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

አስተዳደሩ የኑሮ ውድነቱን እና ገበያውን ለማረጋጋት እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዓሉን በደስታ እና እንደየ በሸማችአቅማችው እንዲያሳልፉ በ12ቱም ወረዳ በሚገኙ ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ አንድ ኪሎ ስጋን በ650 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

ህብረተሰቡም በአቅራቢያው በሚገኙ ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች ጎራ በማለት በተቀመጠው ተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት እና ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል የክፍለ ከተማው ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ሚያዝያ 04/2018 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

12/04/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ይላል፡፡

የሁላችንም ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ፥ የቱሪዝም የንግድ ፣ የባህል፣ የታሪክ፣ የብዝሓነት እና የአንድነት ማዕከል በመሆን የሁለንተናዊ ከፍታ ጉዞዋን በልዕልና እየቀጠለች ትገኛለች።

በሁሉም ዘርፍ ዘላቂና ቀጣይነት ያለዉ ለዉጥ እያስመዘገበች፣ ፕሮጀክት ጀምሮ በጥራት እና በፍጥነት የመጨረስ ተምሳሌት የሆነችውን አዲስ አበባ፣ በተለይም በኮሪደር ልማት፣ በወንዝዳር ልማት እና ለሰው ክብር ቅድሚያ በሚሰጡ ሰው ተኮር ስራዎች ዓለም የሚያስደምም ደማቅ አዲስ ታሪክ በመፃፍ ላይ ትገኛለች፡፡

በፈጣን ለውጥ ውስጥ የምትገኝው መዲናችን ፣ የመሶብ አንድ ማዕከልን በማስፋፉት፣ አገልግሎትን በማዘመን የህብረተሰባችን ተጠቃሚነት ለማላቅ ተግተን የምንሰራ፣ እንዲሁም እንደወትሮው አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ውብ፣ ለጎብኝዎቿ ተመራጭ፣ ንፁህና ነፋሻማ ፣ ለሁሉም ለመኖር ተስማሚ እንድትሆን በቁርጠኝነት እንደምንሰራ እያረጋገጥን፤ መልካም የፉሲካ በዓል እንዲሆን እንመኛለን።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዓሉ፣ የሰላም የፍቅርና የአንድነት እንዲሆን እየተመኘ፣ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት እና የመተሳሰብ እሴቶቻችን ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪውን ያቀርባል!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
መልካም በዓል

11/04/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

የትንሣኤ በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ መዳን ያለውን ፍቅር እስከ መስቀል ሞት የገለጸበትና የሞት ድል የተበሰረበት ታላቅ ዕለት ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በታላቅ ፍቅር፣ በትሕትና እና በመተሳሰብ ሊሆን ይገባል።

ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ያለንን አጋርነት በተግባር የምንገልጽበት፣ አንዳችን ለሌላችን የደስታ፣ የሰላም እና የአብሮነት ምክንያት የምንሆንበት በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ።
መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"ከተደጋገፍንና ከተረዳዳን የበርካታ ወገኖቻችን ሕይወት መቀየር እንደምንችል እስከ አሁን የሰራናቸው ተግባር ህያው ምስክር ናቸው!"አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ...
11/04/2026

"ከተደጋገፍንና ከተረዳዳን የበርካታ ወገኖቻችን ሕይወት መቀየር እንደምንችል እስከ አሁን የሰራናቸው ተግባር ህያው ምስክር ናቸው!"
አቶ ጃንጥራር አባይ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

ሚያዝያ 03/2018 ዓ•ም የካ ኮሙኒኬሽን

በየካ ክፍለ ከተማ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከፍተኛ ጥራት የታደሱ የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤቶች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ በተገኙበት የቁልፍ ርክክብ ተደርጓል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት ከተደጋገፍንና ከተረዳዳን የዜጎችን ሕይወት መቀየር እንችላለን። የቤት እድሳት ነዋሪዎችን ከተጎሳቀለ ኑሮ በማላቀቅ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ በበኩላቸው በዓሉን በመረዳዳትና በደስታ እንዲያሳልፉ በማድረጉ ረገድ የባለሀብቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቤት እድሳት የተደረገላቸው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፤ ቀደም ሲል ይኖሩባቸው የነበሩ ቤቶች ለመኖሪያነት የማይበቁና ለተለያዩ በሽታዎች የሚያጋልጧቸው እንደነበሩ አስታውሰው አሁን ግን መንግስት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዕለቱም ለነዋሪዎቹ ከቤት ቁልፍ በተጨማሪ የቤት ዕቃዎችና የበዓል መዋያ ስጦታዎች ተበርክተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው 215 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን ለተለያዩ አቅመ ደካሞች አስረከቡ **********በከተማችን የበጎ ፈቃድ ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ...
11/04/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው 215 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን ለተለያዩ አቅመ ደካሞች አስረከቡ
**********

በከተማችን የበጎ ፈቃድ ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተና ባህል እየሆነ መምጣቱ የሚያስደስት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ሁልጊዜም በበዓላት ወቅት እንደምናደርገው፣ ዛሬ በትንሣኤ በዓል ዋዜማ በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የገነባናቸውን 215 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች፤ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ለአቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአገር ባለውለታዎችና ለልማት ተነሺዎች ከሙሉ የቤት ቁሳቁስና ከበዓል መዋያ ጋር በስጦታ አበርክተናል ብለዋል።

ይህንን በጎ ተግባር በተለያየ መልኩ ለደገፋችሁ ልበ ቀና በጎ ፈቃደኞች፣ ተቋማትና አመራሮች በሙሉ በተለይም ከ 80 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ላደረገው የኦሮሚያ ባንክ በተጠቃሚዎች ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የትንሣኤ በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ በፍቅር ራሱን እስከ መስቀል የሰጠበት እና በትንሣኤ የምሥራች የተበሰረበት ነው ብለዋል።

በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በትሳኤን ዓላማ እና ምሳሌነት መሰረት በታላቅ ፍቅር እና መተሳሰብ ሊሆን ይገባል። ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ያለንን መተሳሰብ በተግባር የምንገልጽበት፣ አንዳችን ለሌላችን የደስታ፣ የሰላም እና የአብሮነት ምክንያት የምንሆንበት በዓል እንዲሆንልን ሲሉ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

Address

Around Signal Kibeb (101m)
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeka Woreda 07 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yeka Woreda 07 Communication:

Share

Category