ortodox_tewahdo_yemaryam

ortodox_tewahdo_yemaryam Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ortodox_tewahdo_yemaryam, Photographer, Meskel Square መስቀል አደባባይ, Addis Ababa.

እንኳን ለእምነ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዓመታዊበዓል አደረሰንሕዳር 17 በዓለ ዕረፍትዋ ነው"የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።"ምሳሌ 21፤11ቅድስት እናታችን የነበረችበት ዘመን ሐይማኖት የጠፋበት የ...
26/11/2025

እንኳን ለእምነ ቅድስት
ወለተ ጴጥሮስ ዓመታዊ
በዓል አደረሰን

ሕዳር 17 በዓለ ዕረፍትዋ ነው
"የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።"
ምሳሌ 21፤11

ቅድስት እናታችን የነበረችበት ዘመን
ሐይማኖት የጠፋበት የግፍ አእባን የሚወርድበት
እንዲህ እንዳለንበት ዘመን በፈቃዳቸው ያበዱ በዝተው ሐገር የሚታመስበት መስሎ አዳሪ አብሎ መስካሪ የበዛበት ተፈሪ ተከባሪ የጠፋበት ካህናት የሚታረዱበት ዘመነ ሰማእታት ነበር አፄ ሱስንዮስ እምነት ለውጠው የማሉበትን ወንጌል ክድው በካቶሊካውያን ቤተክርስቲያን መከራዋን ያየችበት ወቅት ይህ ሰአት ነው ቅድስት ወለተ ጴጥሮስን ያስገኘ!!!

ንጉሱ በተገኘችበት እንድትገደል ሞት ቢያውጅባትም በጎንደር ከተማ በገመድ እየተጎተተች ስቃይዋን ቢያበዙም ካህናቱም ሕዝቡንም ከማንቃት ከተዋህዶ እንዳያፈገፍጉ ከማትጋት ማንም ያገዳት የለም ኃይለ እግዚአብሔር አልተለያትምና።
በትዳር ኖራ ሶስት ልጆችንም አፍርታለች ግን የአበው መዋረድ የቤተክርስቲያን መንደድ እመር አድርጎ ከቤትዋ አስወጣት በሰሜን ኢትዮጵያ ሐያል ነበልባል ሆና ንጉሱንም ከሐድያኑንም መድረሻ አሳጣች ብዙዎች መከራን ተሰቅቀው እምነት ክደው እንዳይጠፉ እንደውም ሰማዕትነት ክብር እንዳለው በመግለጽ ብዙዎችን ለሰማያዊ ክብር እንዲበቁ ምክንያት ሆነች።
በዋልድባና በሌሎች ገዳማት በርካታ የመንፈስ ቅዱስ ልጆች ነበራት
ምንኩስናን ተቀብላ የ700 መናንያን እናት እመምኔትም ነበረች ሞትን የማትፈራ ገዳማዊት ባህታዊት ቅድስት እምነ ወለተ ጴጥሮስ ።
እናታችን ዛሬም አትለይን በምልጃሽ ታደጊን በእምነት በምግባር እንድንተጋ ጸሎትሽ ይርዳን በቃል ኪዳንዋ ትጠብቀን
ስለ ግፉአን ስዱዳን በጭንቅ በመከራ ላሉ ከእግዚአብሔር ትማልድልን ምልጃ ጸሎቷ ከዘረኝነት ደዌ ከፍቅር ረሐብ ከዝሙት እሳት ከክሕደት አሽክላ ይሰውረን የተግባር ሰው ኹላችንንም ያድርገን
አሜን አሜን አሜን

ደብረ ታቦር የጌታችን የባሕርይ አምላክነት የተገለጠበት ብቻ ሳይኾን የቅዱሳንም ክብር የተገለጠበት ነው። ቅዱሳን ከዚህ ዓለም በዕረፍትም በመነጠቅም ከተለዩ በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገሩ ...
22/08/2025

ደብረ ታቦር የጌታችን የባሕርይ አምላክነት የተገለጠበት ብቻ ሳይኾን የቅዱሳንም ክብር የተገለጠበት ነው። ቅዱሳን ከዚህ ዓለም በዕረፍትም በመነጠቅም ከተለዩ በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገሩ በገሀድ ታይቶበታል።

እግዚአብሔርን በመለኮታዊ ክብሩ ያዩ ዐይኖች እኛም ቅዱሳን ነን በማለት አይመጻደቁም። እግዚአብሔርን ካየን ቅዱሳን አያስፈልጉኝም በማለትም አይታበዩም።

ይልቁንም በልዩ መደነቅ በልዩ ተመስጦ ኾነው ከቅዱሳን ጋር ለመኖር ይጓጓሉ። ጌታቸውንም በአክብሮት ይጠይቃሉ። ለእኛ በዚህ መኾን መልካም ነው። ለአንተም ለቅዱሳንም ቤት እንሥራ ይላሉ። እግዚአብሔር ይከበርላቸው እንጅ ለቅዱሳን የስማቸው መጠሪያ ቤት ለመሥራት ያብቃቸው እንጅ ለራሳቸው ግድ የላቸውም።

ዋጋ የላቸውም የሚለው መከራከሪያቸውን ዋጋ የሚያሳጣ ድንቅ ዕለት!

ዳዊት በመዝሙር ''አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።'' [፻፴፩፥፰] ብሎ ታቦቱ ለክርስቶስ የሆነችውን እናቱን፣ እናታችንን [፹፮፥፭] ተነሺ እንዳለ የአባቱን ቃል ጠብቆ...
22/08/2025

ዳዊት በመዝሙር ''አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።'' [፻፴፩፥፰] ብሎ ታቦቱ ለክርስቶስ የሆነችውን እናቱን፣ እናታችንን [፹፮፥፭] ተነሺ እንዳለ የአባቱን ቃል ጠብቆ ከአባቱ እንደተማረ የአባቶቹ ልጅ ጠቢቡ ሰሎሞን በመኃልየ መኃልዩ ''ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ።'' [፪፥፲] ብሎ ትንሣኤዋን በትንቢት አበሰረን፤ዳግመኛም የነሳው ሥጋ የአብርሃም ልጅ ከሆነች ከድንግሊቱ መሆኑን ጳውሎስ ለዕብራውያን እንደነገረ [፪÷፲፮] ዳዊትም ጌታ የነሳውን ይህን ቅዱስ ሥጋ እንዳከበረው እና መበስበስን ያይ ዘንድ እንዳልተወው መስክሯል። [፲፭÷፲]
ለዚህም ነው እኛ ልጆችሽ ትንሣኤሽን የምናምን፤ ከሰዱቃውያን ተለይተን በቀኙ ቆመሽ እንደምታማልጂን እምናምን።[መዝ ፵፬፥፱] ነብሰ በላውን ያስማርሽ፣ለውሻ የምትራሪ ርኅራኄ ካንቺ ዘንድ ያለ እናት ሆይ በቀደመ ቃልኪዳንሽ፥ በአንጻረ ያዕቆብ ኢትዮጵያ ላንቺ የቃል ኪዳን ሃገር ሆና የተሰጠች እንደሆነች ኢሳይያስ ነግሮናል። [፵፫፥፫] በመሆኑም እናታችን ሆይ ትንሣኤሽን ለሐዋርያት እንደገለጥሽላቸው፣ የእናት ሀገራችንን ትንሣኤ አሳዪን። ጥፋቷን አታሳዪን።

ለዚህች ቀን የደረሳችሁ፡ እንኳን ለበዓለ ፍልሰቷ አደረሳችሁ፤ አደረሰን፨

#ነሐሴ #ኪዳነምሕረት #ፍልሰታ

‹‹ሰኔ 21›› ቀን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዳሴ ቤቷ ነው።  ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ድንግል እናቱን እመቤታችንንና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ወረደ፡፡እመቤታችንን መንበር፣ ጴጥ...
27/06/2025

‹‹ሰኔ 21›› ቀን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዳሴ ቤቷ ነው።

ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ድንግል እናቱን እመቤታችንንና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ወረደ፡፡

እመቤታችንን መንበር፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቁርቧቸዋልና ፍጹም ደስታም ሆነ፡፡

ዳግመኛም ጴጥሮስን እጁን ጭኖ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞታል፡፡ በዚህም ጊዜ ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ሐዋርያት አንድ ሆነው አመስግነዋል።

ይህ ፅሑፍ ወይም ታሪኩ ሰኔ 20 ቀን ሕንፀተ ቤተክርስቲያን የቀጠለ ነው።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጣዕም ፍቅሯ በረከቷ ምልጃና ጸሎቷ ከሁላችን ጋር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር🙏

ተነስቷል ጌታ ተነስቷል
20/04/2025

ተነስቷል ጌታ ተነስቷል

ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝...
29/03/2025

ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝ማረያም💝

27/03/2025
ዕረፍቱ ለአባ ጳውሊ
09/02/2025

ዕረፍቱ ለአባ ጳውሊ

አስተርዮ ማርያም 🤍
28/01/2025

አስተርዮ ማርያም 🤍

Address

Meskel Square መስቀል አደባባይ
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ortodox_tewahdo_yemaryam posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category