22/02/2026
🔷🔷 #ለራሳችን ከራሳችን በላይ አለልን!
📌 አብርሃም ወደ ግብጽ በእንግድነት ሲገባ አንድ ነገር አሰጋው፦ የሚስቱን የሦራን መልከመልካምነት ያዩ ግብጻውያን እንዳይገድሉት ፈርቶ ሦራን እህቱ እንደሆነች ብቻ እንድትናገር አስማማት።
👉ፈርኦንም በአለቆቹ አማካኝነት ውቧን ሦራ የራሱ ማድረግ ቻለ
ሚስቱ አደረጋት።
እግዚአብሄር ግን ከአብርሃም ጋር ስለነበረ በመጨረሻም ፈርኦን ላይ እግዚአብሄር መቅሰፍት አመጣ ፈርኦንም አብራምን ለምን ሚስትህ እንደ ሆነች አልነገርከኝም ውሰዳት ብሎ ሰጠው። (ዘፍ.12)
📌 አብርሃም ለራሱ በግሉ ጥንቃቄ አድርጓል ነገር ግን ጥንቃቄው ሚስቱን ከመነጠቅ አላዳነውም ነበር።
ከሰው ጥንቃቄ በላይ የእግዚአብሄር ጣልቃገብነት እንደሚበልጥ ማሳያው በቀላሉ እንዳሰበው እንደጠበቀው ሳይገድሉት ፈርኦን ሚስቱን እንካሲለው ነው።
ሰው ለራሴ ይበጀኛል ብሎ ያበጃጀው ነገር ጎጂ የሚሆንበት ጊዜ አለ ዋናው ቁምነገር ግን አካሄዳችን ከእግዚአብሄር ጋር ነው ወይ የሚለው ነው።
የአብራም አካሄድ ከእግዚአብሄር ጋር ስለነበረ አምላኩ ጥሎ አልጣለውም።
ለራሱ ትክክል መስሎ የታየውን የተጠነቀቀው ነገር ለጉዳት አሳልፎ ሲሰጠው ያመነውና
ሀገርህን ዘመዶችህን ቤተሰብህን ጥለህ
ውጣና እኔ ወደማሳይህ ምድር ገብተህ
ለልጅ ልጅ በረከት አደርግሀለሁ ያለውን
ጌታ ተማምኖ ስለወጣ ያመነው ህይወቱን ኑሮውን ጥሎ የተከለው ጌታ አላሳፈረውም!
አንተ ሰው አካሄድህ ከእግዚአብሄር ጋር ብቻ ይሁን እንጂ ያንተ ነገር አንድ ቀን ይሆናል! አንድ ቀን ይበዛል!!
📌 አካሄድህ ከእግዚአብሄር ጋር ሲሆን
አየህ ከራስህ በላይ እግዚአብሄር ይጠነቀቅልሃል!
እግዚአብሄር ይዋጋልሃል!
አብራም ሚስቴ ናት ቢል እንደሚገድሉት ነበር የጠበቀው እግዚአብሄር ካንተጋር ሲሆን ግን የተጠበቀው ነገር ቀርቶ ያልተጠበቀው መሆን ይጀምራል🔥🔥
አብራም እንዲ የከበደበት ነገር በእግዚአብሄር ፊት ቀላል ሆነ ፈርኦን በጣም በቀላሉ ሚስትህን ውሰድ አለው።
ከባድ የሆነው ተራራ የሆነው ነገር አካሄድህን ከእግዚአብሄር ጋር ስታደርግ
🔥ሰረጓጉጡ መስተካከል ይጀምራል
🔥 ተራራው መናድ ይጀምራል
🔥 የተበላሸው መስተካከል ይጀምራል
🔥 ከባዱ ቀላል ይሆናል
🔥በመንገድህ ላይ አንድ ነገር እርግጠኛ ሁን!
አካሄዴ ከእግዚአብሄር ጋር ነው?? ወይስ...
የሚሳካለት ሰው በራሱ የተጓዘ ሳይሆን ህይወቱን ዘመኑን ለእግዚአብሄር የሰጠ ሰው ነው!🔥
📌 እንደ አብራም እግዚአብሄርን ተማምኖ የወጣ ሰው አያፍርም!! እግዚአብሄርን ተማምነህ በራስህ ነገሮች ላይ ወስን!
አብራም በቤተሰቡ ላይ፣በኑሮው ላይ እንደ ወሰነው ወስን አንድ ቀን ጌታ የፈቀደ ቀን ነገርህ መቃናት ይጀምራል🔥
ክርስትና የመደላድል ጉዞ ሳይሆን የመሰጠትና የጭንቅ ጉዞ ነው መጨረሻው ግን ድልና ክብር የሆነ ህይወት!
የማይንገጫገጭ ፒስታ የሌለበት መንገድ ጠብቀህ ወደጌታ እንዳትመጣ! ነገር ግን አካሄድህን ከእግዚአብሄር ጋር በማድረግ ካለህበት ነገር ለመውጣት ወስን! የችግሩ ቁልፍ አካሄድን ከእግዚአብሄር ጋር ማድረግ ነው!! የችግሩ ቁልፍ
አንተ ጋር ነው!
በራስህ የመረጥከው መንገድ እንዳላዋጣህ ራስህ ምስክር ነህ ከዚህ በኋላ ግን የራስህን መንገድ ትተህ የጌታን መንገድ ወደ ክብር ህይወት የሚያደርሰው መንገድ ላይ ህይወትህን መንዳትና መምራት ጀምር የጌታ ፈቃድ ባንተ ላይ ይሰለጥናል🔥