ZER photography

ZER photography Make video clip,film,photo ....

13/01/2023

ኢትዮጵያዊ መሆን መታደል ነው።🇪🇹🇪🇹🇪🇹

18/08/2022

ኢትዮጵያ መልካም በዓል ይሁንልን።

አንዱ የክረምት ገፀ በረከት እንደምናውቀው ምድራችንን በአረንጓዴ መሙላት ነው። እኔም ከሣቡኝ አረንጓዴ ነገሮች ክረምቱ ጀባ ካለን ጀባ አልኳችሁ።!
06/08/2022

አንዱ የክረምት ገፀ በረከት እንደምናውቀው ምድራችንን በአረንጓዴ መሙላት ነው። እኔም ከሣቡኝ አረንጓዴ ነገሮች ክረምቱ ጀባ ካለን ጀባ አልኳችሁ።!

እነዚህ አበባዎች ባልደራስ አካባቢ እሚገኘው ሮሚና ሬስቶራንት በር ላይ ያሉ አበባዎች ናቸው። በቤቱ ውስጥ ጥበቃነት  እሚሰራው ፦ ሙሴ የተባለው ወዳጄ ነው እሚንከባከባቸው።በጣም እሚገርመው ነ...
10/07/2022

እነዚህ አበባዎች ባልደራስ አካባቢ እሚገኘው ሮሚና ሬስቶራንት በር ላይ ያሉ አበባዎች ናቸው። በቤቱ ውስጥ ጥበቃነት እሚሰራው ፦ ሙሴ የተባለው ወዳጄ ነው እሚንከባከባቸው።በጣም እሚገርመው ነገር ምንም ተከፍሎት ወይንም ጥቅም ፈልጒ አደለም አበባዎቹን እሚንከባከበው እሱ ሁል ግዜም ከአበባዎቹ ጋር ጥሩ ግንኙነት ጥሩ መአዛቸውና ባህሪያቸውን ማወቅ ያስደስተዋል። ሙሴ ለሠጠኸኝ ምክርና አገልግሎት ከልብ በመነጨ ምስጋና አመሰግናለው።

ይቆለፍ ድንበሩ!!!ፍቅር ሠላም አለፈ ሰው ሰውን ጠለፈአንዱ አንዱን አንሳፈፈ ቀረፈ።ሰው ሰውን ሊበላ አሠፈሠፈሚዲያው ሰላም እደሌለን ለፈፈ።ሰዎች ከቤታቸው ጠፉያ በርሀ ያ ማእበል ክፉመቼም ለ...
03/06/2022

ይቆለፍ ድንበሩ!!!

ፍቅር ሠላም አለፈ
ሰው ሰውን ጠለፈ
አንዱ አንዱን አንሳፈፈ ቀረፈ።
ሰው ሰውን ሊበላ አሠፈሠፈ
ሚዲያው ሰላም እደሌለን ለፈፈ።

ሰዎች ከቤታቸው ጠፉ
ያ በርሀ ያ ማእበል ክፉ
መቼም ለማይሞላ ኑሮ (ልፉ)2
በማያልቀው ጉዞ ልባቸውን ትፉ።
ባለ ቁርሾች ተስፋፉ
በእብሪት ልባቸውን ነፉ።

ደሞ እሱን ብሎ ሰላም ፍቅር አሣላፊ
ደሞ እሱን ብሎ አክትቪስት ይሄ ለፍላፊ።
ፖለቲካው ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ
ሰው ሰውን በልቶ ሁሌ አሸናፊ
ሁሌ ከፊት ተሠላፊ።

ሀይ ባይ ሠው ጠፋ
ኑሮው ከፋ
የንቡ ቀፎ ባዶውን ቀረ ወቶ በተስፋ
አሥታራቂም ጠፋ።
አስመሣዩ በተንኮል ገፋ
እርግጥ
አገር ወዳድም አልጠፋ!
በቃላት እሚያዳፋ!
ተንኮል ጥላቻን እሚገፋ!
ድንበርን ከድንበር እሚሰፋ።

ነይ ሠላምን ዘምሪ ወፌ
ከሁሉ እንዳልቀር ተርፌ
ፍቅርን ርቄ እንዳልቀር ተንከርፍፌ
እንዳልቀር ተቆልፌ
ሠውም እንዳይለኝ ወፈፌ።

ፍቅርና ሠላምን አቅቶኝ ማለፍ
እንደሌላው እንደሌለው አስቤ ትርፍ
መክፈቻውን ሳልጠይቅ ቁልፍ
እንዳልልም እልፋን እልፍ።

ፍቅርና ሠላምን ገምዶና ጠልፎ
ለእንስሣም ይሠጥ ተርፎ
ከሰው ወደ ሠው እሚለውን አልፎ
በመንጋው ይሙላ የንቡም ባዶ ቀፎ
ድንበሩም ይዘጋ ይቅር ተቆልፎ!!!!

ሠውም ካፉ ጥሩ ቃልና ቀና ሀሳብ ካላወጣ ልክ እንደ ድንበሩ አንደበቱ ይቆለፍ። አብሶ በምላስ እየደለሉ አገርን ከፋፍሎና አንዱን ካንዱ አባልቶ በልጦና ከፍ ብሎ ለመታየት ለምትፈልጉ ያገራችን ሹማምንቶች ይሁንልኝ!።!።!........

በህይወታችን ስንኖር በብዙ እንመኛለን ተመኝተናልም።በትንሹ አጥተናል በብዙም አትርፈናል።!
18/05/2022

በህይወታችን ስንኖር በብዙ እንመኛለን ተመኝተናልም።በትንሹ አጥተናል በብዙም አትርፈናል።!

15/04/2022
በፍቅር እንጂ.... በፀብማ!!ኢትዮጵያ ሀገሬ እኛ ልጆችሽ እስኪ እንቁም ከፊትሽምን አረክሽልኝ ብሎ ማነው እሚወቅስሽየሰው ልጅ ሲባል አጥፊ ነውናከስህተቱ ተምሮ እስኪሰጥሽ ምስጋናክብርሽ በአለ...
28/02/2022

በፍቅር እንጂ.... በፀብማ!!

ኢትዮጵያ ሀገሬ
እኛ ልጆችሽ እስኪ እንቁም ከፊትሽ
ምን አረክሽልኝ ብሎ ማነው እሚወቅስሽ
የሰው ልጅ ሲባል አጥፊ ነውና
ከስህተቱ ተምሮ እስኪሰጥሽ ምስጋና
ክብርሽ በአለም ላይ ይታይ
ያቃጭል ድምፅሽም ይሰማ
እስኪገባው ያለሽ ክብር ሞገስ ግርማ።

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ምን ማለት
ብለህም አጠይቀኝ እኔም ጠልቄ አላቃት!።
ነገር ግን በትንሹ ልንገርህ
እኔ እማውቃትን ታህል ላጫውትህ
አባቶቼ ያሉኝን በታሪክ
እናት ነችና ሀገርክ
ብትሰበር የለህ ምትክ።
ኢትዮጵያ ማለት በቃ ኢትዮጵያ ናት
ከምንም ዘርፍ ከፋፍለህ እማታያት
በቃ ኢትዮጵያዊነትህን አትመርምራት
በልብህ ቀብረህ አኑራት
እንዲያው እየኮራህባት
ተማፀንላት ጥሩ መና
አምላክህን በልመና።

ትርጉሙ ነው ለካ
በሀገርክ ኩራ ተመካ።!!

ለሀገርህ ሥጥ ያለህን
ሠላም ካለክ ሰላምን
ፍቅር ካለክ ፍቅርህን።

በጠብ ለመጣብክ
ዱላህን ይዘህ ፈትለክ
የጦርህን ጫፍ ሣላት
ጋሻህን ይዘህ ዝመት
አሊያ አርግላት ስለት
ለምቶደው ታቦት።

ካንተ በላይ ያስባት እሡ
ከቀናት በለሡ
ይምጣልን በነጭ ፈረሡ
እንዳድዋው እንደለተ ቀኑ
ዛሬም ነገም ወደኛ ኑ ኑ !።

አሁንም እንደ ድሮው
በኢትዮጵያ በሀገሬ ላይ በዝቶል አንባጒሮው
ብረቱን አንሥቶ
ጠብ መንጃውም በዝቶ
አሁንም ሊገላት
ወደታች ሊጥላት
ይመኛል ሊበላት ሊያጣጥማት
እንዲያው ሀገሬው ጅል መስሎት።

እህ ልጆ መቼ ሠንፎለት
መቼ ደክሞለት
መቼሥ ጆሮው ሠምቶት
ቀድሞው ሠልቅጦት
የበሰበሰን ቆሻሻ ካልነኩት መች ይሸትና
ካላደፈረሱትስ መች ይጠራና
ሀበሻም እንዲያው ነውና
ካልነኩት አይነካ
ጠላት ፊት ፊቱ አይፈካ
አሞተ መራሩ እንዳይበላህ ሆላ
ለፍቅር ለፀብ አለው ቆንጆ መላ።

ዛዲያ ይህ ሁሉ ሲሆን
አልሠምቶም ወይ(2)
እንግዳው ላሣይ በጦር በሜዳው ታንተው ፊት ልታይ
ዘውድዬ ስንቁን ሸክፊ በይ
ለናት ሀገሬ ዘምቼ
ጠላቴን በጣጥሼ
በበላሁት ቊራርሼ
አልተወውም ቀምሼ
እንዲያው ነካክቼ
እጅ እጅ አሥብዬ
ብረቱን አሥጥዬ
ባንቺ በናቴ አስምዬ
ብሎ እንዲል ኢ..ት..ዮ..ጵያን
በፍቅር እንጂ በፀብማ ፈራን።

እስኪ ጥበብን ከኤልያስ እንዝረፈው እንጋራው እንጠይቀው። እያንዳንዱ የኤላ  ቃላት አደለም ፅፎት ሲናገረው ለጆሮ ሙሉ ናቸው። አብረን በምንማርበት ጊዜ የምር ሁላችንንም ያስገርመን ነበር። ስለ...
11/02/2022

እስኪ ጥበብን ከኤልያስ እንዝረፈው እንጋራው እንጠይቀው። እያንዳንዱ የኤላ ቃላት አደለም ፅፎት ሲናገረው ለጆሮ ሙሉ ናቸው። አብረን በምንማርበት ጊዜ የምር ሁላችንንም ያስገርመን ነበር። ስለ ትያትር የነበረው እውቀት በመመረቂያችን ግዜ ባቀረብነው የሙሉ ሰዐት ትያትር ላይ ያሳየን ትልቅ ችሎታውና የነበረው አስተዋፅኦ ለየት ያለ ነበር። ይህም በድርሰትና በአዘጋጅነት ለየት ባለ መልኩ የጎንደርን የጋብቻ ስነሥርዐት ቱፊታዊነቱን በጠበቀ መልኩ ቆንጆ አርጎ ፅፎ ሸጋ አርጎ አጋብቶብናል። ይህ ስራ አሁንም በሁላችንም ልብ ውስጥ አለ።
አሁን ላይ በርግጠኝነት ማውራት እምችለው ከርተን ኮል ለየት ባለ መልክና ይዘት ትምህርቶቹን አሻሽሎና አበልፅጎ ይዞ መቶል። እድሉ አያምልጣቹ።

08/02/2022

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ZER photography posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category