28/07/2026
⚠️ ጠቃሚ ማሳሰቢያ ከቃቆ ፒክቸርስ (Kako Pictures)! ⚠️
ውድ እና የተከበራችሁ የቃቆ ፒክቸርስ ቤተሰቦች፤
በአካልም ሆነ በስልክ መስመር በመደወል "ወላይታ ሶዶ መምህራን ግቢ" የተከፈተው አዲስ የፎቶ ቤት የእናንተ ነው? ብላችሁ ለጠየቃችሁን በሙሉ ምላሻችንን ለመስጠት እንወዳለን።
ይህ በስማችን የተከፈተው ፎቶ ቤት የእኛ እንዳልሆነ እና በእኛ ስም ሌላ አካል የከፈተው መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን። ከተቋማችን እውቅና እና ፍቃድ ውጭ በስማችን ለሚሰጡ ማናቸውም አገልግሎቶች ቃቆ ፒክቸርስ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልጻለን።
መልካም ዜና! 🎉
ቃቆ ፒክቸርስ በቅርቡ በወላይታ ሶዶ ከተማ ላይ በአዲስ እና እጅግ ዘመናዊ በሆነ መልኩ ስራ የሚጀምር መሆኑን በደስታ እንገልጻለን። አድራሻችንን እና የምንጀምርበትን ትክክለኛ ቀን በቅርቡ በይፋዊ ገጾቻችን የምናሳውቅ ይሆናል።