chifrgochi.com

chifrgochi.com Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from chifrgochi.com, Photographer, Lalibela.

15/06/2025

ከንባብ ልዩ ቦንዳ የተላለፈ መልዕክት ልብስ ገዝታችሁ የጠበባችሁ ለናንተ ጊዜ ያለፈበት የምትሉት ያጠረ የሰፋችሁ ከለር ያልተመቻችሁ ልብስ ካላችሁ አልያም ደስ ብሏችሁ ገዝታችሁት ሳትለብሱ ያስቀመጣችሁት ምን ላድርገው ብላችሁ ግራ የተጋባችሁ ቁም ሳጥናችሁን ያጨናነቅ ሻንጣ ሳጥናችሁን ያጣበበ ልብስ ካላችሁ እንደ ልብሱ ሁኔታ አይተን እንገዛወታለን ግን ለመግዛት የምንፈልጋቸው የልብስ አይነቶች ከውስጥ ልብሶች ውጭ ማንኛውንም ልብሶች እንገዛለን ያሉበት ድረስ መተን እንገበያያለን።
በዚህ ቴሌግራም አድራሻ በውስጥ መስመር በፎቶም በቪድዮም ልትልኩልን ትችላላችሁ
https://t.me/+_9MXIdyvxF1iOWIy

ላልይበላ! ትኩረት
11/11/2023

ላልይበላ! ትኩረት

29/10/2021
የጥንቷ ላልይበላ-!
19/09/2020

የጥንቷ ላልይበላ-!

LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA  LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LA...
07/10/2018

LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELALALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA LALIBELA

ከዚያኔው የቀጠለ
"ህንፃው አደጋ ላይ ነው። አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ800 አመት በላይ ሞልቶታል።ህንፃው የተሰራለት መጠለያ ለቅርሱ እንደጥላ ታስቦ ከብዙ ነገር ማለትም ከፀሀይ ከዝናብ ከተፈጥሮአዊ አደጋወች እንደሚጠብቀው ታስቦ ቢሆንም የተሰራው አሁን ላይ ግን ትልቅችግር እንደሚፈጥርበት የአካባቢው ነዋሪ በዘርፉ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ባለሞያዎች ተናግረዋል። የተሰራው ሸልተር መጠለያነቱ ቀርቶ ለቅርሱ ስጋት ሆኗል። ሸልተሩ ሊያገለግልበት ከታቀደው ጊዜ ገደቡ ካለፈ 5አመት አልፎታል። ከፍተኛ ሀይል ያለው ነፋስ ከነፈሰ ደግፈው የያዙት እነዚህ ግዙፍ ክብደት ያላቸው ብረቶች መገጣጠሚያው ላይ ያሉት ቡለኖች ከነበሩበት ይዞታ አንፃር እየሰፉና ለመላቀቅ ሰጋት እየሆኑ ነው። የታሰሩበት ቡለኖች ተለያዩ ማለት የተጋረጠው አስከፊ አደጋ ሆነ ማለት ነው ከወዲሁ መፍትሔው በባለ ሞያወች ተጠንቶ ከ800ሚሊዮን እስከ 1ቢለዬን ብር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል ገንዘቡ ተሰባስቦ መፍትሔው ካልተበጀ ስጋቱ በእጥፍ ይጨምርና መስተካከል ወደማይችልበት ደረጃ ይሸጋገር ይሆን ብዬ "እሰጋለሁ" ስለ መካነ ቅርሱ የሚነገረው ሁሉ ምናባዊ ቅዠት እንደሚመስል በጊዜው ለሚጎበኙት ቱርስትም ይሁን ምእመን በድፍረት መናገር ይቻላል። ነበርኮ እንደዛ ነበርኮ እንደዚህ ማለቱ የሚጠቅም አይመስለኝም ሁሉም የኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ ሊጮህ ሊከራከር መፍትሔ ሊያፈላልግ ግድ ነው። የሁላችነንም መመኪያ መጠሪያ ጋሻ መካሻ ለሆነው ለዚህ ድንቅዬ ቅርስ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ልናበረክት ተገቢ ነው። የአካባቢው ማህበረሰብ እንደተለመደው ጥያቄወችን በማንሳት ተፈፃሚነቱን እያፋጠነ ይገኛል በከተማዋ በልማቱ ዘርፍ ጥያቄወቹ ብዙ ቢሆንም ቅድሚያ ሊታሰብበት የሚገባው ህንፃችን መሆኑን አምነው ተጋድሎ ለሚያደርጉት ለቅዱስ ንጉስ ላልይበላላ ህዝብ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው። ከዛሬ 26 አመት በፊት የተጠየቀ የ60 ኪ·ሜ የኮረኮንች መንገድ በአስፓልት እንዲቀዬር ጥያቄ ቢያቀርብም ነዋሪው ይሔው እስከ ዛሬ ድረስ እንኳን አልተፈታም ይሔ ሁሉ ተፅእኖ ለምን? ተመለሰ የሚለው ጥያቄ ራሱ አመርቂ ምላሺ አልተሰጠውም የሚሰራው መንገድ አሳፋሪ ለመሆኑ የዬ ምስክር ነው አሁን ግን በማይደራደርበት ቅርስ ህይወታቸውን ሳይቀር እንደሚሰው ቆርጠው ታጥቀው ተነስተዋል። ይሄኮ የአለም ቅርስ ለእነሱ ደግሞ መኩሪያም ነው። የእውነት መደራደሪያ አይሆንም አለም በአንድ አጨብጭቦ የመሰከረለት በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ይህ ፍልፍል ውቅር አቢያተ ክርስቲያን አሻራው እንኳን እዝችው ሀገራችን ኢትዮጵያ አክሱም ውስጥ ብቻ ነው የተገኘው። እንደ ተመራማሪዋ ገለፃ ሌላ አለም ላይየሌለ እኛጋ ብቻ ያለ መለያችን መመኪያችን አሻራችን ንጉስ ቅዱስ ላልይበላ ነው። የሀገር ኩራት ለሆነው ለዚህ ድንቅ እና ብርቅ ቅርስ የበኩላችንን እንወጣ መልእክቴ ነው። እግዚአብሔር ይጠብቅልኝ ባላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛልኝ ንፁህ ምኞቴ ነው።

21/08/2018

ወልዱ ሀብቴ♥
♥♥♥♥♥♥
አሸን ፍቅር አሸን ደስታ
የታሪክ ባለቤት የኢትዮጵያ ዋልታ
አምረሺ ድመቂልኝ የኔ ውቧ ላስታ
በልዩ በአሉ ባሸንድዬው ሆታ♥
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥♥
ሰላም ለምወዳችሁ እንዴት ከረማችሁ ድንቅ ታሪክ ወዳለባት ባለም መድረክ ኢትዮጵያውያን በነገስንበት ከአክሱም ስረወ መንግስት በመቀጠል የዛጎዬ ሰደረወ መንግስት ያበበባት የስልጣኔ አሻራ በፅሁፍ በአፈ ታሪክ ሳይሆን በአይን ታይቶ በእጂ ተዳሶ የማሳመን ብቃት ያለው የጥንት ታሪካዊቷ ሀገራችን እንቁ ሀብታችን መገለጫ መዋቢያችን መኩሪያ መመኪያችን ለሆነው ታሪካዊ ቅርስ መገኛ ወደሆነችው ቅዱስ ላልይበላ የጥበብ አሻራውን እስከዛሬ ድረስ ያስቀመጠባት ላስታ ላልይበላ በየአመቱ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት የሚጠበቅና በየአመቱ የሚፆመው የፍስለታ ፆም እንደተጠናቀቀ ነሀሴ 16/12/ 2010 ዓ/ም በአካባቢው በባህላዊ ወግ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ለባህል መሰረት የልጃገረዶች ጨዋታ የሆነውን የአሸንድዬ ባህላዊ ዘፈን ባህላዊ ውዝዋዜ ባህላዊ የአለባበስ ባህላዊ የፀጉር አሰራር ድምፀ መረዋ በሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ ተወላጂ እንስቶች በዓሉ ይደምቃል ይዋባል በአሉን ከሚያደምቁት መካከል እድሚያቸው ለትዳር ያልደረሱ እንቡጥ ፅጌረዳ ወጣት መልከ መልካም ሴቶች የሚደምቁበት የሚዋቡበት የሚያጌጡበት የዛሬን አያድርገውና የሚታጩበት ጊዜ ነው።
ይህ ልዩ የሆነ ባህላዊ ጭፈራ የታከለበት ደማቅ ስነስርአት ከሀይማኖቱም ጋር ተያያዥነት አለው።
ዝግጂቱ በዓሉ ከመድረሱ ቀደም ብሎ ዝግጂት ይደረጋል በበዓሉ ለመሳተፍ ከመላው የዓለማችን ጫፎች ለመታደም ከመምጣታቸውም ባለፈ በክልሉ ያሉ ወረዳወችም በህብረትና በፍቅር በጉጉት የሚጠብቁት አመታዊ ክብረ በዓል ነው።
በአቅራቢያችን ያሉ ክልል ወረዳወችም እንደ ትግራይ ክልል አሸንዳ በሚል መጠሪያ ስም ሲከበር በሰቆጣ ወረዳ ሻደይ በሚል መጠሪያ ስም ሲከበር በቆቦ ወረዳ ደግሞ ሶለል ተብሎ በሚታወቀው ባህላዊ ጭፈራ ስርአቱን ሳይቀይሩ ባህሉን ሳይበርዙ በቋንቋ ልዩነት ብቻ በተመሳሳይ ጊዜና ወቅት ባማረና በደመቀ ሁኔታ ባህሉ ያከብሩታል።
በዚህ ክብረ በዓል ወዳጂነትን አንድነትን ሰላምን ፍቅርን ባህሉን ለትውልድ ማሸጋገርንም ጭምር በማሰብ የተሻለ የገቢ ምንጭ ለማግኘት ቋሚ ሆኖ በየአመቱ ሊያጓጓ በሚችል ተሳታፊወችን በመጨመር ታዳሚያኑን በማብዛት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።
አሸንድዬ ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት ወንዶች ወንድሞቻቸው የሌላ ሰፈር ወጣቶች እንዳይረብሻቸው እንዳይተናኮሏቸው የእድሜ ገደብ ሳይኖረው ለደህንነታቸው ጥበቃ ይደረግላቸዋል። ድንገት በአቋም ፈርጠም ያለ ወጣት ሊከተላቸው ካልቻለ
በእድሜ አነስ ያሉ የአካባቢው ነዋሪ ህፃናት ወንዶች ሳይቀሩ ግዴታቸውን ለመወጣት እህቶቻቸውን ተከትለው ድንገት ባጋጣሚ ለሚፈጠረው የደህንነት ስጋት ለታላቆቻቸው መልእክት በማድረስ ግዴታቸውን ይወጣሉ።
የዚህ ባህላዊ ጭፈራ ከተለመደው አከባበር በተሻለ እንዲከበር ያስፈለገበት ዋናው ምክኒያት ለትውልዱ ዘላቂ የሆነ ትውፊታዊ ስርዓት ያለው ባህል ከማውረስ አንፃር ነው።
የአመት በአሉ አከባበር በማህበረሰቡ በሚጠመቅ ጠላ በቡሔ ዳቦ ያለው አርዶ ለሌለው የሚያካፍልበት ሁሉም የማህበረሰብ አካል የሚደሰትበት በደረሰ እያለ የተመኘው ክብረ በአል ደርሶ ሲታደም ደስታው ወደር ይታጣለታል።
ላስታ ላይ በአሸንድዬ በበአሉ መገኘት መታደም ብዙ ባህላዊ የሆኑ አስደሳችአዳዲስ ነገሮችን በማየት ከሌሎች ባህላዊ እሴቶች ጋር የሚያወዳድሩበት ክብረ በዓል ነው አሸንድዬ።
በክብረ በአሉ ጭፈራ በየ መንደሩ እየዞሩ ከማድመቃቸው በፊት በአካባቢው ባለ ደብር ቤተ ክርስቲያን ሔደው አመት ከአመት እንዳደረሳቸው አመስግነው ጨፍርው ለሚመጣው አመት ተስለውጉዟቸውን በጭፈራ እያደማመቁ በመቀጠል በአካባቢው የተከበሩ የእድሜ ፀጋ አዛውንት በሚባሉ ቤት በመጀመር አመት በአላቸውን ያደማምቃሉ።
በእለቱ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ በሀይማኖት አባቶች ሀይማኖታዊ ቅኔ ዝማሬወችም ተካተውበት ለእንስቶቹ በእምነታቸው እንዲበረቱም እንዲጠነክሩም ይመረቃሉ።
አሸንድዬ አዲስ መንፈስን ማደስ የሚያስችልየተለዩ ያልተለመዱ ውብና ድንቅ ባህላዊ ነገሮችን የምናይበት ልዩ አመት በዓል ነው አዛውንቶ ወጣቱ አሮጊቱ ፈዞ ፈንጥዞ በስሜት ጭልጥ ብሎ የሚጓዝበት ስሜትን ኮርኳሪ መልካሙን ጊዜ ማስታወሻ የሆነ ለየት ያለ ተናፋቂ ክብረ በአል ነው አሸንድዬ። በላስታ ምድር♥

15/12/2017

•••ወልዱ ሀብቴ……
ታህሳስ 06/4/2010ዓ,ም

"ለኑ…… ላስታ"

ቅዱስ ላልይበላ ባምላክ በፈጣሪ
ታምኖ ተመርጦ ነው ይህን ታሪክ ሰሪ
የጥበብ አሻራ ትንግርት ታምር አብሪ
የላስታው ፍሬ የሮሀው ጀግና
አለም ነው ክብሩ ህንፃው በገና
በምነቱ ቋጥኝ ጥበብን አሳዬ
እየሩሳሌምን ባምሳሉ ጎበኜ
የላስታው ፍሬ የሕንፃው ዋሻ
እምነቱ ለሱ ሆኖለት ባሻ
የዘላለሙ የምነቱ ሚስጥር
ቅርሱን ለማዳን እንዲህ ሲታትር
ይለፍ ለትውልድ ዘመን ይሻገር
የአለቱ ታምር የድህነት መንበር
ለዘመን አብርቷል ዘመናትን ይክበር
ቃሉን ጠብቆ ለትውልድ ሊያሻግር
ቀና ደፋ ይላል ስተትን ላይሰራ
ታሪክ መድገም ባይችል ታሪክን ሊያጋራ
የላልዬን ቅርሱን እንጠብቅ በጋራ
ብሎ ተናገረ ነጋሪት አሰማ
ወደፊት ነው እንጂ የምን ወደኋላ
ለልጂ ልጂ ደራሺ
ትውልድን አዳሺ
ዘላለም ክብር የእልፍ ነጋሺ
ላልዬ ክብር መመኪያ ኮነው
ጎብኝን ያስገረመ ከልብ ያሳመነ
ተጨማሪ አያሻው ህንፃው ተናጋሪ
ቆርጦ ፈልጦ ልጦ ድንጋይን አዘዘ
ቅዱስ ላልይበላ ለዓለም ተናዘዘ
ጥበብ ከፈጣሪ የተሰጠህ ለታ
ያሻህን ከማድረግ ከልካይ የለም አለ
የታላቁን ንጉስ ታሪኩን እናስስ
ብለው ተነሱ ባንድነት መንፈስ
መጣ ወደፊት ታሪክ ሊሰራ
ህዝቧ ቀዳሚ በተግባር ኗሪ
ይሰራል ታሪክ ሆኖ ቀዳሚ
አለሁ ከጎንህ ብለህ አጂበው
አቅም ጉልበትክን ፍቅርን አካፍለው
አትሰስት ለሱ ጊዜ ገንዘብክን
ታሪክ ለመድገም ታሪክ ተጋራ
ጥረት ውጥረቱን!
ድካም ልፋቱን!
ሀሳብ ጉልበቱን!
ህዝቡ ለቅርሱ ሊሆን መከታ
ቆርጦ ተነስቷል መስዋእት ሊሆን
ህይወት ስትንፋስ ላይሰስት ላፍታ
እንቁዋን ላስታ
በላጯን ለስታ
ጠብቃት ጌታ
ሆነህ አለኝታ!
የንጉስ ልጆች ነን የላልይበላ! !!!

ከዚያኔው የቀጠለ "ህንፃው አደጋ ላይ ነው። አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ800 አመት በላይ ሞልቶታል።ህንፃው የተሰራለት መጠለያ ለቅርሱ እንደጥላ ታስቦ ከብዙ ነገር ማለትም ከፀሀይ ከዝናብ  ...
26/11/2017

ከዚያኔው የቀጠለ
"ህንፃው አደጋ ላይ ነው። አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ800 አመት በላይ ሞልቶታል።ህንፃው የተሰራለት መጠለያ ለቅርሱ እንደጥላ ታስቦ ከብዙ ነገር ማለትም ከፀሀይ ከዝናብ ከተፈጥሮአዊ አደጋወች እንደሚጠብቀው ታስቦ ቢሆንም የተሰራው አሁን ላይ ግን ትልቅችግር እንደሚፈጥርበት የአካባቢው ነዋሪ በዘርፉ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ባለሞያዎች ተናግረዋል። የተሰራው ሸልተር መጠለያነቱ ቀርቶ ለቅርሱ ስጋት ሆኗል። ሸልተሩ ሊያገለግልበት ከታቀደው ጊዜ ገደቡ ካለፈ 5አመት አልፎታል። ከፍተኛ ሀይል ያለው ነፋስ ከነፈሰ ደግፈው የያዙት እነዚህ ግዙፍ ክብደት ያላቸው ብረቶች መገጣጠሚያው ላይ ያሉት ቡለኖች ከነበሩበት ይዞታ አንፃር እየሰፉና ለመላቀቅ ሰጋት እየሆኑ ነው። የታሰሩበት ቡለኖች ተለያዩ ማለት የተጋረጠው አስከፊ አደጋ ሆነ ማለት ነው ከወዲሁ መፍትሔው በባለ ሞያወች ተጠንቶ ከ800ሚሊዮን እስከ 1ቢለዬን ብር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል ገንዘቡ ተሰባስቦ መፍትሔው ካልተበጀ ስጋቱ በእጥፍ ይጨምርና መስተካከል ወደማይችልበት ደረጃ ይሸጋገር ይሆን ብዬ "እሰጋለሁ" ስለ መካነ ቅርሱ የሚነገረው ሁሉ ምናባዊ ቅዠት እንደሚመስል በጊዜው ለሚጎበኙት ቱርስትም ይሁን ምእመን በድፍረት መናገር ይቻላል። ነበርኮ እንደዛ ነበርኮ እንደዚህ ማለቱ የሚጠቅም አይመስለኝም ሁሉም የኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ ሊጮህ ሊከራከር መፍትሔ ሊያፈላልግ ግድ ነው። የሁላችነንም መመኪያ መጠሪያ ጋሻ መካሻ ለሆነው ለዚህ ድንቅዬ ቅርስ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ልናበረክት ተገቢ ነው። የአካባቢው ማህበረሰብ እንደተለመደው ጥያቄወችን በማንሳት ተፈፃሚነቱን እያፋጠነ ይገኛል በከተማዋ በልማቱ ዘርፍ ጥያቄወቹ ብዙ ቢሆንም ቅድሚያ ሊታሰብበት የሚገባው ህንፃችን መሆኑን አምነው ተጋድሎ ለሚያደርጉት ለቅዱስ ንጉስ ላልይበላላ ህዝብ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው። ከዛሬ 26 አመት በፊት የተጠየቀ የ60 ኪ·ሜ የኮረኮንች መንገድ በአስፓልት እንዲቀዬር ጥያቄ ቢያቀርብም ነዋሪው ይሔው እስከ ዛሬ ድረስ እንኳን አልተፈታም ይሔ ሁሉ ተፅእኖ ለምን? ተመለሰ የሚለው ጥያቄ ራሱ አመርቂ ምላሺ አልተሰጠውም የሚሰራው መንገድ አሳፋሪ ለመሆኑ የዬ ምስክር ነው አሁን ግን በማይደራደርበት ቅርስ ህይወታቸውን ሳይቀር እንደሚሰው ቆርጠው ታጥቀው ተነስተዋል። ይሄኮ የአለም ቅርስ ለእነሱ ደግሞ መኩሪያም ነው። የእውነት መደራደሪያ አይሆንም አለም በአንድ አጨብጭቦ የመሰከረለት በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ይህ ፍልፍል ውቅር አቢያተ ክርስቲያን አሻራው እንኳን እዝችው ሀገራችን ኢትዮጵያ አክሱም ውስጥ ብቻ ነው የተገኘው። እንደ ተመራማሪዋ ገለፃ ሌላ አለም ላይየሌለ እኛጋ ብቻ ያለ መለያችን መመኪያችን አሻራችን ንጉስ ቅዱስ ላልይበላ ነው። የሀገር ኩራት ለሆነው ለዚህ ድንቅ እና ብርቅ ቅርስ የበኩላችንን እንወጣ መልእክቴ ነው። እግዚአብሔር ይጠብቅልኝ ባላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛልኝ ንፁህ ምኞቴ ነው።

21/11/2017

ጋራራው የትምአለ
ሽንተረር ወንዙ(2)
እኔን የናፈቀኝ
ሰው ከነ ወዙ(2)
ማን መኖር ይችላል ርቆ ከናቱ
ኢትዮጵያዬ እያለ በየሄደበቱ''

ቅዱስ ላልይበላን የማያውቅ ሊያውቀው የሚገባ የሚያውቀው ደግሞ ላላወቁት በማስተዋወቅ ይተባበረኝ በማለት መልእክቴን አጋራለሁ። በቀደምት አያቶቻችን በእውነተኛ እናትነትና አባትነት ላሳደጉን።ፍቅ...
18/11/2017

ቅዱስ ላልይበላን የማያውቅ ሊያውቀው የሚገባ የሚያውቀው ደግሞ ላላወቁት በማስተዋወቅ ይተባበረኝ በማለት መልእክቴን አጋራለሁ።
በቀደምት አያቶቻችን በእውነተኛ እናትነትና አባትነት ላሳደጉን።
ፍቅርን ላጋሩን ለሐይማኖት እራሳቸውን አሳልፈው ለነብሳቸው የኖሩ።
ስጋቸውን የበደሉ ለሀገር ፍቅር ለሀይማኖት ክብር ህይወታቸውን የሰው፣
የእውነተኛ ማንነት ተምሳሌት የኢትዮጵያ ጀግኖች ዛሬም ድረስ ሐብቶቻችን ናቸው። ካወረሱን ከሰጡን አንጡራ ሐብቶቻችን የመጀመሪያዋ እናት ሀገር ኢትዮጵያችን ቋንቋ ባህልና ሐይማኖት እነዚህ ቢሆኑም የማይታደስ የማይበረዝ የተለዬ ለመንፈስ እርካታ ለህይወት አለኝታ ፣
የሆነ ሐይማኖት አለን ኦርቶዶክስ (ለሐይማኖቱ ተከታዮች) ሐይማኖት መዳኛ መፈወሻ ጭንቅን በሺታን ማስረሻ ለእግዚአብሔር ቤት ድልድይ መድረሻ ነው። ይህ ህይወት የዘለዓለም ድህነት ማስታወሻ የምድር ታላቅ በረከት ነው ሐይማኖት። ቅዱሳን ነገስታት በገዙዋት ባስተዳደሩዋት ሀገራችን ኢትዬጵያ የበረከት የቱርፋት መንደር ነበረች፣ ድሮ ድሮ ከኛ በፊት በፊት ዛሬ ዛሬማ ዋ ዋ ብቻ ነው ።
የአሁኑ አገዛዝም ስርአትም ተከድኖ ይቆዬን ብቻ መጨረሻውን ፍፃሜውን ያሳምርልን።
እና ላልይበላ ወይም ላሊበላ ሁለቱም መጠሪያዋ ስሟ ነው ደስ ባላችሁ እወቁዋት ንጉስም ቅዱስም ሆኖ ድፍን 40 አመታትን በገዛው ቅዱስ ንጉስ ላልይበላ ስያሜ የምትጠራ ትንሺዬ ታሪካዊ ሀገር ናት ይገርማል መልካም ስም ለዘመናት ደምቀው እንደተፃፉ ትውልድ ያሻግራሉ። አንዱ ጋዜጠኛ ይሔን ብሎ ነበር "የእውነት ሰው ከሆንክ" ቅዱስ ንጉስ ላልይበላን ተመልከት በምትመለከተው በምዳስሰው ነገር ሳትወድ በግድህ ታምናለህ እንዴት ሰውን ያህል ፍጡር ከአንድ አለት ከሙሉ ቋጥኝ ይህን የመሰለ ትንግርታዊ ህንፃ ዘመናዊነት ባልዋጀው? ቴክኖሎጂ በሌለበት? ሰው ማንበብም መፃፍም ባልተዳረሰበት? በዚያ ዘመን እንዴት ታነፀ የዘወትር ጥያቄህ ነው።
ይች የህዝብ ሀብት ይች ተምሳሌታዊት ሀገረ ላልይበላ ያለችበት ሁኔታ በጣም አስጊና አስደንጋጭ ነው ከከተማዋ ማስተር ፕላን ጀምሮ እስከ ታሪካዊው የአለም ቅርስ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ። ዩኒስኮ ከመዘገባቸው ታሪካዊ ቦታወች አስፓልት መንገድ የሌላት ሆስፒታሏ ያልተሟላ መፀዳጃ ስፍራወች በቅጡ ያልተሟላላት ሁሉም የራስና የራሱን ጥቅም የሚያሳድድባት ከብዙወች በፊት ብዙ የነበራት ግን ከብዙወች ኋላ የቀረች ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ የማህበረሰቡ ነዋሪና በአመራር ወንበር አሟዋቂወች መሆኑ ይሰመርበት። በአብዘሀኛው የከተማዋ ነዋሪ የሚተዳደረው በቱሪስት በሚመጣ ገንዘብ ነው። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 90·9% የሚገኘው ከቱርስት ነው። አሁን ህዝቡን የሚያስደነግጥ አለምን የሚያስደነብር ትልቅ ችግር ። ይቀጥላል?

ይድረስ ለታሪካዊ ማንነታችን ተቆርቋሪዎች ብቻነጭ በገዛን ኑሮ እያልክ ቅኝ ግዛት ለምትናፍቅ እና አሁንም በተዘዋዋሪ መንገድ ቅኝ እየተገዛህ ላለህ ከንቱ ትውልድ ይኸ አይመለከትህም♥♥♥♥ ለኢት...
01/11/2017

ይድረስ ለታሪካዊ ማንነታችን ተቆርቋሪዎች ብቻ

ነጭ በገዛን ኑሮ እያልክ ቅኝ ግዛት ለምትናፍቅ እና አሁንም በተዘዋዋሪ መንገድ ቅኝ እየተገዛህ ላለህ ከንቱ ትውልድ ይኸ አይመለከትህም

♥♥♥♥ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
♥♥♥♥ ይድረስ ለላስታ ላሊበላ ህዝብ እና ጋይዶች
✿✿✿✿ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች
✿✿✿✿ በአለም ላይ ያላችሁ ለመላው ኢትዮጵያዊ የቅርሱ አፍቃሪዎች እና ተቆርቋሪዎች፡፡ እንዲሁም
★★★★ በዘርፉ የተሰማራችሁ ሙሁራንና ተመራማሪዎች በሙሉ
# # # # ሀገራዊ ትኩረት የተነሳው ባለቤት ያጣው ዘመናትን ቸሻግሮ እኛ ዘመን የደርሰው እና በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የቅዱስ ላሊበላ ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመታደግ የድርሻችንን እንወጣ ዘንድ አጅግ ውብና ማራኪ በሆነው ኢትዮጵያዊነት ስም ጥሪየ ይድረስ እላለው፡፡
*****ሁላችንም ሀሳባችን እናንሳ
*** ሸር እናድርግ
*** የመፍትሄ ሀሳብ እናምጣ

ዛሬ በጥዋት ከቤት ወደ ቢሮ በምጓዝበት ወቅት ሁሌ ውስጤ ላይ የነበረው እና በየ አመቱ ወደ ቅድስቲቱ ደብረ ሩሃ ስሄድ ሰላም የሚነሳኝ ጉዳይ በብስራት FM የሬዲዮ ጣቢያ ስሰማ ጥርጣሬየ ደረሰ ስጋቴ ተከሰተ ፡፡
የሬዲዮ ጣቢያው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ፋካሊቲ መምህር የሆኑ አንድ ዶክተርን ዋቢ በማድረግ የታላቁ የጥንታዊው እና የዓለም ዓቀፉ የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ከዛሬ 10 ዓመታት በፊት ለቤተ መቅደሱ መጠለያ በዩኒስኮ የበጀት ምንጭ በአለማቀፍ የጣሊያ ተቋራጭ የተሰራው ሸድ ለቤተ መቅደሱ ትልቅ ሰጋት እና ከፍተኛ አደጋ መሆኑን ለብስራት ኤፍኤም አሰታውቀዋል፡፡ በማለት ሲዘግብ እጅግ አዘንኩ ከዚህ በፊት አርክቴክት ዩሃንስ በ ማህበራዊ ሚዲያ በተወሰነ መልኩ እንዳቀረበው አይቻለሁ፡፡ የሚገርመው የአማራ ብዙሃን መገናኛ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ የሰሜን ወሎ ቱሪዝም መምሪያ የጎንደር እና የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የቱሪዝም ትምህርት ክፍል የአካባቢው ጋይድ ማህበር እና የደብሩ አስተዳደር ይኸን እያዩ በዝምታ ማለፉ በታሪክ ተወቃሽ ከመሆንም በላይ ህግ በህግ ሲዳኝ ተጠያቂ እንደሚሆኑ እርግጠኛ ነኝ፡፡

በመጀመሪያ ከዲዛይኑ ጀምሮ ስራው እስኪ ጠናቀቅ ድረስ በሚሰራው አለማቀፍ ተቋራጭ እና በአካባቢው ተወላጆች ፡ በጋይድ ማህበሩ መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ነበረበት፡፡ አልፎ አልፎ ሳይንቲፊክ ኮሚቴው በቦታው እየተገኘ ማስተካከያ እንዲደረግ ሲያደርግ እንደነበረ የሚገልፁ ወገኖች አሉ፡፡

1. በተለይ ዲዛይኑ አሁን መጠለያውን የተሸከሙት ምሰሶዎች / ፔላሮች/ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ሆነው ጣራው ተከፋች እና ተዘጊ እንደሚሆነ የተወራ ቢሆንም ስራው ግን ከዚህ የተለየ ሆኖ ነው የተሰራው::

2. በሌላ በኩል ለስራው የተቀመጠው ማቴሪያል እና ስራላይ የዋለው የተለያዩ መሆኑን የሚገልፁ አሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደማሳያ የሚገለፀው የላሊበላ ጋይዶች ማህበር ለምዕመናኑ ግንዛቤ በመፍጠር በተደጋጋሚ ከተቋራጩ ድርጅትጋር እልክ አስጨራሽ ትግል ሲያደርጉ እንደነበር ያስታውሳሉ ፡፡

3. ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣናት በጊዜው የሚነሱ ጥያቄዎችን በድንብ አጢኗቸው ቢሆን ኑሮ እና ያኔ የቀረበው የላሊበላ ህዝብ ጥያቄ በግልፅ ተፈተው ቢሆን አሁን ላይ መጠለያው ለቤተመቅደሱ ስጋት አይሆንም ነበር የሚሉ በረካታ አካላት አሉ፡፡

አሁን ያለፈውን አሰራር ማንሳቱ ጥቅሙ አይታየኝም እንጅ የተጠቀመው ብረት የፕላስቲክ ጣራ ለመሸከም ክብደት ብዙ ቶን የሚመዝን ብረት ለምን ተደረገ?? ጣራው በቀላሉ በእሳት ሊቀጣጠል የሚችል ፕላስቲክ ለምን ሆነ? የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የስራ ውል ስምምነት ከዩኒስኮና ከተቋራጩ ድረጅት ሲወስድ ጊዜው ሲደርስ በማን እንዴት እና መቼ እንደሚነሳ ለምን ውል ስምምነት ውስጥ አልተካተተም ??? ከተካተተ በውሉ መሰረት እንዲነሳ ያልተደረገው ለምን ይሆን???

★★★ በትልቁ ግን ነጮች የእኛን እድገት የአኩሪ ታሪክ ባለቤት መሆናቸን መች ይወዳሉ?? ወደ ሀገር ከሚገቡት ውስጥ ሰንቱ ሌባ ስንቱ ዘራፊ አንደሆነ ፈጣሪ ይቁጠረው ፡ከዚህ በመነሳት ገና ከመጠለያው ስራው ጀምሮ በተንኮል የተሞላ ቅርስ የማጥፋት እኩይ ድርጊታቸው ጎልቶ የወጣ በመሆኑ አሁን ሆን ብለው ጀሮ ዳባ ልበስ አንዳሉ ማሳያ ድርጊት ነው፡፡ ነጮች አይደለም ይኸን ያህል ግዙፍ ስራ ሰርተው ትንሽ ለሚሉት ድርጊት የአገልግሎት ዘመን ያለፈበትን ነገር ተሎ በማስወገድ ይታወቃሉ፡፡ እና ዛሬ ለምን ለእኔ በቀልም እና ቅርሱን የማውደሚያ ረቂቅ ስልት ይመስለኛል ፡፡

★★★ ሌላው ጉዳይ ግን አሁን በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አባቶች ተወያይተው ለጠቅላይ ሚኒስቴር ሀይለማርያም በደብዳቤ እንዲጠየቅ ውሳኔ አሳልፏል የሚል ዜና ✿✿✿ሀራ ተዋህዶ ይዛ ወጥታለች ፡፡

ይበል የሚያስብል ቢሆንም በጣም የዘገየ መሆኑ ግን አለም ያውቀው ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ የኛ መሪዎች ደግሞ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ ቢያንስ ቢያንስ ከ5-10 ዓመት ይወስድባቸዋል ፡፡ እዚህ ላይ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶቻችን እንዳይሻክሩ በሚል ፍርሃት ገፍተው ላይሄዱም ይችላሉ ብየ አስባለሁ፡፡

የኔ የራሴ የመፍትሄ ሀሳብ
1. አለማቀፋዊ ዕውቀት ያለው ከህግ ፡ ከምህንድስና፡ ከቅርስ ጅኦግራፊያዊ ባለሞያ የተውጣጡ ኮሚቴዎች ማቋቋም

2. ፋታ የማይሰጥ ከላሊበላ እና ከአካባቢው ለቅርስ ጥበቃ ባለስልጣናት ለጠቅላይ ምኒስትር ለተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄዎችን ማቅረብ

3. የውጭ ጎብኝዎችን ወደ ቅዱስ ላሊበላ እንዳይደርሱ በማገድ ለአለማቀፉ ተቃውሞ ማሰማት
( ይኸን ማድረግ ግን ለሀገሪቱም ሆነ ለላሊበላ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ ከፍተኛ ነውና የመጨረሻ አማራጭ ይሆናል )
4. አባቶች ጥያቄውን ተሎ እንዲያቀረቡና ተሎ ምላሽ እንዲያገኙ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፡፡

♥♥ የእናንተስ የመፍትሄ ሀሳብ ምንድነው?♥♥

Address

Lalibela

Telephone

+251916586944

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when chifrgochi.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category