06/11/2026
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የሚገኘው የዳግማዊ ደብረ ሊባኖስ ቅዱስ ያሬድ ወአቡነ ፊልጶስ ገዳም ስር የሚተዳደረው 'መካነ ጥበባት ዘቅዱስ ያሬድ የአብነት ትምህርት ቤት'፣ ዕድሜያቸው ከ8 ዓመት ጀምሮ ለሆኑ ታዳጊዎች ያዘጋጀው ልዩ የበጋ (የክረምት) አዳሪ ትምህርት ምዝገባ ሊጠናቀቅ 7 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
ቀደም ሲል እስከ ግንቦት 30 ቀን ድረስ የነበረው የምዝገባ ማጠናቀቂያ ጊዜ፣ በርካታ ወላጆችን ለማስተናገድ ሲባል እስከ ጁን 17 (ሰኔ 10) ድረስ የተራዘመ መሆኑ ይታወሳል። በመሆኑም ወላጆች ይህንን ወርቃማ አጋጣሚ በመጠቀም በቀሩት ጥቂት ቀናት ውስጥ ልጆቻቸውን በፍጥነት እንዲያስመዝግቡ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ጥሪውን አስተላልፏል።
ይህ በአዳሪነት የሚሰጠው የ8 ሳምንታት ልዩ የክረምት ትምህርት፣ ህጻናት እና ታዳጊዎች በማንነታቸው ኮርተው፣ በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶች ታንጸው እንዲያድጉ ለማድረግ ያለመ ነው።
የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች፦
* የመጽሐፍ ቅዱስ እና የሥነ-ምግባር ትምህርት
* የአማርኛ እና የግዕዝ ቋንቋ
* የውዳሴ ማርያምና የቅዳሴ ትምህርት
* ዘመናዊ የኮምፒውተር ስልጠና
* መንፈሳዊ የዜማ መሳሪያዎች ስልጠና (በገና፣ ክራር እና ከበሮ)
የትምህርቱ ቆይታ (በሁለት ዙር)፦
* አንደኛ ዙር፡ ከሰኔ 15 እስከ ሐምሌ 12 ቀን
* ሁለተኛ ዙር፡ ከሐምሌ 13 እስከ ነሐሴ 10 ቀን