Hulu Media

Hulu Media ...
(5)

26/01/2026
10/11/2025
07/11/2025

“እርሱ ደሙን አፍስሶልናል ስለዚህ ሌላ ደም መፍሰስ የለበትም!”

"በክርስትናችን በሃይማኖታችን መገደላችን የሚቆመው መቼ ነው? ነፃነት እንፈልጋለን:: የሰው ልጆች ደም በከንቱ መፍሰስ መቆም አለበት:: ይኼ ፖለቲካ አይደለም:: ሰላም መሻት ፣ ዕረፍት መፈለግ ፣ አንሙት ማለት ፖለቲካ ሳይሆን ሰብአዊ መብት ነው:: ሰው መሆን ነው:: ደከመን:: ብዙ ጊዜ ሰማን:: እናንተም በእኛ ፈረዳችሁብን:: እናንተም ወቀሳችሁን:: እውነት አላችሁ::
ግን ለማን ነው የምንነግረው ይኼንን? ማን ነው የሚሰማን ይኼንን? ማን ነው የሚያቆመው ይኼንን?

ተለማመድነው እኮ:: ስንቶቻችን ስናልቅ ነው የሚቆመው? ይብቃ:: ሕዝባችን ዕረፍት ይፈልጋል:: ሞት ሰለቸን በቃን:: ደም መፍሰስ ሰለቸን:: ይበቃናል:: ምድሪቷ ዕረፍት ያስፈልጋታል:: ሕዝቡ ዕረፍት ያስፈልገዋል:: ስለ እኛ ደም ፈሰሰ እኮ:: በእርሱ ቁስል ተፈወስን እኮ:: ሌላ ደም አያስፈልግም:: መከራችን እንዲያበቃ ጸልዩ"

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሊቀ ጳጳስ
ጥቅምት 27 2018 ዓ.ም. የተናገሩት
የብፁዕነትዎ በረከት ይደርብን::

04/11/2025

ይኼንን ጽሑፍ ቁጭ ብለህ እያነበብህ ያለኸው በዚህ ሰዓት ምሥራቅ አርሲ ገጠር ውስጥ ስላልተገኘህ ብቻ ነው:: በዚህች ቅጽበት በሥጋት ውስጥ ሆነው "ከአሁን አሁን ምን ይመጣብን ይሆን?" እያሉ ያሉ የኦሮሚያ ምእመናን ቁጥራቸው ብዙ ነው:: የተገደሉትን ተናግረን ሳናበቃ አሁን ደግሞ ሌላ ቦታ ብዙኃን እንደተገደሉ እየሰማን ነው::

ሰሞኑን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ሔሮድስ ስላሳደዳት እመቤታችን "ሰቆቃወ ድንግል" እያልን እያዘንን ነው:: ከሰይፍ ልጅዋን ማስጣል ያልቻለች የአርሲዋን እናትስ እንዴት ዝም እንበላት? ይህንን የማያቆም ሞት ዜና ሰምተን ወደ ጉሮሮአችን የሚወርድ ምግብና መጠጥ የምንተኛውም እንቅልፍ የለም:: የእነርሱ ሞት የእኛ ሞት ነው:: የእነርሱ መቁሰል የእኛ ቁስል ነው:: የቦታ ለውጥ እንጂ በእነርሱ የደረሰው በእኛም ሊደርስ ይችላል::

ቤተ ክርስቲያን ምሕላ እንድታውጅ ፣ ለተሠዉት ተገቢውን ክብር እና ጸሎተ ፍትሐት እንድታደርግ እንጠብቃለን:: ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ቦታ የንጹሐን ደም ዳግመኛ እንዳይፈስስ እንደ ራሔል ዕንባዋን የምትረጭበት ጊዜ አሁን ነው::

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ትኩረት ያልሠጠውን ችግር ሌላ አካል ሊጨነቅበት አይችልም:: ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደራዊ መዋቅርዋ መንግሥት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ በሙሉ ትኩረት የምትሠራበት ጊዜም አሁን ነው:: ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ዓይነት ጊዜ የሚያሳየው ምላሽ ከሌለ ሌላ ቀን ቢጣራ የማይሰማውን ቤተ ክርስቲያን አልባ ክርስቲያን በራሱ ላይ ይፈጥራል:: ሐዋርያዊትዋ ቤተ ክርስቲያንም በክህነት የማትመራ የመሆን አደጋ ይገጥማታል:: ክህነት ከሌለ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንም ምሥጢራትም የሉም::

ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንም ይህንን ጊዜ ለመካሰስ ፣ አባቶችን ለመሳደብ ፣ አንዱ ሌላውን ለማስጠቆርና ለመናቆር ሳይሆን ለጸሎት ለምሕላና ለሰብአዊ ሥራና መሬት ላይ ቢወርዱ ችግሮችን የሚፈቱ ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ በትብብር ለመሥራት ምክንያት ብናደርገው የተሻለ ነገር ማምጣት እንችላለን::

የሌላ እምነት ተከታዮች ሆነው ይህ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያውያን ላይ የተቃጣ ጥቃት ብለው ጉዳዩን በተቋምም በግልም ያወገዙ ሰዎችን እናከብራለን:: "ይበላችሁ" ብለው የተሳለቁትን እና በክፉ ቀን ክፋታቸውን ላሳዩን ደግሞ እውነተኛ ማንነታቸውን ስላሳዩን እያመሰገንን "አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ “እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ፡” ያሉአትን" ብለን ለሰማያዊው ዳኛ ሠጥተናቸዋል:: መዝ. 137:7



23/10/2025

ቤተሰብ🫂

በ2025 Best sport informative content በሚል እጩ ሆኛለው እናም ውድ ቤተሰቦቼ ከስር የጠቀመጠው ሊንክ በመጫን እየገባቹ ምረጡኝ አመሰግናለው 🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tca2025.com/category/21

Address

Ethiopian
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hulu Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share