Awramba Times

Awramba Times Awramba Times is an online media outlet providing latest news and analysis about Ethiopia & the horn
(1)

ኢህአፓ ትግራይን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት ያወጣቸው ሁለት ተቃራኒ አቋሞች ውዝግብ ፈጥረዋል!-----አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] -  የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ ዛ...
21/07/2026

ኢህአፓ ትግራይን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት ያወጣቸው ሁለት ተቃራኒ አቋሞች ውዝግብ ፈጥረዋል!
-----

አውራምባ ታይምስ [አዲስ አበባ] - የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ ገዥው የብልፅግና ፓርቲ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ዋና መንፈስ በመጣስ የትግራይን ሕዝብ እንደገና ወደ ዳግም አውዳሚ ጦርነት ለመክተት ተግቶ እየሠራ ነው ሲል ክስ ሰንዝሯል። የፌደራል መንግሥት የትግራይን ሕዝብ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ፣ ነዳጅ፣ በጀት እና መሠረታዊ አገልግሎቶችን በመከልከል በ“ድምፅ አልባ ከበባ” ውስጥ አቆይቶታል ያለው ኢሕአፓ፣ አሁን ደግሞ ሕግ ማስከበር በሚል ሽፋን አዲስ ጦርነት ለመክፈት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እያካሄደ ነው ሲል ከሷል።

ይህ የኢህአፓ መግለጫ ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ መዋሉን ተከትሎ በትግራይ ልሂቃን ዘንድ የተወሰነ ድጋፍ ቢያስገኝለትም፣ በሌሎች የክልሉ ልሂቃን ዘንድ ግን ፓርቲው ቋሚ አቋም የሌለውና "ጊዜያዊ የፖለቲካ ሙቀትን ብቻ አስልቶ የሚራመድ" የሚል ትችትን አስተናግዷል። እነዚህ ተቺዎች ለዚህ እንደ ምክንያት የሚያነሱት ፓርቲው ከአምስት አመት በፊት ጦርነቱ ሲጀመር የያዘውን አቋም በዋቢነት በማንሳት ነው።

የአገር መከላከያ ሰራዊት በህዳር 19/2013 ዓ.ም መቐለን ሲቆጣጠር ኢህአፓ ባስተላለፈው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት፣ "ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ታላቅ ተጋድሎ ፈጽሞ የጁንታው ቡድን ዋነኛ ምሽግ የሆነችውን መቐለ ከተማ መቆጣጠሩን ስንሰማ ደስታችን ወደር አልባ ሆኗል" ማለቱ ይታወሳል። እነዚህ ተቺዎች ይህንኑ የፓርቲው የቀደመ አቋም በማስታወስ አሁን ያራመደው አቋምስ በጊዜያዊ የፖለቲካ ሙቀት ያልተጋረደ ቋሚ አቋም መሆኑን እንዴት ማመን ይቻላል ሲሉ ጠይቀዋል።

21/07/2026

ንዶ/ር ደብረፅዮን ፊት ንፊት ዝወቐሳ ኣዶ!
-------
እቲ መንእሰይ ኣሚኑሉ እዩ ክጋደል ዘለዎ። ኣግዲድካ ክኾን የብሉን። ኣሽንባይ ኣግዲድካ ተጋደል ክትብሎ፣ ኣግዲድካ መዓር ብላዕ እንተይልካዮ እኳስ ፍቓደኛ ኣይኸውንን።
ናብ መንግስታዊ ሓላፍነት ድማ መናእሰያት ይምፅኡ፣ የብርዩኹም።

11/07/2026

የደብረጽዮንና የአብይ የአራት ሰአታት ውይይት
----------
ብዙዎቹ የህወሓት መሪዎች ጓደኞቼ ናቸው። እናም በሚዲያ ቃለምልልስ ላይ ስነሱ ስጠየቅ ክፉ ላለመናገር እጠነቀቃለሁ።
ዛሬ ግን አንድ ነገር ልንገራችሁ። ቅድም ጌታቸው የጠቀሰው ሰው (ዶ/ር ደብረጽዮን መሆናቸው ልብ ይሏል) እኔ ባለሁበት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለብቻቸው እጅ ለእጅ ተያይዘው ለአራት ሰአታት የፈጀ የእግር ጉዞ እያደረጉ ሰፊ ውይይት አድርገው ነበር ከዛ በኋላ እኔና ዶ/ር ደብረጽዮን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ውይይት አደረግን። ከዛ ምን ተፈጠረ?

ዝርዝሩን ከአቶ ዘሪሁን ተሾመ አንደበት!

10/07/2026

ኮነ ኢሉ ናይ ስድራ መለስ ሹም ንኽጠፍእ ዝገብር ዘሎ ጌታቸው ኣሰፋ እዩ። እዙይ ድማ መለስ ብሂወት እናሃለወ ዝተጀመረ ናይ 20 ዓመት ፕሮጀክት እዩ። ካብ ጌታቸው ብተወሳኺ ፈትለወርቅ ብ1979 ዓ.ም ገምጊሙኒ ነይሩ ኢላ ኣይትፈትዎን። ደብረፅዮን እውን ብ1993 ዓ.ም ናብ ማይጨው ደብርዩኒ ብዝብል ፅልኣት ኣለዎ!

-----

ሙሉእ ትሕዝቶ ናይቲ ኣብ ላንዳ ሪፖርት ዝወፀ ቃለመሕትት ንምክትታል ሊንክ ኣብ ኮመንት ተቐሚጡ ኣሎ።

ፈትለወርቅ ዲፕሎማሲ ምን እንደሆነ አልገባትም ስትልሰምሃል መለስ ገለጸች------አውራምባ ታይምስ [መቐለ] - የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ልጅ፣ ሰምሃል መለስ ዜናዊ በቅርቡ...
04/07/2026

ፈትለወርቅ ዲፕሎማሲ ምን እንደሆነ አልገባትም ስትል
ሰምሃል መለስ ገለጸች
------

አውራምባ ታይምስ [መቐለ] - የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ልጅ፣ ሰምሃል መለስ ዜናዊ በቅርቡ በትግራይ የወጣውን አዲስ አዋጅ "የደርግን ስርአት የሚያስታውስ አዋጅ" ስትል የሰላ ትችት አቀረበች።

ከ #ትግሃት ሚዲያ ጋር በቅርቡ ቃለምልልስ ያካሄደችው ሰምሃል መለስ፣ አዲሱ አዋጅ ህግ በሚያውቁ ሰዎች ይቅርና ማንበብና መጻፍ በሚችሉ ሰዎች እንኳን ተጽፏል ብላ ለማመን እንደምትቸገር ገልጻ "ብዙ ችግር ያለበት አዋጅ ነው፤ ሌላው ቀርቶ ሀሜትን እንኳን የማይፈቅድ የደርግ ዘመን ህግ ነው" ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።

የህወሓት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ያነሷቸውን አስተያየቶች በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላት ሰምሀል፣ የፈትለወርቅ መግለጫ መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንዴት እንደሚታረም የመፍትሄ አቅጣጫ ከማቅረብ ይልቅ የሷና የቡድኗን ስልጣን ማጠናከርን ብቻ ታሳቢ ያደረገ አሰልቺ ዲስኩር ስትል ገልጻዋለች። አሁን ያለው የአለም ሁኔታም ሆነ ዲፕሎማሲ እንዴት እንደሚሰራ ፈትለወርቅ ጨርሶ አልገባትም ስትል የምትሟገተው ሰምሃል፣ ዲፕሎማሲ ማለት ለሚወጡብህ የተቃውሞ መግለጫዎች መልስ መስጠት ማለት አይደለም ከዛ ይልቅ መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ተገንዝቦ የማሻሻያ እርምጃዎችን ይዞ መቅረብ ነው ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።

ቀደም ባሉ ጊዜያት በህወሓት ዙሪያ ብዙ ምሁርና አሰላሳይ ልሂቅ ነበር የምትለው ሰምሃል አሁን ግን ያ ሁሉ አቅም ተበትኖ ፓርቲው እዚህ ደረጃ ላይ ደርሶ ማየት እንደሚያሳፍራት በቁጭት ገልጻለች።

የትግራይ ወጣት ክልሉን ለቆ እንዳይወጣ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግበት ነው ተባለ------አውራምባ ታይምስ [መቐለ] - የትግራይ ወጣት ክልሉን ጥሎ እንዳይሰደድና እንዳይፈናቀል ጥብቅ ቁጥጥር ማድረ...
30/06/2026

የትግራይ ወጣት ክልሉን ለቆ እንዳይወጣ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግበት ነው ተባለ
------
አውራምባ ታይምስ [መቐለ] - የትግራይ ወጣት ክልሉን ጥሎ እንዳይሰደድና እንዳይፈናቀል ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በሱ ዙሪያ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በቅርቡ እንደ አዲስ በተዋቀረውና የህጋዊነትና የቅቡልነት ጥያቄ እየቀረበበት ባለው የዶ/ር ደብረጽዮን ካቢኔ ውስጥ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ሆነው የተመደቡት ይሕደጎ ስዩም ዛሬ በመቐለ ከተማ በተዘጋጀ አንድ መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ ወጣቱ ትውልድ ክልሉን ለቆ እየወጣ ያለው በራሱ ፍላጎት ሳይሆን "የውስጥና የውጭ ጠላቶች" ሲሉ በጠሯቸው አካላት ሴራ መሆኑን በመግለጽ ወጣቱ በክልሉ ሰርቶ ራሱንና ሀገሩን መለወጥ እየቻለ፣ አሁን በሚታየው መልኩ እንዲሰደድና እንዲፈናቀል እየተደረገ ያለው በተቀናጀ ሴራ በመሆኑ በቅርቡ መፍትሄ ያገኛል ብለዋል።

"በውስጥና በውጭ ያሉ ጠላቶች ሆንብለው የትግራይን ህዝብ ለማሸበር አልመው 'ጦርነት ሊነሳ ነው' የሚል የሀሰት ወሬ እየነዙ፣ ወጣቱ ከሀገሩ እንዲወጣና ለህገ-ወጥ ስደት እንዲጋለጥ ተደርጓል" ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ይህንን ሴራ ጥብቅ ክትትል አድርጎ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ከሌሎች የሚመለከታቸው አጋር የጸጥታ አካላት ጋር በተቀናጀ ሁኔታ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

የአሜሪካ መንግስትና የአውሮፖ ህብረትን ጨምሮ በርካታ አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማትና ሚዲያዎች ለወጣቱ መሰደድ ምክንያት እየሆነ ያለውን አስገዳጅ ወታደራዊ አፈሳ እንዲቆም በርካታ ይፋዊ መግለጫዎችን በማውጣት ቢያወግዙም በዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራውና ራሱን "ክልላዊ መንግስት" ብሎ የሚጠራው አካል ግን የግዳጅ አፈሳውን ፊታቸውን ጭንብል በለበሱ የጸጥታ አካላትም ጭምር እየታገዘ በሆቴሎች፣ በአብያተክርስቲያናት፣ በተለያዩ የመዝናኛ ስፍራዎች አጠናክሮ መቀጠሉን በየቀኑ በማህበራዊ ሚዲያና በመደበኛ ሚዲያ በስፋት እየተሰራጩ ያሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ያረጋግጣሉ።

29/06/2026

"የፕሪቶሪያውን ስምምነት የፈረምን ሰዎች 'ክህደት ፈጽማችኋል' በሚል እንድንረሸን በህወሓት ስራ አስፈጻሚ ሐሳብ ቀርቦ ነበር። የፈረምነው ሰነድም ተቀዳዶ ይጣል ተብሎ ነበር"

ሌ/ጄነራል ጻድቃን ገብረተንሳይ

23/06/2026

"ኣብቲ ሽዑ እዋን ጌታቸው ኣሰፋ ዝኾነ ኣጋጣሚ እንተረኺቡ ክርሽነኒ እዩ ይሓስብ ነይሩ። ስብሓት ግን ከምኣ እንተጌርካ ክትእሰር ኢኻ ኢሉ!"

ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገብረተንሳይ ምስ ቲቢኤስ ኣብዝነበሮ ፃንሒት ዝተዛረቦ!

15/06/2026

"እቶም ዘፅነቱና ኣካላት፣ ኣፅኒቶምና ጥራሕ ስቕ ኣይበሉን። እቲ ጭካነኦምን ሕማቕ ተግባሮምን ንሕና ንኽንደግሞን ንኽነቕፅሎን ኣውሪሶምና እዮም ከይዶም"

ዶ/ር ሙዑዝ ግደይ፣ ምስ ላንዳ ሪፖርት ኣብዝነበሮ ቃለመሕትት ዝተዛረቦ! ሙሉእ ትሕዝቶ ናይቲ ቃለመሕትት ንምክትታል ሊንክ ኣብ ኮመንት ኣሎ!

13/06/2026

ምኽሪ ንዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
------
ናትካ ፕረዚደንትነት ንዓና እንታይና እዩ? ንስኻ ፕረዚደንት ንኽትኮን ተባሂሉ ትግራይ ናብ ኩናት ካብትኣቱ፣ ወዲ ውለድ እሞ ሹሙ "ፕሬዚዳንት" በሎ!

Address

700 Bellevue Way NE
Addis Ababa
98004

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awramba Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Awramba Times:

Share