Daniel Ary' nayoo

Daniel Ary' nayoo Introducing cultures, History, Places,nature, Photos, new informations etc.

ወንድም ዶ/ር በለጠ ሽኩሮ የወርቅ ኒሻንና ዲፕሎማ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል!===========================የአቢሲኒያ የኢንደስትሪ ሽልማት ድርጅት የአለርት ስፔሻላይዝድ   ሆስፒታል...
26/07/2024

ወንድም ዶ/ር በለጠ ሽኩሮ የወርቅ ኒሻንና ዲፕሎማ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል!
===========================
የአቢሲኒያ የኢንደስትሪ ሽልማት ድርጅት የአለርት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማሀበራዊ ዘርፍ ህዝቡን በቅንነት በማገልገል ላበረከተው አስተዋፅኦ እና ለሃገርና ለህዝብ የሚጠቅም አገልግሎት በመስጠቱ የ2016 ዓ.ም የአቢሲኒያ የወርቅ ዋንጫና ዲፕሎማ ሲሸልም የቀዶ ጥገና ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር በለጠ ሽኩሮ የወርቅ ኒሻንና ዲፕሎማ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል!

በላቀ አገልግሎትህ አኩርተንሃል! እንኳን ደስ አለህ!

Via Habtamu Taye Belete Shikuro

The Arabian Peninsula and East Africa from Space
10/05/2023

The Arabian Peninsula and East Africa from Space

“መጪው ዘመን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምክንያት አስፈሪ ሆኗል”፦ ጀፍሪ ሒንተን =======================================ቻትጂፒቲን የመሰሉ ፈጠራዎች የሰው ልጅን ...
03/05/2023

“መጪው ዘመን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምክንያት አስፈሪ ሆኗል”፦ ጀፍሪ ሒንተን
=======================================
ቻትጂፒቲን የመሰሉ ፈጠራዎች የሰው ልጅን መልሰው ሊቆጣጠሩት እንደሚችሉ የሰው ሠራሽ አስተውሎት አባት የሚባሉት ጀፍሪ ሒንተን ፍንጭ ሰጡ።
የ75 ዓመቱ ጀፍሪ ሒንተን ይህን የተናገሩት ጉግል ኩባንያን በለቀቁበት ወቅት ነው።
እኒህ ሳይንቲስት ለኒውዮርክ ታይምስ በጻፉት ሐተታ፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዙርያ በሠሯቸው ሥራዎች አሁን ላይ ጸጸት እንደሚሰማቸው ጠቅሰዋል።
ሳይንቲስቱ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ደግሞ እንዴት አንዳንድ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፈጠራዎች ‘አስፈሪ እና አደገኛ’ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተንትነዋል።
‘ሰው ሠራሽ አስተውሎት ፈጠራዎች ለጊዜው ከሰው ልጅ በላይ አልሆኑም፤ በጊዜ ሂደት ግን የሰው ልጅን ይቆጣጠሩታል ይመስለኛል’ ብለዋል።
የዶ/ር ሒንተን በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ልህቀት ዙርያ ያደረጓቸው ጥናት እና ምርምሮች ቻትጂፒቲን ለመሰሉ ትልልቅ ሥራዎች መፈጠር መሠረት የጣሉ ናቸው።
የብሪታኒያ እና ካናዳ ጥምር ዜጋ የሆኑት ሳይንቲስቱ፣ የአስተውሎት ሥነ ልቡና (cognitive psychologist) እና የኮምፒውተር ሳይንስ ዝነኛ ተመራማሪ ናቸው።
ከጉግል መልቀቃቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ቻትቦት በቅርብ ጊዜ የሰው ልጅ አእምሮ ሊሸከመው የሚችለውን መረጃ በተሻለ ሊሰንድ ይችላል ብለዋል።
”ለምሳሌ አሁን ጂፒቲ በጠቅላላ ዕውቀት ዙርያ ካየነው የሰው ልጆችን በሙሉ ይበልጣል። በምክንያታዊነት እና ሚዛናዊነት ካየነው ገና ከሰው ልጅ አቅም አልደረሰም። ነገር ግን ምክንያታዊነት እና አመክንዮን ቀስ በቀስ ተምሮ የሰው ልጅን ሊልቅ ይችላል” ብለዋል።
ሳይንቲስቱ ዶ/ር ሒንተን ጨምረውም፣ ‘አሁን ባለው ፍጥነት የሰው ሠራሽ አስተውሎት የሰው ልጅን አስተውሎት በልጦ ለመገኘት ብዙ ዘመን አይወስድበትም’ ብለዋል።
በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ደግሞ ዶ/ር ሒንተን ይህን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፈጠራ በጎ ላልሆኑ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ የሚያውሉ አካላትን ወቅሰዋል።
የሰው ልጆችን እና ቻትቦትን በማወዳደር አደገኛነቱን ሲያስረዱም፣ 10 ሺህ ሰዎችን ለማሰልጠን እና አንድ ቦታ ለማድረስ የሚወስደውን ዘመን በማሳያነት በመጥቀስ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ግን አንድን መረጃ አንድ ጊዜ ከተማሩት በኋላ በቅጽበት 10 ሺህ ማሽኖች አወቁት ማለት ነው። ይህ ለሰው ልጅ ስጋት ነው ብለዋል።
ዶ/ር ሒንተን ሰው ሠራሽ አስተውሎት ላይ እየተሠራ ያለው ነገር አሳስቧቸው ሥራ መልቀቃቸውን ቢጠቅሱም ሌሎች ምክንያቶችም ሥራ ለመልቀቃቸው ምክንያት መሆናቸውን አልሸሸጉም።
“አሁን ዕድሜዬ 75 ደረሰ። ጡረታ ጊዜዬ ነው። ስለ ጉግልም በጎ ነገሮችን መናገር አለብኝ፤ ለጉግል እየሠራሁ ስለ ጉግል በጎ ነገር ባወራ አያምርብኝም፤ መልቀቅ ነበረብኝ’ ብለዋል።
ዶ/ር ሒንተን ጉግል የሰው ሠራሽ አስተውሎትን በተመለከተ ኃላፊነት የሚሰማው ድርጅት እንደሆነ መስክረዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

ፈጣሪ ይመስገን!!Thank You, God, for Saving Me From such an Accident!! ====================================In life, some event...
30/09/2022

ፈጣሪ ይመስገን!!
Thank You, God, for Saving Me From such an Accident!!
====================================
In life, some events and occurrences happen that are not planned for, one of such is, getting involved in an accident. No matter how big or small the accident might be, coming out of it alive is not a small feat and it is worth showing gratitude to God for. Thank you very much for saving my life after that terrible accident. I’m so grateful you exist and I get to enjoy this world because of you. Every day, whether bad or good, I know you are here with me watching over me and that gives me the strength to keep pushing through any obstacle.

Thanks to God!! From Horror to Hope, I survived a traumatic Motorcycle Accident!!
30/09/2022

Thanks to God!!
From Horror to Hope, I survived a traumatic Motorcycle Accident!!

Thanks to God!! From Horror to Hope, I survived a traumatic Motorcycle Accident!!
30/09/2022

Thanks to God!!
From Horror to Hope, I survived a traumatic Motorcycle Accident!!

ምዕራባዊያን አሁን እየወጉ ያሉት የወደፊት ተስፋና ራዕያችሁን ነው "=========================================" ምዕራባዊያን አሁን እየወጉ ያሉት የወደፊት ተስፋና ራዕ...
24/11/2021

ምዕራባዊያን አሁን እየወጉ ያሉት የወደፊት ተስፋና ራዕያችሁን ነው "
=========================================
" ምዕራባዊያን አሁን እየወጉ ያሉት የወደፊት ተስፋና ራዕያችሁን ነው "
አሜሪካንና አውሮፓውያን እንወዳችኋለን ቢሏችሁ አትመኗቸው። ተጠንቀቁ, እነሱ የሚፈልጉት ሀብታችሁን ነው እነሱ የሚወዱት የዚችን ሀገር ነዳጅ እንጂ ህዝቦችዋን አይደለም ። ዛሬ እናንተ እኔን ትወጉ ዘንድ እያነሳሷችሁ እና እያገዝዋችሁ ነው :: ነገር ግን እናንተ ከኔ ጎን ቆማችሁ እነሱን ብትዋጉ ብልህነት ነው , ምክንያቱም ምዕራባውያን አሁን እየወጉ ያሉት የወደፊት ተስፋና ራዕያችሁን ነው
ልብ ያለው ልብ ይበል !
Do not trust Americans or Europeans who say they love you. Be careful! They want your wealth They love the fuel of this country, not its people. Today you are inspiring and helping to fight me . But it is wise to stand by me and fight them. Because what the West is fighting for now is your hope for the future
' Muammer Ghadaffi '

በሁለትና ከዚያ በላይ ሃሳቦች መካከል በሚጎድል ወጥነት የተነሳ የሚፈጠር ውስጣዊ ውጥረት እና ምቾት ማጣት!!!===========================================በአንድ ሞቃት...
24/12/2019

በሁለትና ከዚያ በላይ ሃሳቦች መካከል በሚጎድል ወጥነት የተነሳ የሚፈጠር ውስጣዊ ውጥረት እና ምቾት ማጣት!!!
===========================================
በአንድ ሞቃት የበጋ ቀን አንድ ቀበሮ በጫካው ውስጥ ምግብ ፍለጋ ሲማትር የወይን ዘለላዎች ተንጠልጥለው ያይና ይጎመጃል።
ወደ ወይኑ ዛፍ ተጠግቶ ወደላይ በመዝለል የመጀመሪያውን ሙከራ በማድረግ ዘለላዎችን ለመድረስ ሞከረ አልተሳካም።
በድጋሚ ተጠግቶ አቅሙን አሰባስቦ ለሁለተኛ ጊዜ የወይኑን ዘለላዎች ለመቅጠፍ ዘለለ ፤ በጭራሽ አልደረሰበትም
ለሶስተኛ ጊዜ ቢሞክርም አልሆነም
በተደጋጋሚ ሞክሮ ያልተሳካለት ቀበሮ
" ይሄኔ እኮ ፍሬው መራራ ነው እንድያውም ጊዜዬን ለምን ላባክን?! "
ሲል ለራሱ ተናግሮ መንገዱን ቀጠለ 😃

ይሄ ከኤዞፕ ታዋቂ ተረት መካከል አንዱ ነው ሰዎች ሊደርሱበት የማይችሉት የመሰላቸውን ጥግ ከመኮነን አይቦዝኑም።
የዚህ አይነት ዝንባሌ ከተረቱ በተወሰደ ሃሳብ
"sour grape" በሚል በተለምዶ ይጠራል።
~
sour grapes an attitude in which someone disparages or pretends to despise something because they cannot have it themselves.
In Aesop's fable The Fox and the Grapes , the fox, unable to reach the tempting bunch of grapes, comforts himself with the thought that they were probably sour anyway.
~
በስነልቦና ደግሞ "Cognitive Dissonance" ይባላል። በሁለትና ከዚያ በላይ ሃሳቦች መካከል በሚጎድል ወጥነት የተነሳ የሚፈጠር ውስጣዊ ውጥረት፣ ምቾት ማጣት ወዘተ … ነው።
ይህን የስነልቦና ውጥረት ለመቋቋም ሲሉ ሌላ ሃሳብ ከላይ የተጠቀሰው ምሳሌ ላይ ቀበሮው መብላት የፈለገውን ነገር ባለማግኘቱ እና መብላት በመፈለጉ መሃል የተፈጠረውን የሃሳብ ግጭት ና በውስጡ የሚፈጠረውን ፀፀት ለመቀነስ ወይ ለማስቆም (Minimize regret of irrevocable choices) የተጠቀመው ዘዴ የወይኑን ፍሬ መኮነን ነበር።

ሰዎች ራሳቸውን ለሰው ማጋለጥ አይደለም የገዛ ራሳቸውን በግል መጋፈጥ (fear of knowing one's self) ይፈራሉ።
ቀበሮው አለመቻሉን ሙከራው የተሳካ አለመሆኑን ለራሱ ከማመን ይልቅ ወይኑ መራራ ሊሆን እንደሚችል ለራሱ በመንገር ለማለፍ ሲሞክር ይታያል።
~
Moral of Aesop's Fable:
"It is easy to despise what you cannot get"

24/12/2019

ራስህን በራስህ ክፈት - ቆላፊውም ከፋቹም አንተው ራስህ ነህ! (እ.ብ.ይ.)
=========================================
አብዛኛውን ጊዜ የዓለሙ ትምህርት በኑሮህ፣ በዩንቨርስቲ ቆይታህ፣ በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጊዜህ የሚያስቀስምህ ቀለም፣ የሚያስጨብጥህ ዕውቀት ስለውጫዊው (ቁሳዊው) ዓለም እንጂ ስለአንተነትህ አይደለም፡፡ ት/ቤቱ፣ ዩንቨርስቲው፣ ኮሌጁ፣ ማህበረሰቡ፣ ሚዲያው፣ ቤተሰብህ፣ ወዳጅ ጎረቤትህ፣ ዘመድ አዝማድህ የሚግትህ ካንተ ውጪ ስላለ ነገር እንጂ አንተ ራስህን ፈልገህ እንድታውቅና ከውስጥህ ጋር እንዴት ልትግባባ እንደምትችል አይደለም፡፡ ምሳሌው፣ አብነቱ ሁሉ የሌላ ሰው እንጂ የአንተ አይደለም፡፡ ሌሎችን መምሰል እንጂ አንተ ራስህን ትሆን ዘንድ ዓለሙ አይሰብክህም፡፡ ዓለማዊ ሞዴል ወይም የቢዝነስ ሰው አርአያ እያሳየህ በእነሱ አምሮትና ምኞት ያንቆላልጭሃል እንጂ እውነተኛው አንተነትህን ከውስጣዊ ነፍስህ ፈልቅቀህ ታወጣ ዘንድ ሰዋዊ ተምኔትህንና ውስጣዊ እውነትህን እንድታውቅ አያግዝህም፡፡ ቤተሰብህም ቢሆን ቀለብህን እየሠፈረ ልብስህንና የሚያስፈልግህን ቁሳቁስ ያሟላልሃል እንጂ ከራስህ ጋር ትገናኝ ዘንድ መንገድ አያመቻችልህም፡፡ መምህርህም በምሳሌ የሚያስተምርህ ሌላን ሰው እየዘከረ ነው፡፡ ካንተ ቀድመው ስለነበሩና በስኬት ማማ ላይ ጫፍ ስለደረሱ አንቱ ስለተባሉ ሰዎች ማወቅ ክፋት ባይኖረውም ስለራስህ እንድታውቅና ራስህን ፈልገህ እንድታገኝ የሚያደርግህ አዋቂ ግን ብዙም አታገኝም፡፡ ለምን ብትለኝ አብዛኛው አስተማሪህ፣ ወላጅህ፣ አዋቂ ነው የምትለው የዘመንህ ምሁር ተብዬው ራሱን ፈልጎ ያገኘ ሳይሆን ሌሎችን በመምሰል ኑሮውን የሚገፋ ነው፡፡ ራሱን በመከተል ሳይሆን ሌሎችን በመከተል ቁልቁል የሚወርድ ነው ዙሪያህን የከበበህ፡፡ ተከበሃልና ወዳጄ ራስህን በመሆን የቆረጣ ስልት አፈትልከህ ውጣ!!

‹‹ሌሎችን መሆንና መምሰል›› ዓለም ሁልጊዜ የሚሰብከን ከንቱ ስብከቱ ነው፡፡ አንተ ራስህን ለመሆን በምትሞክርበት ቅፅበት እንኳን የቅርብህ ሰው አዲስ ስም እየሠጠህ፣ አቃቂር እያወጣብህ ከራስህ ጋር እንድትጠፋፋ ይገፋፋሃል፡፡ አንተ ሁሉን ችለህ፣ ከራስህ ጋር ያለውን ውጊያ ተቋቁመህ ከአንተነትህ ጋር ትግል ብትገጥምም ከማህበራዊ ኑሮህ ያገሉሃል፡፡ ሶቅራጦስ ሰው ከራሱ ጋር ይተዋወቅ ዘንድ ‹‹ራስህን እወቅ!›› በማለቱ ነው መርዝ ግተው የገደሉት፡፡ የመንጋው ፍርድ ይፈታተንሃል፡፡ የቅርብ ሰውህ አስተያየት ከመንገድህ እንድትዛነፍ ያባብልሃል፡፡ ተፅዕኖውና ግፊቱ ከባድ ነው፡፡ እሱን መቋቋም የሚችል ጥንካሬ ከሌለህ እነሱ በጠፉበት ዓለም ያጠፉሃል፤ በሚተራመሱበት ምድር ትተራመሳለህ፡፡ እህ!

አንተ ግን ከራስህ ጋር ሙግትና ትግል ከጀመርክ፤ እመነኝ ራስህን ፈልገህ ለማግኘት መንገድ ጀምረሃል ማለት ነው፡፡ ራሱን ማወቅ የሚታትር ሰው የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሰውነቱን ፈልጎ ያገኛል፡፡ ሰውነቱን ያገኘም ሰው ዕውቀቱና ጥበቡ ለመላው የሰው ልጅ የሚተርፍ ይሆናል፡፡ ‹‹ራስን መሆን!›› ራስህን ለራስህ የምትሸልመው ታላቅ ኒሻን ነው፡፡ ራስህን መሆን ማለት ትክክለኛ ሰው መሆን ማለት ነው፡፡ ሰው የተፈጠረበትን የሚያውቀው እውነተኛ ሰው መሆን ሲችል ብቻ ነው፡፡ ሰው የሆነ ሰው ሰውን ሁሉ ይወዳል፡፡ ምክንያቱም ሰውነት ሰብዓዊነት ከጎደለው ሰው መምሰል እንጂ ሰው መሆን የታል፡፡ ሰው የሆኑ ነገር ግን ሰብዓዊ ያልሆኑ (Humans without humanity) ብዙ ሰዎች ዓለማችን አጣበዋታልና፡፡

ትልቁ ጥያቄ ሰው ራሱን እንዴት ያገኛል የሚለው ነው፡፡ ከዛስ ራሱን ፈልጎ ካገኘ በኋላ እንዴትስ ነው ትክክለኛ ሰው የሚሆነው የሚለው ጥያቄ የብዙዎቻችን ጥያቄ ነው፡፡ ብዙ ምሁራን ራስን ማግኘት የሚቻለው ከራስ ጋር በፀጥታ በመነጋገር ነው ይላሉ፡፡ ይሄን በተመለከተ ብዙ ሃሳቦች ከተለያዩ ምሁራን ተንፀባርቀዋል፤ አሁንም እየተንፀባረቁ ነው፡፡ ብዙዎች ሰው ራሱን ፈልጎ ለማግኘትና ራሱን ለመሆን ይሄ መንገድ ያዋጣል እያሉ የራሳቸውን ጥቆማ በመፅሐፎቻቸው፣ በንግግሮቻቸው፣ በስብከቶቻቸው ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ፍልስፍና ግን እንደሩቅ ምስራቃውያኑ የተካነበትና የረቀቀበት የለም፡፡ እንደአብነት ለመጥቀስ ያህል ከጥንታውያኑ ፈላስፎች አንዱ ከሆነው ከቡድሃ ጀምሮ እነኦሾ ስለውስጣዊ ንግግርና ተመስጦ ብዙ ብለዋል፡፡ በዘመናችንም ታዋቂ የሆነው ጀርመን የተወለደውና የካናዳ ዜግነት ያለው ኤካርት ቶሌም ‹‹ዝምታ/ፀጥታ ይናገራል›› የሚል ትርጉም በያዘው “stillness speaks” ተብሎ በሚታወቀው መፅሐፉ ራስን ፈልጎ በማግኘት ውስጣዊ ሠላምን ማረጋገጥ እንደሚቻል በመፅሐፉ ይጠቅሳል፡፡

በዚህ መፅሐፉ በመግቢያው ላይ ከጠቀሰው ሃሳቡ ጥቂት ሃሳብ ጨልፈን እንዋስ እስቲ፡-

‹‹እውነተኛ መንፈሳዊ መምህር ምንም ነገር አይጨምርልህም፤ የስነምግባር መመሪያዎችንም አያሸክምህም፤ አዲስ መረጃም አይሠጥህም፡፡ የሚያደርግልህ ነገር ቢኖር፤ … አንተ ከራስህ ጋር የተለያየህበትንና የተጠፋፋህበትን ጉዳይ ካንተ እንዲወገድና ከራስህ ጋር በጥልቀትና በርቅቀት እንድትገናኝ ብቻ ይረዳሃል፡፡ አንተ ስለራስህ ያለህ ዕውቀትና ስለትክክለኛው ማንነትህ የተዛባውን አመለካከትህን እንድታሻሽል መንገድ ያሳይሃል፡፡›› ይለናል፡፡

እውነት ነው! ‹‹ለሰው አዲስ ነገር አትነግረውም፤ ታስታውሰዋለህ እንጂ!›› እንደሚባለው መልካም መምህር የውስጥህን እውነት ያነቃቃል እንጂ በዓለም ላይ የሌለ አዲስ ነገር አያስተምርህም፡፡ ብልህ መምህር ሃሳብ እያስነሳ በሃሳብህ እንድትጠልቅና እንድትረቅ የዕውቀት ክብሪት ይጭራል እንጂ ተሠርቶ ያለቀለት የመረጃ መዓትን አይቆልልብህም፡፡

ዳሩ ምን ዋጋ አለው! የዓለም መምህር ካንተ ውጪ ስላለው ዓለም መረጃ እየጫነ አዕምሮህን ይደፍነዋል፡፡ ስለራስህ ዓለም ስለውስጥህ ሕይወት ታውቅ ዘንድ አያነቃህም፣ ልብህን አያነሳሳውም፤ አዕምሮህንም አያነቃቃውም፡፡ ብልህና ጥበበኛ መምህር ፈልጎ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ምክንያቱም ራሱን ፈልጎ ያላገኘ ሰው በሞላበት ዓለም ውስጥ ከራስህ ጋር እንድትገናኝ የሚያግዝህ አጋር ማግኘት ብርቅ ነው፡፡ ራሱን የሆነ ሰው ብቻ ነው ለሌሎች ራሳቸውን ይሆኑ ዘንድ መንገድ ሊያሳይ የሚችለው፡፡ ለዚህ ነው ብዙ ምሁራንና ሰባኪዎች ምክራቸውና ስብከታቸው ከንቱ ሆኖ የሚቀረው፡፡ ምክንያቱም የሚሉትን ሆነው ስለማይኖሩት ፍሬ ሊያፈራ አልቻለም፡፡ ሰሚውም ቢሆን ለመሆን ስለማይሞክርና በተግባር ሆኖ ለመገኘት አቅም ስለሚያጣ ይሰማል እንጂ አያዳምጥም፤ መሆንን ይመኛል እንጂ አይሆንም፡፡

ዕድለኞች ሆነን እውነተኛ መምህር ብናገኝ እንኳን መንገድ ይጠቁመን ይሆን እንጂ እኛን ሆኖ አይተውንም፡፡ መምህሩ ይመክርህ ይሆናል እንጂ ከስህተትህ ዋሻ፤ ከአመለካከትህ ጢሻ ጎትቶ አያወጣህም፡፡ የውስጥህን ሠላም የምታረጋግጠው አንተና አንተ ብቻ ነህ፡፡ ያንተ ሠላም መሆን ለሌላውም ሠላም ይሠጣል፡፡ ዓለማችን የምትዋከበው፣ ረብሻው፣ ኳኳታው፣ ትርምሱ፣ ጩኸቱ፣ መጠላለፉ፣ መረገጋገጡ፣ መገዳደሉ፣ ጥግ ለጥግ ሆኖ መጠዛጠዙ የበዛው ሠላማቸውን የተነጠቁ ሰዎች ስለሞሉ ነው፡፡ ሠላሙን ያጣ ሰው ለራሱም፣ ለሌላውም፣ ለሐገሩም፣ ለዓለምም አደጋ ነው፡፡ ከጠፋህበት ዓለም ተመልሰህ ወደትክክለኛው የማንነት ዓለምህ የምትመለሰው በራስህ ፍለጋ ነው፡፡ የተዘጋውን አንተነትህን፣ ዓለሙ የከረቸመብህን ቁልፍ ከፋፍተህ ራስህን የምታገኘው አንተው ራስህ ነህ፡፡ ዓለሙ እንዲቆልፍብህ የፈቀደው ሌላ ማንም ሳይሆን አንተው ራስህ ነህ፡፡ ስለዚህ ዘጊውም ከፋቹም አንተው ራስህ ነህና ተቆልፎበት ከቆየው አመለካከትህ ወጥተህ ከመከራህ የሚያድንህና ከጭንቀትህ የሚያረጋጋህን ውስጣዊ ሠላምህን ተጎናፀፍ፤ ራስህን በማሸነፍ ከፍ ከፍ በል፡፡

ኤካርት ቶሌ አሁንም በመፅሐፉ መግቢያ ይቀጥላል፡-

‹‹መንፈሳዊ መምህር ውስጣዊ ሠላምህን መግለጥ እንድትችል መንገድ ይጠቁምሃል፡፡›› ሲል ይገልፃል፡፡

እውነት ነው! ሠላም የሰው ልጅ የመጨረሻ የፍለጋው ውጤት ነው፡፡ ውስጣዊ ሠላምን መግለጥ ራስን ፈልጎና አውቆ የማግኘት ከፍታ ነው፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በብዙዎቹ መልዕክቱ መጨረሻ ላይ ‹‹የአዕምሮ ሠላም ይስጣችሁ›› የሚለው፡፡ የአዕምሮ ሠላም የሠላሞች ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ ሠላም የሌለው አዕምሮ የሚያፈልቀው ጥፋትን ብቻ ነው፡፡ የተረበሸ ማንነት ራሱንም አካባቢውን አልፎ ተርፎም ዓለሙን ይረብሻልና፡፡

ወዳጆች ሆይ….. ራሳችንን ፈልገን በማግኘት ውስጣዊ ሠላማችን እናረጋግጥ የዕለቱ መልዕክት ነው፡፡

ውስጣዊ ሠላም ሠላማዊ ዓለምን ይፈጥራል!

የአዕምሮ ሠላም ለሁላችን ይሁን!

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ!!

አዕምሮህን ከስሜትህ በላይ ጠንካራ እንዲሆን አሰልጥነው! እ.ብ.ይ========================================የሰው ልጅ በተፈጥሮው ስሜታዊ ነው፡፡ ሰው ምንም እንኳን ስሜታ...
22/12/2019

አዕምሮህን ከስሜትህ በላይ ጠንካራ እንዲሆን አሰልጥነው! እ.ብ.ይ
========================================
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ስሜታዊ ነው፡፡ ሰው ምንም እንኳን ስሜታዊ ተፈጥሮ ቢኖረውም ስሜታዊ ብቻ ግን አይደለም፡፡ ስሜቱን የሚገራበት፣ አላስፈላጊ የሆነ ደመነፍሱን አደብ የሚያስገዛበትና የሚቆጣጠርበት እንዲሁም አስቦ፣ አውጠንጥኖ፣ ግራ ቀኙን አወዳድሮና አመዛዝኖ፤ በደንብ አስተውሎ መወሰን እንዲችል የአዕምሮ ሃይል፣ የማሰብ ፀጋም ታድሎታል፡፡ ይሄን ፀጋውን የመጠቀም ፋንታ የሰውየው ድርሻ ነው፡፡ ሰው እንደአሳቢነቱ ስሜቱን እንዲመራ እንጂ በስሜቱ ብቻ እንዳይናጥ ራሱን ማብቃት ይጠበቅበታል፡፡ ራስን ማስተማርን የመሠለ ምን ነገር አለ! አዕምሮንና ውስጣዊ ሕይወትን ከማበልፀግ በላይ ታላቅ ብልፅግና ከወዴት ይገኛል! የትም የለም!

አንድ የመንገድ መሠረተ ልማት ካልታደሰ፣ በየጊዜው ካልተሻሻለ፣ ካልተጠገነ፣ ከጊዜው ጋር እንዲሄድ ተደርጎ ካልተስፋፋ ጥቅም እንደማይኖረው ሁሉ አዕምሮም ስሜትን እንዲያሸንፍ፣ ደመነፍስን እንዲገዛ ካልተለማመደ፣ በአዲስ ሃሳብ ካልሠለጠነ የስሜቱ ባሪያ ይሆናል፡፡ ሰው አዕምሮውን የስሜቱ አለቃ ማድረግ ካልቻለ በስሜቱ የሚነዳ ደመነፍሳዊ ብቻ ይሆናል፡፡ ይሄ ደግሞ ከእንስሳ እንዳይሻል ያደርገዋል፡፡ ለዚህ ነው ብዙዎች በስሜት ጀምረው በስሜት የሚጨርሱት፡፡ ለማሰቢያ ጊዜ የሌላቸው ሰዎች ለጥፋት ጊዜ ይተርፋቸዋል፡፡ በስንት ድካም አባቶቻቸው የመሰረቱትን ሐገርና አንድነት ለማፍረስ ይቸኩላሉ፣ ስንት የለፉበትን ትዳራቸውን ለመናድ ይጣደፋሉ፡፡ አብረው በደስታውም በሃዘኑም ያሳለፉትን ወገናቸውን ለመጥላትና ለማዋከብ ይክለፈለፋሉ፡፡ ስሜታቸውን የሚያቆሙበት፣ ደመነፍሳቸውን የሚቆጣጠሩበት ታኮ ስላልፈጠሩ በወደዱበት ስሜታቸው ይጠሉበታል፤ በአፈቀሩበት ልባቸው ይረግሙበታል፤ በአቀፉበት እጃቸው ያንቁበታል፡፡ ስሜታቸው እንደጎርፍ ሆኖ ወደየት እንደሚያጎርፋቸው አያውቁም፡፡ ማንና ምን እየነዳቸው እንደሆነ አይረዱም፡፡ የትናንት ወዳጃቸውን የዛሬ ጠላታቸው ያደርጉታል፡፡ አይ አለማሰብ! ማሰብ እየቻሉ መልካም ነገር አለማሰብ መረገም ነው!

በስሜቱ የሚጎተት፤ በደመነፍሱ የሚገፋ፣ ማንም እንዳሻው የሚነዳው ሰው ወደየት እንደሚሄድ አያውቅም፡፡ የሕይወቱ አቅጣጫ፣ የኑረቱ መንገድ የሚወሰነው ስሜቱ አጣድፎ በወሰደውና ሴረኛ አክቲቪስቱ ባነጎደው እንጂ እሱ አስቦና ተመራምሮ በደረሰበትና በመረጠው አይሄድም፡፡ ስሜታዊው ሰው ልክ እህቱን እንደወደደው እንደንጉስ ዳዊት ልጁ እንደአምኖን ስሜታዊ ፍቅር ‹‹ከወደድኩሽ ውድ ይልቅ የጠላሁሽ ጥል በለጠ›› እያለ ባፈቀረበት ልቡ ለመጥላት ይቸኩላል፡፡ ለመውደድ እንደጓጓው ለመሰልቸት ይጣደፋል፡፡ የዘመኑም ፍቅር እንዲሁ ነው፡፡ የት ይደርሳሉ የተባሉ በአጭር ሲቀጩ እያየን ነው፡፡ ትናንት በፍቅር እንዳልከነፉ ዛሬ ለመካሰስና ለመወነጃጀል አልፎም ተርፎ ለመገዳደል የሚፈላለጉ ቤት ይቁጠራቸው፡፡ የዚህ ሁሉ ምንጩ ግን በስሜት ጀምሮ በስሜት መጨረስ ነው፡፡ በአዕምሯው አስበው፤ በሕሊናቸው ወስነው የጀመሩ ግን በሃሳብ ቢለያዩም ለጠብ አይፈላለጉም፡፡ ልዩነታቸውን የውበታቸው ማድመቂያ፣ የአንድነታቸው ጌጥ እንጂ የጠባቸው ሰበብ አያደርጉትም፡፡

ስሜትና አዕምሮ የተባለ መፅሐፍ ስለስሜት ሲናገር እንዲህ ይላል፡-

‹‹እንደስሜት ሰውን ከፍና ዝቅ እያደረገ የሚንጥ ሃይል የለም፡፡››

እውነት ነው! ሰው የስሜቱ አገልጋይ ከሆነ በትንሹ ይበሳጫል፤ በትንሹ ይደሰታል፡፡ ለስሜት ቦታ ከሰጡትና ከታዘዙለት ሐይሉ ከባድ ነው፡፡ አንዴ ወደላይ፤ አንዴ ወደታች ይንጣል፡፡ መናጥ ብቻ አይደለም አንስቶ ያፈርጣል፤ መላልሶ ይጥላል፡፡ ከራስ ጋር ህዝብን ከህዝብ፣ ባልን ከሚስት፣ ወገንን ከወገን እያጣላ ከዓለሙም ጋር ያጋጫል፡፡ ሕዝብን እያለያየና ወገንን ከወገን እያጨራረሰ ያለው ይሄው የስሜት ማዕበል ነው፡፡ የስሜት ማዕበሉ ከተነሳ አዕምሮና ማሰብ ካላቆመው ሌላ ማቆሚያ የለውም፡፡ ፍሬኑ መላልሶ ማሰብ ነው፤ ማርሹ መረጋጋት ነው! በደመነፍሱ የሚዋከብ ሰው ልክ እንደብረት ድስት ሲጥዱት ይግላል፤ ሲያወርዱት ይቀዘቅዛል፡፡ አክቲቪስቱ በመራው ይመራል፣ ፖለቲከኛው ባዋከበው ይዋከባል፤ መንጋው በነዳው ይነዳል፡፡ እንዴት፣ ለምን፣ ማን፣ ምን ብሎ የሚጠይቅበትና የሚያስብበት ደቂቃ የለውም፡፡ አብሮ የኖረውን ወገኑን ጠላት አድርጎ ለማሰብ የአክቲቪስቱ ፕሮፓጋንዳ፣ የዘረኛው ፖለቲከኛ ቅስቀሳ ይበቃዋል፡፡ እንዳልተገራ ፈረስ የሥሜቱ ገርጋሪ፣ የጥፋት ተጠሪ ይሆናል፡፡ ሰው ስሜቱን ካልገራ በስሜቱ ተመርቶ ስህተትን ይሰራል፡፡ እየተንቀለቀለ የሚመጣበትን ስሜት ረጋ ብሎ አደብ ካላስገዛው በጥፋት መንገድ ቁልቁል ወደታች ይወርዳል፡፡ የሐጢዓት ቁልቁለት የሕይወት መንገዱ ይሆናል!

ስህተቱን ከፈፀመ በኋላ የሚያስብ ሰው የፈሰሰን ውሃ ለማፈስ እንደመሞከር ነው፡፡ ምናልባት ለወደፊቱ የሚማርበትና የሚያተርፈው ፀፀትን እንጂ ለአሁኑ ስህተቱ የሚጠቅመው አንዳች ነገር የለውም፡፡ ከመፍሰሱ በፊት ማሰብ፣ ከጥፋቱ በፊት ቆም ብሎ ነገሮችን በብዙ አቅጣጫ ማየት ሰውን ከጥፋቱ ይጠብቀዋል፡፡ አንድም ሰከንድ ቢሆን ሰው ለራሱ ማሰቢያ ጊዜ ከሰጠው ራሱን በራሱ ከስህተት ይታደጋል፡፡ ቻይናውያን ‹‹በአንድ የንዴት ጊዜ የሚደረግ ትዕግስት ከመቶ ሐዘኖች ያተርፋል›› የሚሉን ለዚህ አይደለ!!

ዛሬ ዛሬ በሐገራችን እየተስፋፉ ያሉ ስሜታዊነት የወለደው አጥፊነት ቆም ብሎ ካለማሰብ የመነጩ ናቸው፡፡ ጥቂት የሴራ ፖለቲከኞች፣ በሕዝብ ደም መነገድ የሚፈልጉ ሰውነታቸውን በዘነጉ አክቲቪስቶች ምክንያት ሰው በክፉዎች እየተገፋ በደራሽ ስሜቱ ይናጣል፤ ወገን በደመነፍሰኞች ይዋከባል፤ ሕዝብ ሰላሙን ያጣል፡፡ ብዙሃኑ በስሜት ማዕበል በመዋከቡ ለጥቂቶች ጥፋት እጅ ሠጥቷል፡፡ ጥቂቶቹ ክፉዎች ብዙሃኑን መልካሞች ማሸነፋቸው ይገርማል፡፡ አይ ጊዜ! አያሳየን የለ!

ወዳጆች ሆይ…. አዕምሯንን ከስሜታችን በላይ ጠንካራ እንዲሆን እናሰልጥነው፡፡ ለራሳችን ጊዜ እንስጥ፡፡ እንረጋጋ! መረጋጋት ለማሰብ ጊዜ ይሠጣል፡፡ ማሰብ ደግሞ ለማመዛዘን ይረዳል፡፡ ማመዛዘን አስተውሎ የመወሰን ምንጭ ነው፡፡ አስተውሎት የተሞላበት ውሳኔ ደግሞ ሁሉን የሚጠቅም እንጂ ለአንዱ ብቻ ቆሞ ሌላውን የሚጎዳ አይሆንም፡፡ አዕምሮ ተረጋግቶ ካሰበ ለበጎው ነገር ይሸነፋል፡፡ የተረጋጋ አዕምሮ እውነተኛ ሰውነትን ፈልጎ ያገኛል፡፡ እውነተኛ ሰውነትም ሌሎችን እንደራስ አድርጎ ማሰብ ነው! ይሄ አስተሳሰብ ደግም የፍቅር ዋልታ ነው፡፡ ፍቅር ደግሞ የአንድነትና የመስማማት ማገር ነው፡፡ አንድነትና መስማማትም የአዕምሮ ሰላምና ደህንነት ይሠጠናል፡፡ የአእምሮ ሠላምም ደስታን ያከናንበናል፡፡ አራት ነጥብ!

አዕምሯችንን እያሰለጠንን፣ ቆም ብለን እያሰብንና ስሜታችንን እያሸነፍን የክፉ ፖለቲከኞችንና የዘረኛ አክቲቪስቶችን ሴራ እናሽመድምድ የዕለቱ መልዕክት ነው!

ቸር ማሰብ ራስንም ሌላውንም በፍቅር ማሸነፍ ነው!

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ!

!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daniel Ary' nayoo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Daniel Ary' nayoo:

Share

Category